የሃይማኖት ፅንፈኝነት መዋጋት ማለት የእምነት ድንጋጌዎችን እንዳይፈፀሙ መገደብ ማለት አይደለም!! አቡ ዳውድ ኡስማን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ፅንፈኝነት ማለት የራስን አስተሳሰብ በግዳጅ ሌሎች ላይ ለመጫን መሞከር፣የሌሎችን አስተሳሰብ ባለማክበር በግዳጅ ለማጥፋት መንቀሳቀስ ሲሆን ዜጎች ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎቻቸውን የሌሎችን መብት ሳይጋፉ በነፃነት እንዳይተገብሩ ማገድም የፅንፈኝነት አንዱ መገለጫ ነው፡፡

እኔ የመረጥኩልሽን አለባበስ ተከተይ ብሎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ማስገደድ ፣ታምኖበት የሚደረግን ሃይማኖታዊ አለባበስ በግዳጅ አውልቁ ማለት ፅንፈኝነት ካልሆነ ከቶውንስ ምን ሊባል ይችላል??

የሀይማኖት ጽንፈኝነት አመለካከት እንጂ አለባበስ አይደለም፣ ኒቃብን መግፈፍ አመለካከትን እይቀይርም፣ የፅንፈኝነት አመለካከት ቀድሞውኑ ከነበረ እንዲህ አይነቱ ተግባር ቢያባብሰው እንጂ አያጠፋውም፣ ካልነበረም አዲስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው።

የሃይማኖት ፅንፈኝነት ችግሮች እና ሁኔታዎች የሚፈጥሩት እንጂ በተፈጥሮ የሚገኝ ገፀ በረከት አይደለም፡፡

ኒቃብን ማሶለቅ ማለት ፅንፈኝነትን ማሶገድ ማለት መስሎ ከታየ ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡ የሃይማኖት ፅንፈኝነት አዕምሮ ውስጥ ያለ አስተሳሰብ እንጂ ውጫዊ አካል ላይ የሚደረገ ልብስ አይደለም፡፡

የሃይማኖት ፅንፈኝነትን የምንከላከለው ሁሉም ሃይማኖታዊ ተግባራትን አውቆ በደንብ መተግበር ሲችል እንጂ ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎችን እንዳይፈፀሙ በመከልከል አይደለም፡፡

ፅንፈኝነት የአስተሳሰብ ጠባብነት የሚፈጥረው ችግር እንጂ ሃይማኖት በራሱ የሚፈጥረው አይደለም፡፡

የሃይማኖታዊ ፅንፈኝነቶችን ማከም እና መታገል የሚቻለው በደልን እና ጭቆናን በቀዳሚነት በማስወገድ፣ ማህበረሰቡ ሚዛናዊ እና ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዲኖረው ነፃነቱን በጠበቀ መልኩ በማስተማር፣እኩልነትን እና ፍትህን በማስፈን፣ ዜጎች የፈለጉትን እምነት ያለማንም አስገዳጅነት በራሳቸው ፈቃድ እንዲከተሉ እና ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎቻቸውን በነፃነት መተገበር ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

ጥንፈኝነትን በሃይማኖት ሽፋንም ይሁን በፖለቲካ ሽፋን ይፈፀም እምነታችን ስለሚያዘን እንቃወማለን፡፡ በስልጤ ዞን እና በሌሎች ቦታዎች ኒቃብን በግዳጅ የማሶለቅ የጽንፈኝነት ተግባር ፅንፈኝነትን ለመዋጋት ሳይሆን ኢስላምን ለማዳከም እና ለማጥፋት የሚደረግ የፅንፈኝነት ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም ይህ የፅንፈኝነት ተግባር ይቆም ዘንድ አጥብቀን እንቃወማለን

በስልጤ ዞን እና በሌሎች ቦታዎች ኒቃብን በግዳጅ የማሶለቅ የጽንፈኝነት ተግባር ሊቆም ይገባል!!

በዲናችን ላይ የሚመጣውን ፈተና ሁሉ በፅናት እና በሰብር ችግሩን የምንወጣ አላህ ያድርገን

አሚን

Abu Dawd Osman's photo.