አዲሱ ምደባ ሒልተን አዲስ ሆቴልን ወደ ሦስት ኮከብ ዝቅ አደረገው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዲሱ ምደባ ሒልተን ሆቴልን ወደ ሦስት ኮከብ ዝቅ አደረገው

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ጋር በመተባበር በዘረጋው የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ፕሮግራም መሠረት፣ አንጋፋው ሒልተን አዲስ ሆቴል ወደ ሦስት ኮከብነት ደረጃ ዝቅ አለ፡፡ ሚኒስቴሩ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት 68 ሆቴሎች በደረጃ ምደባው ተካተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 28 ሆቴሎች ከደረጃ በታች ወይም ‹‹ዜሮ ኮከብ›› ሲደረጉ፣ ሸራተን አዲስ፣ ራዲሰን ብሉ፣ ካፒታል ሆቴልና ስፓ እንዲሁም ኢልሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለአምስት ኮከብ ደረጃን እንዳገኙ ይፋ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር 27 ሆቴሎች መሠረታዊ የደኅንነት፣ የሳኒቴሽንና የኃይጂን አጠባበቅ ሠርቲፊኬቶችን ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው፣ ከደረጃ ምዘናው ውጪ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡ እንደ ዋቢ ሸበሌና ሐራምቤ ያሉትን ጨምሮ በርካታ ሆቴሎች የደረጃ ውጤት ያላካተታቸው ሆነዋል፡፡