ለሕወሓት ስውር እጆች ታዛዥ ስላልሆንን እየተጠቃን ነው ሲሉ የጉምሩክ ሰራተኞች ይናገራሉ:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተለያዩ አይነት የሙስና ወንጀሎች ሲሰሩ በጉምሩክ እና ገቢዎች መስሪያ ቤትን የሙስና ወንጀል የለም ብሎ ባይካድም ከጥቅማቸው ይልቅ የሕዝብ አደራ አንበላም የሚሉ ሰራተኞች ለሕወሓት ስውር እጆች አንታዘዝም በማለታቸው በሙስና ስም ጥቃት እየደረሰብን ለእስር እየተዳረግን እየተንገላታን ነው ሲሉ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የጠቆሙት ፋይል ይናገራል::የሕወሓት ሃላፊዎች በተሳሰረ ቡድናዊ ስልት በሃገር እና በሕዝብ ላይ እየሰሩ ያሉት ግፍ እና ዘረፋ እየተደጋገመ ከመምጣቱም በላይ በተለያዩ የጉምሩክ ክፍሎች እና የገቢዎች ቢሮ ውስጥ ከፍተኛ የሰነድ ወንጀል ከመፈጸም አልፈው አይን ያወጣ ዘረፋ በማካሄድ ላይ ሲሆኑ ይህንን ድርጊት የማይተባበሩትን ወደ እስር ቤት በማስገባት እንደሚወነጅሉ ታውቋል::

ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የደረሰው ባለ 16 ገጽ አቤቱታ የመንግስት ባለስልጣናት የሚፈጽሙት ወጀል አስቁማችሁ ንጹሃንን መወንጀል እና ማሰር በፈጠራ ክስ በሃስት ምስክር ማጉላላት ካላቆማችሁ ከታሪክ ተጠያቂነት እናንተም ሆናቹ ቤተሰቦቻችሁ አታመልጡም ሲል ይገልጻል::ከውጪ ድርጅቶች በተለይ ከቻይናውያን ጋር በመተባበር በጉምሩክ አከባቢ ከቻይና በባለስልጣናት ዘመዶች በኩል የሚገቡ እቃዎች ካለምንም ከልካይነት በቀጥታ ምንም ሳይቀረጥባቸው እና ሳይታዩ እነደሚወሰዱ ታውቋል::የሕወሓት ከፍተኛ ሹማምንት በዘመዶቻቸው በሚመሩ ጭፍሮቻቸው በቡድን በቡድን በመሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዱም በተለያዩ የድንበር የጉምሩክ ኬላዎች በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የጉምሩክ እና የገቢዎች ቢሮዎች ውስጥ ስውር እጆቻቸውን በማዝለቅ የተለያዩ አስደንጋጭ ዘረፋዎችን ሲያካሂዱ ከተለያዩ ሃገራት የሚገቡ እቃዎች ካለቀረጥ እና ካለደረጃ መዳቢ ምርመራ ተወስደው ለገበያ በመውጣት ትጉሃን ነጋዴዎች ስራ ላይ ከባድ እክል እና ጋሬጣ እየፈጠሩ መሆኑ ተገልጿል::

እንዲሁም የገቢዎች ቢሮዎች ድረስ በመግባት ሰነዶችን በመቀያየር ፎርጂድ ሰነዶችን በማያያዝ ፋይሎችን በማጥፋት በሃገር ላይ ከባድ ክህደት እና ዘረፋ እየተፈጸመ መሆኑ ተገልጿል::ከትግራይ ክልል ከአቶ አባይ ወልዱ ጀምሮ በፌዴራል ሚኒስቴር የስራ አካላት ላይ ጣልቃ በመግባት ስራዎች በዝምድና ፍትህ በገንዘብ እና በትውውቅ እንዲሁም በተለያዩ ስልቶች ከባባድ መንግስታዊ የዘረፋ ሽብር እየተፈጸመ መሆኑ አቤቱታው ያመለክታል::ከዚህ ሁላ የሕወሓቶች ሕገወጥ ድርጊት ጋር አልተባበር ያሉትን በተለያዩ የፈጠራ ክሶች ወደ እስር በመውሰድ እፎይ ብለው ዘረፋውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ ያሉት ባለ አቤቱታዎች ሕገወጥነትን በተከላከልን በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጥቃት እየደረሰብን ነው ሲሉ አማረዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.