ወገን በወረርሽኝ በሽታ እያለቀ ነው:: የድርቁ ሁኔታ ከመባባሱ አልፎ ከንጽህና ጋር የተያያዙ እና ውሃ ወለድ በሽታዎች ተስፋፍተዋል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi – ስካቢስ የተሰኘ ወረርሽኝ በምሥራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ወሎና በዋግ ህምራ ዞኖች በሚገኙ 20 ወረዳዎች ላይ መከሰቱን የተባበርት መንግስታት ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን ከፍተኛ የሰብኣዊ ቀውስ ያስከተለውን የድርቁን ሁኔታ ሽላ በማለት አጣብቂኞቻቸውን ለማላላት ደፋ ቀና የሚሉት ባለስልጣናት በስብሰባ ተጠምደዋል::የሕዝብን ሃሳብ ለመስረቅ እና አቅጣጫ ለማስቀየስ የሚውተረተሩት የአገዛዙ ጭፍሮች ለዜጎች ምንም አይነት ትብብር ሊያደርጉ ፈቃደኛ አይደሉም::
ስካቢስ የተሰኘው ይህ ወረርሽኝ በሽታ በመስፋፋቱ በዋግ/ሕመራ ብቻ ወደ 89 ሺህ ዜጎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል፡፡የችግሩ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የተለያዩዘርፎችን ትብብር የሚጠይቅ እንደሆነ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል ቢነገርም የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ አካላት በፖለቲካ ስብሰባ ስለተጠመዱ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል:: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳለው ከ2015 መግቢያ ጀምሮ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናት በእጥፍ የጨመረ ሲሆን ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ የምግብ ፕሮግራም የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ቁጥር ከየወሩ በ20 በመቶ እየጨመረ መሆኑን ገልጾ በሴፕቴምበር 2015 የተመዘገቡ በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር እና በነሐሴ ወር ከተመዘገቡት ሕፃናት ልዩነት ቢኖርም በአገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ መሆኑ ታውቋል::በሰሜን ኢትዮጵያ ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው እንደሆነ ሲታወቅ በየወሩ በክልሉ ወደ 7000 የሚጠጉ በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ወደ ምግብ ፕሮግራም እንደሚመጡ ተገልጿል::

የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል የገንዘብ ምንጭ በወያኔ መንግስት በኩል ያልተዘጋጀ እና ያሌለ ሲሆን ለተወሰኑ 6% ለሚሆኑ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል እርዳታ ለማድረግ ሲሞከር ከውጪ እህል ለመግዛት የተደረቀ ሙከራም በውጪ ምንዛሬ እጥረት አጣብቂኝ የፈጠር መሆኑ ሲታወቅ የሚፈለገውን የምግብ እርዳታ ፍላጎት ለሟሟላት ለለጋሾች የቀረበ ጥሪ ምላሽ እንዳላገኘ ታውቋል::ለኤርዳታ የሚሆኑ ነገሮች ባለመዘጋጀታቸው እንዲሁም አስፈላጊ እርዳታዎች ባለመኖራቸው ከወያኔ የፖለቲካ ፍጆታ እና ከተቃወሰው ኢኮኖሚ አንጻር ድርቁ ለሚቀጥሉት አመታት ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል የሚሉ ወገኖች የተፈጥሮ ችግር የፈጠረው ድርቅ በቁጥጥር ስር ማዋል እየተቻለ በመዘናጋት ብቻ ሰብኣዊ ቀውሱን ሰው ሰራሽ ስለሆነ ብቻ ድርቁ ማቆሚያ እንዳሌለው እየተነገረ ነው::