ከ200 በላይ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱ ተነገረ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከ200 በላይ ተሳፋሪዎችን ይዞ በሲናይ በረሃ ሲጓዝ የነበረው የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱን የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል።ኤር ባስ ኤ-321 የተሰኘው ይህ አውሮፕላን ከቀይ ባህሩ የሻርማል ሼክ ሪሶርት በመነሳት ወደ ሩሲያ እያቀና ነበር ።
የአውሮፕላኑን መሰወር አስመልክቶ የተለያዩ መላምቶች ሲሰጡ ቆይተው፥ ቢቢሲ በሰበር ዜናው የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግርን ዋቢ አድርጎ አውሮፕላኑ መከስከሱን ይፋ አድርጓል።አውሮፕላኑ 217 መንገደኞችን እና ሰባት የበረራ ሰራተኞችን ይዞ የነበር ሲሆን፥ አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎችም የሩሲያ ቱሪስቶች መሆናቸው ነው የተነገረው።
የግብፅ ባለስልጣናት አውሮፕላኑ ከተነሳ ከ23 ደቂቃ በኋላ ከቆፕሮስ የአየር መቆጣጠሪያ ጋር ሲያደርግ የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስታውሰዋል።ከግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የወጡ መረጃዎችን ጠቅሶ፥ አደጋውን የሚያጣራ ኮሜቴ በካቢኔ ደረጃ መቋቋሙን ደግሞ ዘ ሚረር ነው።