በሃጂ ስነስርአት ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 47 ደርሷል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በሃጂ ስነስርአት ወቅት በተፈጠረ መጨናነቅ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 47 መድረሱን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
ባለፈው መስከረም 13 ቀን 2008 በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በደረሰ አደጋ ከ1ሺህ በላይ የተለያዩ ሀገር የሃይማኖታዊ ስነ ስርአቱ ተሳታፊዎች ህይወታቸውን ባጡበት ወቅት ኢትዮጵያውያን ላይ አደጋ ስለመድረሱ ወዲያው ማወቅ ያልተቻለ ሲሆን ከቀናት በኋላ 2 ኢትዮጵያን ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቦ እንደነበርና ኋላም የሟቾች ቁጥር ወደ 31 ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከትናንት በስቲያ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቁጥሩ 47 መድረሱንና ተጐድተው ሆስፒታል ገብተው ከነበሩት 26 ኢትዮጵያውያን 24 ተሽሏቸው ከሆስፒታል ሲወጡ፣ 2ቱ ተኝተው ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
ለሃጅ ስነስርአት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የነበሩ ከ1ሺህ 100 በላይ አማኞች መመለሳቸውንም ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡ በዘንድሮ የሃጂ ስነስርአት ላይ 10ሺ ኢትዮጵያውያን መሣተፋቸውም ታውቋል፡