ወያኔ/ኢሕአዴግ በውይይት ያምናል ብሎ ማሰብ መርዝ እንደመጠጣት ይቆጠራል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰከን ያለ እና ረጋ ያለው ወዳጅ ይፈልጋል::በፈላ ሰአት ሁሉ በስሜት መነዳት በፕሮፓጋንዳ መደበላለቅ ትልቅ አደጋ ያስከትላል::እኛ የለውጥ ሃይሎች ማለት ከራሳችን እና ከባለፈው ሂደቶቻችን መማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች እንደሆንን እዚህ ደርሰናል::የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ ምርጫውን አሸነፍኩ ባለ ማግስት ተቃዋሚዎችን በምመሰርተው መንግስት ውስጥ ሃሳባቸውን አሳትፋለው ብሎ ሲያቅራራ ነበር::መወያየት መመካከር ልዩነትን አቻችሎ በሃገራዊ አጀንዳ ዙሪያ መስራት ታላቅነት ነው ይህ ግን ወያኔ ጋር የለም ወያኔ መሰሪ ነው እባብ እንደወዳጅ እያጫወተ ከጀርባ የሚያርድህ ነው::ኑ እንወያይ ኑ እንመካከር ብሎ ስንቱን ፓርቲ አክስሟል…ስንቱን አድክሟል…ስንቱን ታጋይ ከጨዋታ ውጪ አድርጓል..ኧረ ስንቱን ?

በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ያሉ እንደ አንዱአለም እና ሃብታሙ ያሉ በሳሎች የዚሁ የእንወያያ ጥሪ ሰለባ ናቸው:;ጥርስ የተነከሰባቸው ወያን በጠራቸው የውይይት መድረኮች ላይ በተናገሩት ሕዝባዊ ጠንካራ ንግግሮቻቸው ነው::ወያኔ በውይይት እና በመመካከር የሚያምን ቢሆን ኖሮ ብርሃኑ ነጋን የሚያክል የስልጣን ጥም ያሌለበት ምሁር እና ለሃገር የሚጠቅሙ ሰዎች (ቢያዋጣም/ባያዋጣም)የትጥቅ ትግል እናደርጋለን አይሉም ነበር:;ወያኔ በውይይት እና በመመካከር ቢያምን ኖሮ ሃሳባቸውን በነጻነት የገለጹ ባለ ብዕር ኢትዮጵያውያንን ካለምንም ማስረጃ ወህኒ አያጉራቸውም ነበር:;ሌላም ምሳሌ አለ በወንድማችን አቡበከር አህመድ የሚመራው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴያችን የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ይዞ ሲነሳ ኑ ተወያዩ እንወያይ ብሎ ባስቀመጣቸው ቢሮ የተያዘው ቃለ ጉባዬ ቀለም ሳይደርቅ ነው ንጹሃኑን አሸባሪ ብሎ የፈረጃቸው:: ሌላም ሌላም ብዙ ማለት ይቻላል::ከአማራጭ ሃይሎች ምክር ቤት ጀምሮ እስከ ራሱ እስከጠራው አይሲስ ሰልፍ ድረስ ወያኔ በዜጎች ላይ መሰሪ ተግባሩን ተግብሯል::

ወያኔ ወይይት ማለት ለሱ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ለማሾፍ እና ለመዝናናት የሚጠቀምባት የፖለቲካ ማጭበርበር እንዲሁም የዋሃንን ለማታለል እና ምእራባውያንን ቀልብ ለመግዛት ብሎም የሚያፍናቸውን እና የማይፈልጋቸውን የፖለቲካ ሰዎች ለመለየት ይጠቀምበታል::በሃገር ቤት የሚገኙ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የወያኔን መሰሪ ፖለቲካ ጠንቅቀው ያውቁታል::ወያኔ ምንም የሚፈይደው ነገር እንደሌለም አሳምረው ያውቁታል::ወያኔ ኑና ላወያያቹ ያለው ላለፉት አስርተ አመታት ተወቅጦ ተወቅጦ ያልተሳካውን እና ሲንከባለል ለዛሬ የደረሰውን የከሰረውን የትራንስፎርሜሽን እና እድገት እቅድ እንጂ በሃገሪቱ ስላሉት ችግሮች አይደለም::ይህ ድህነትን እቀርፍበታለው ያለው እቅዱ እንኳን ድህነትን ሊቀርፍበት ይቅርና የደሃ ደሃ በመፍጠር መጪ ትውልዶች የማይከፍሉትን እዳ በመበደር ሃገሪቷን ለብሄራዊ ውርደት ሕዝብንም ለኑሮ ዝቅጠት ዳርጎታል::

ወያኔ ስለታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ስለ ሕሊና እስረኞች እና ስለ ሞተው ፍትህ በሙስና ተዘፍቆ ሕዝብን ስለሚያጉላላው አስተዳደር ስለ ኑሮው ውድነት ችግር አሊያም ስለ ሃገሪቱ አጠቃላይ መሰረታዊ ጉዳዮች እንወያይ ብሎ ተቃዋሚዎችን አልጠራም::ይህ ቢሆን ደግ ነበር:;ውይይቱን የጠራው አሁንም ልብ ማለት ያለብን ጉዳይ ቢኖር ስለተሽመደመደው እና ለሃገር ኪሳራ ስለሆነው የትራንስፎርሜሽን እቅድ እንወያይ ስላለ ይህ ደግሞ ምንም ፋይዳ የለውም::ወያኔ ስለታሰሩ ዜጎች ቅንጣት ያህል ሰብኣዊነት እና ርሕራሄ አይሰማውም:: ከስራ ከቀየ ስለተፈናቀሉ ይሁን ስለተሰደዱ ዜጎች ምንም ደንታ የለውም::ወያኔ ሲፈጥረው ቻሌንጅ መሆን የማይችል የማፊያ ቡድን ነው::እያወቅን እየተረዳን ካለፈው የማንማር ጨቅላ እና የዋህ ፖለቲከኞች ከሆንን በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ያስቸግራል:: ጠንካራ እና የተቀናቃኝን የፖለቲካ ስትራቴጂ ለማክሸፍ የለውጥ ሃይሎች እርስ በእርስ መመካከር ያስፈልጋቸዋል::ከወያኔ ጋር ግን እደራደራለሁ እወያያለሁ አሊያም እመካከራለሁ ማለት መርዝ እንደመጠጣት ይቆጠራል::ተለጣፊ እና ታማኝ ተቃዋሚዎቹ ይሰብሰቡለት::አሁንም ንቃት ያስፈልገናል::እንንቃ!!!

Minilik Salsawi's photo.