በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስት ከምዝገባ ከትምህርት ከምግብ ማገድ አዲሱ የወያኔ ማስፈራሪያ ሆኗል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi – የወያኔው መንግስት በራስ አለመተማመኑ እንደቀጠለ ነው::ከምርጫው በፊት በየትምህርት ተቋማቱ በየመስሪያ ቤቱ በስልጠና ስም ከፍተኛ የሃገር እና ሕዝብ ገንዘብ አባክኖ በሕዝብ ሮሮ ናላው ዞሮ ማሾፊያ የሆነው እና በአጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ወያኔ ድህነትን አጠፋለሁ ልማት አለማለውሁ በሚ ሰበብ ከፍተኛ የሆነ እዳ በሃገሪቱ እና በመጪው ትውልድ ላይ በመጫን ህዝብን ለባሰ ድህነት በመዳረግ ላይ አልበቃ ብሎት ይህን ሰሞን ደግሞ ስልጠና ካልሰጠኋቹህ ምዝገባ የለም ምግብ የለም ትምህርት አትማሩም በማለት ተማሪዎችን ሲያጉላላ መምህራንን ደሞ ደሞዛቸውን በመቁረጥ አዲስ ሕዝብን የማሸማቀቂያ እና ማስፈራሪያ ስልት ጀምሯል::

በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በማስታወቂያ ቦርድ እና በበራሪ ወረቀትነት እየታደሉ የሚገኙት ወረቀቶች እንደሚያመለክቱት ማንኛውን ተማሪ ይሁን መምህር በወያኔ ስልጠና ላይ ካልተገኘ እንደሚታገድ ይገልጻል::በረሃብ ይቀጣል::አስፈላጊ ነገር አያገኝም ይባረራል::ተማሪዎችን ይሁን መምህራን ምንም አይነት ፊት ያልሰጡት ይህ ስልጠና እንደባለፈው ስልጣና ውጤት አልባ እና መቀለጃ እንደሚሆን የሚገልጹ ተማሪዎች የሃገር ሃብት ከማባከን ውጪ ምንም ፋይዳ የለውም በማለት ላይ ይገኛሉ::አንድን ሕዝብ እመራለሁ ብሎ ነጋጠባ ከሚገዘት አምባገነ የሃሰት ስርኣት የሚጠበቅ ቢሆንም ተማሪዎች ይሁኑ መምህራን መብቶቻቸውን ለማስከበር ታጥቀው መነሳት ይጠበቅባቸዋል::

Minilik Salsawi's photo.