የኢትዮጵያን ታሪክ የ100 አመት ታሪክ ሲያስመስሉት መታዘብ ከጀመርን ድፍን ሰላሳ አመት ሊሞላን ነው። (ኤርሚያስ ቶኩማ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል ለዚህም ማስረጃው የኢትዮጵያ ታሪክ ትርጓሜን ተመልከቱት የሕወሓት ሰዎች ከጫካ ተስማምተውበት በመጡት ግንዛቤ የኢትዮጵያን ታሪክ መተርጐም ብሎም ለሌሎች ማስተማር ይፈልጋሉ የኦነግ መሪዎችም የሕወሐት አለቆቻቸው ያስተማሯቸውን እና የነገሯቸውን እንደሀይማኖታዊ ቃል ይዘውት ራሳቸውን የታሪክ ሊቅ ብሎም የኢትዮጵያን ታሪክ የ100 አመት ታሪክ ሲያስመስሉት መታዘብ ከጀመርን ድፍን ሰላሳ አመት ሊሞላን ነው።
ህወሐት ወ ኦነጎች እንደሚያወሩት ሳይሆን አንዱ ጎሣ ሌላውን ጎሣ የበታች አድርጐ እንደህዝብ ይመለከትበት የነበረበትን ዘመን በስክሪፕት ቀርቶ በአፈታሪክ ማግኘት እራሱ ከባድ ነው በተለይም አማራ የተሰኘው ጎሣ ፈርዶበት እንደጨቋኝ እንዲታይ የማይደረግ ጥረት የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። ብዙዎቹ የሕወሐት ወ ኦነግ ታሪክ ጸሐፊዎች የጥንት የኢትዮጵያ መሪዎች በተለይም ከ1855 በኋላ በትረ ሥልጣኑን የያዙት የኢትዮጵያ መሪዎች ለሌላው የሐገሪቱ ህዝብ ንቀትና ጥላቻ እንደነበራቸው ይገልፃሉ ሆኖም አንድም ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም የነበሩን ነገሥታቶች ለአማራ ጎሣ ብቻ የቆሙ እንደነበሩም ያወሳሉ ሆኖም ይህ ስህተት ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ይሄኛው ጎሣ የተሻለ እና ወርቅ ነው የሚል መሪ የመጣው በ1983 ነው ሁላችንም እንደምናስታውሰው መለስ ዜናዊ የተሰኘው የሕወሐት መሪ ከመሞቱ በርካታ አመታት በፊት በ1984 አ.ም አካባቢ የእርሱ የዘር ግንድ የተመዘዘበትን የትግራይ ጎሣ የተመረጠ ወርቅ ዘር እንደሆነ በአደባባይ ገለፀ (በወቅቱ ያደረገውን ንግግር ከዚህ ቀደም እዚህ ፌስቡክ ላይ ስለለጠፍኩት መመልከት ትችላላችሁ) አስቡት ወርቅ የሆነ ዘር ካለ ብር፣ ነሐስ ወይም ድንጋይ የሆነ ዘር አለ ማለት ነው ለሕወሐት ታሪክ ፀሐፊዎች ነሐስ ወይም ድንጋይ የሆነው ዘር የቱ እንደሆነ መገመት ብዙም አዳጋች አይደለም።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደመለስ ዜናዊ ይህ ዘር ወርቅ ነው ያኛው ድንጋይ ነው ያለ መሪ እንኳን በአፈታሪክ በማግኔት ቢፈለግ አይገኝም ሆኖም በአንድ ጎሣ ውስጥ ካሉ ሕዝቦች መካከል የኔ ጎሣ የተሻለ ነው ብሎ የሚያስብ የለም ማለት አይችልም ይህ የነበረ ያለና የሚኖር የግለሰቦች አመለካከት ነው። እንደዚህ ያሉ የሚሰነፍጡ አመለካከቶች ከግለሰብ አልፈው ወደሃገር መሪዎች ከመጡ የሐገር እና የህዝብ መበታተንን የሚፈጥሩ አደገኛ አመለካከቶች ናቸው በ1933 በናዚ ፓርቲ አማካኝነት ወደሥልጣን የመጣው አዶልፍ ሂትለር የታላቋን ጀርመን ኤምፓየር በመላ አውሮጳ በምእራብ ኤስያ እና በሰሜን አፍሪቃ ለመመስረት ሲያስብ የጀርመንን ህዝብ ያነሳሳው የነበረው ታላቅ ህዝብ እንደነበረ እየነገረ ነው ሆኖም አልጠቀመውም ጀርመንን ለበርካታ አመታት የገነጣጠላት ሲሆን እርሱም ቢሆን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።
ሁላችንም ማመን ያለብን ነገር የሕወሐት እና የኦነግ አመራሮች አሁን ከሚናገሩት የኢትዮጵያ ታሪክ በተቃራኒው ስለኢትዮጵያ የ5000 አመት እድሜ ቢናገሩ ከፓርቲያቸው እና ከደጋፊዎቻቸው ጥርስ ውስጥ እንፈሚገቡ ያውቁታል አስቡት ስዩም መስፍን ተነስቶ የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 አመት ሳይሆን የ5000 አመት ነው ብሎ ቢያወራ በሕወሐት ሰዎች የሚደርስበትን ዛቻ እና ቅጣት፤ በዛው ልክ የኦነጉ አፈቀላጤ ጃዋር መሐመድ አጤ ምንሊክ ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ የታገሉ ከፋሺሽት ባርነት ያወጡን ታላቅ መሪያችን ነበሩ ቢል በምን ፍጥነት የኦነግ ሰዎች አንገቱን በሜንጫ እንደሚቀነጥሱት አስቡት።
የሕወሐት ወ ኦነግ አፈቀላጤዎች የኢትዮጵያን ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ የሚያስመስሉት ከእውቀት በመራቃቸው ብቻ ሳይሆን ሆዳቸውን የሚሞሉት ታሪክን አንሻፈው ሲናገሩ ብቻ እንደሆነ ስለሚያውቁት ጭምር ነው።
የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ትልቁ ችግር ሁለትና ሶስት የቅኝ ገዢዎች ታሪክ ፀሐፊዎች የፃፉትን መጽሐፍ አንብበው በድፍረት የኢትዮጵያ ታሪክን ለመተንተን የሚነሱ ድፋሮች መኖራቸው ነው ይላሉ። እውነት ነው ጫካ የነበረውም እራሱን እንደታሪክ ተርጓሚ ይመለከታል የእርሻ መምህሩ ታሪክ ማስተማር ይፈልጋል አንድ ተራ ካድሬ የታሪክ ምሁራንን ሰብስቦ ስለታሪክ ያሰለጥናል።
እንዲህ ሆኖ እንዴት እንደምንቀጥል ሳስበው ያስፈራኛል ሆኖም ሁላችንም ማመን ያለብን እንኳን ተራዎቹ የሕወሐት እና የኦነግ ሰዎች ፋሺሽት ኢጣሊያ እንኳን ኢትዮጵያን መበተን አልቻለም።
#ኤርሚያስ_ቶኩማ