በትግራይ የተደበቀው ገዳይ በሽታ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በትግራይ መንስኤው በውል ባልታወቀ የጉበት በሽታ ብዙዎች ለሞትና ለአልጋ ቁራኛነት እየተዳረጉ እንደሚገኙ በምስል የተደገፉ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡በ1997 በሰሜናዊ ትግራይ በታችኛው ቆራሮ ቀላቕል በተባለ ወረዳ መከሰቱ የሚነገርለት በሽታው ዛና በተባለ አካባቢ በሚገኙ 20 የወረዳው ጣብያዎች 430 የሚደርሱ ሰዎችን በማጥቃት 101 ያህሉን ለሞት መዳረጉ ተወስቷል፡፡
በሽታው ወደ ጎረቤት ወረዳዎች በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ የሚጠቁሙት የአካባቢው ምንጮች በሽታው በታየባቸው ወረዳዎች የክልሉ መንግስት የጤና ባለሞያዎች የተሳሳተ መረጃ በማውጣት በሽታው በጊዜ በቂ ትኩረት እንዳያገኝ ማድረጋቸውን የመረጃው ምንጮች ይወቅሳሉ፡፡
ለአብነት ያህል ዛና ወረዳ በምትገኝ አንዲት አነስተኛ ጣቢያ 1655 ሰዎች በበሽታው ተይዘው ለህመም መዳረጋቸውን የሚጠቅሱት ምንጮች አብዛኛዎቹ ሆዳቸው ተነፍቶ በቂ ህክምና ሳያገኙ እስከወዲያኛው በማሸለብ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ምንነቱ ያልታወቀ የጉበት በሽታ (Unknown liver diseases ULD) ህይወት ካላቸው ነገሮች ከሚፈጠር ፕሮቲን የሚከሰት በአብዛኛው ከእንስሳት የሚመነጭ መሆኑን የሚጠቅሱት የዘርፉ ባለሞያዎች ጉበትን በመመረዝ ለሞት ይዳርጋል ይላሉ፡፡
