• ehln-2

በተለያዩ የብር ኖቶች ላይ ግራፊቲ ጽሁፎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ታውቋል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)

September 28, 2015 – ምኒሊክ ሳልሳዊ — 1 Comment ↓


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።


በተለያዩ የብር ኖቶች ላይ ግራፊቲ ጽሁፎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ታውቋል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)ላለፉት አመታቶች በተለያየ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን ለማስከበር የሚታገሉት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በገዛ አገራቸው በወያኔ አገዛዝ የሚደርስባቸውን ግፍ እና መከራ እስር እንግልት እና ግድያ በመቃወም ለሃይማኖት ነጻነት የሚያደርጉትን ትግል በመቀጠል በዚህ ወር ከወጣው መርሃ ግብር አንዱ የሆነውን ‹‹የወረቀት ብር ግራፊቲ›› (Money Graffiti) በተለያዩ የብር ኖቶች ላይ ከተለያዩ መልእክቶች ጋር በማስፈር መልእክታቸውን በማስተላለፍ ላይ መሆናቸውን እና ይህም ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል::

ይህ የግራፊቲ ጽሁፎችን በወረቀት ብር ላይ አስፍሮ ለስርጭት የማብቃት ስራ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ስማቸው ከሚጠቀሱ የትግል ስልቶች አንዱ ነው ፡፡ የሚለው የትግሉ መሪ ድምጻችን ይሰማ ባወጣው መርሃግብር መሰረት በስፋት እየተሰራበት ሲሆን ይህ የወረቀት ብር ግራፊቲ ትግሉና የትግሉ ዓላማ የወረቀት ብር በሚደርስባቸው የአገሪቱ ክልሎችና ጉራንጉሮች ጭምር ያለምንም ከልካይ እንዲደርስ እድል ይፈጥራልናል::

ትግላችን በአላህ ፍቃድ እስከ ድል ደጃፎች ይቀጥላል!በሚል ጽናት እና ከፍተኛ የሆነ ተነሳሽነት ለመብት እና ለነጻነት የሚደረጉ ትግሎች ውጤት እያፈሩ በሂደት መምጣታቸው ሲታወቅ አዲስ አበባን እና አዳማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገራችን ግዛቶች በስፋት የወረቀት ገንዘብ ግራፊቲ ጽሁፎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ጉዳዩን እየተከታተሉ የሚገኙ የሚዲያ ሰዎች ተናግረዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

    © 2025 Amharic News & Opinion        
    ↑