የድምጻችን ይሰማ ‹‹የወረቀት ብር ግራፊቲ›› (Money Grafitti)ተግባራዊ ስራ ተጀመረ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ድምፃችን ይሰማ
.
ሁላችንም ለስኬታማነቱ በብር ላይ በመፃፍ እንረባረብ!
.
ባለፉት ጥቂት የትግል አመታት ከህዝብ ወደ ህዝብ በሚሰነዘሩ የተለያዩ ሐሳቦች በመገፋት
የቀጠለው ሰላማዊ ትግላችን በሂደት ጥቂት የማይባሉ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን ተጠቅሞ ድምጹን ለማሰማትና የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችም እንዲቆሙ ለማስደረግ
ሲጥር ቆይቷል፡፡

.
.
በእነዚህ ሂደቶችም ሰፊ ልምድ ማዳበር ተችሏል፡፡ ስንጠቀምባቸው ከነበሩ የትግል ስልቶች አንዱ ደግሞ ግራፊቲን (የግድግዳ ላይ ጽሁፍን) በመጠቀም የትግሉን መልእክት ለመላው ህዝብ ማስተላለፍ ነበር፡፡
.
.
መንግስት በበኩሉ ጥያቄ ያስነሱበትን በደሎች በማስቆም ፈንታ የግራፊቲ ጽሁፎችን
በተጻፉበት አጋጣሚ ሁሉ እየተከታተለ ለማጥፋት ሲጥር የቆየ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ፖሊሶችን ጭምር ቀለም እያሸከመ የግራፊቲ ጽሁፎችን በአደባባይ ሲያስጠፋ ቆይቷል፡፡
.
.
ይኸው የግድግዳ ግራፊቲ ስራ አሁንም አጋጣሚ በተገኘ እና አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ
እየተሰራ የሚቀጥል መሆኑ እንዳለ ሆኖ አሁን ደግሞ ተከታትሎ ለማጥፋት አስቸጋሪ
የሆነውን ‹‹የወረቀት ብር ግራፊቲ›› (Money Grafitti) በተለያዩ የብር ኖቶች ላይ. ከተለያዩ መልእክቶች ጋር በማስፈር መልእክታችንን የማስተላለፍ ስራ የምንሰራ ይሆናል፡፡

ምሳሌ ከታች በምስል እንዲካተት ተደርጓል፡፡ ይህ የግራፊቲ ጽሁፎችን በወረቀት ብር ላይ
አስፍሮ ለስርጭት የማብቃት ስራ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ስማቸው ከሚጠቀሱ የትግል
ስልቶች አንዱ ሲሆን የራሱ የሆኑ ጥቅሞችም አሉት፡፡ የሚከተሉትን መጥቀስ እንችላለን፡-
.
.
1/ ትግሉና የትግሉ ዓላማ የወረቀት ብር በሚደርስባቸው የአገሪቱ ክልሎችና ጉራንጉሮች ጭምር ያለምንም ከልካይ እንዲደርስ እድል ይፈጥራል፤

2/ ተሳታፊውን በምንም መልኩ ለጥቃት የማያጋልጥና በየትኛውም ቦታ በቀላሉ መከናወን የሚችል የተቃውሞ ስልት ነው፤

3/ መንግስት እንደግድግዳ ላይ ጽሁፎች ተከታትሎ ሊያጠፋው የሚችልበት መንገድ
የለም፤

4/ በቀላሉ ከአንዱ ወደሌላው የመዛመት እና ለመንግስት አካላትም ጠንካራ መልእክት
የማስታላለፍ ሐይል አለው፤ በመሆኑም ሁላችንም በነፍስ ወከፍ በእጃችን ባሉ የብር ኖቶች ላይ በብእር (እስክሪብቶ) ወይም በማርከር አዲሱን የትግላችንን ምልክት (መጀመሪያ ክብ በመሳል ቀጥሎም በክቡ
ውስጥ 1 ቁጥርን በመጻፍ) በማስፈርና ከቻልንም ተጨማሪ መልእክቶችን በማካተት
ዘመቻውን መጀመር ይኖርብናል፡፡
.
.
በተለይም በቤተሰብ ደረጃ እያንዳንዱ ቤተሰብ ባሉት ልጆችና የቤተሰብ አባላት ልክ (ለምሳሌ አምስት አባላት ያሉት ቤተሰብ አምስት የብር ኖቶች ላይ በመጻፍ) መርሃ ግብሩን መተግበር አስፈላጊና ለስኬቱ ወሳኝ እርምጃ ይሆናል፡፡

በውጭ አገራት የምትኖሩም እንዲሁ ለቤተሰቦቻችሁ በመደወል በስማችሁ የብር ኖቶች ላይ ግራፊቲ እንዲጻፍላችሁ በማድረግ መሳተፍ ይጠበቅባችኋል፡፡

ሁላችንም ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነት የምንችለውን አስተዋጽኦ እናድርግ!!!

ብሄራዊ ጭቆናን አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!
.

ጭቆናው ይብቃ አህመድ's photo.