ይድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች – እየተበዘበዛቹ ዝምታው እስከመቼ ነው?‪ (ምኒሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi – የአለም የነዳጅ ዋጋ ወርዶ አንድ ሊትር በስምንት ብር ጨርሶ ለችርቻሮ ቢቀርብም አገዛዙ በእጥፍ እየሸጠ በመዝረፍ ላይ ነው::በኢትዮጵያ ውስጥ ከታክሲ ስራ ጀምሮ እስከ አገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት የምትሰጡ ዜጎች በላያችሁ ላይ የሚሰራውን ግፍ እና ብዝበዛ ከላያችሁ ላይ የምታራግፉት በተለያዩ መንገዶች በነዳጅ በግብር በትራፊክ ፖሊስ የምትዘረፉትን ንጹህ ገንዘባችሁን የማዳን የራሳችሁን ነጻነት የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባችሁ ስለዚህ ይህ ዝምታቹ እስከመቼ ነው?የሕወሓት/ኢሕኣዴግ አገዛዝ እንደ ጀርባ ቅማል ከቆዳቹ ተጣብቆ ደማችሁን እየመጠጠ ስለሆነ በጋራ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ትልቁን ታሪካዊ ድርሻችሁን መወጣት ሲገባቹ የአለም የነዳጅ ዋጋ ከግማሽ በታች በቀነሰበት በዚህ ወቅት አገዛዙ ግን በርካሽ የሚያመጣውን ነዳጅ በእጥፍ በመሸጥ እየበዘበዛቹ መሆኑን አይናችሁን ገልጣኑ ተመልከቱ::

በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የተባለው የኢኮኖሚ ስላቅ የነዳጅ ዋጋ መውረዱ ነው::የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ባለፈው አመት ከነበረው በግማሽ ወደ ሃምሳ ዶላር ወርዷል::ካሁን በኋላ የነዳጅ ዋጋ እንደማይጨምር የሚያሳዩ

ምልክቶች ተከስተዋል::የኢኮኖሚ ችግሮች አለምን እየናጡ ባለበት በዚህ ወቅት የአለም የመገናኛ ብዙሃን እንደሚተነትኑት የኢኮኖሚው መንገዳገድ የነዳጅ ፍጆታ ስለሚቀንስ ይህንን ደግሞ የሚጠቁም ጉዳይ በቻይና ላይ መከሰቱን እና ይነዳጅ ዋጋውን እንዲወርድ እንዳደረገው ጠቁመዋል በአሜሪካ እየተስፋፋ የመጣው ፍራንኪንግ የተሰኘ አዲሱ ቴክኖሎጂ የነዳጅ ምርትን እንዲጨምር አድርጎታል::በተጨማሪም የኦፔክ አባል አገራት የነዳጅ ምርትን የመቀነስ ፍላጉት እንደሌላቸው እየተናገሩ መሆኑ አብዛኛዎቹ የአለም ሃገራት ቻይናን ጨምሮ በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ሲሆኑ ኢኮኖሚያቸው መነቃቃት ባለማሳየቱ የነዳጅ ፎጆታቸው ቀንሷል::ይህ ደግሞ እንደሚያሳየው የኢኮኖሚ እንቅፋቶች ሲበዙ ይነዳጅ ፍላጎት መቀነስን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ይባስ ወደ ሃያ ዶላር እንዳይወርድ ግምቶች እየተሰጡ ነው::

በኢትዮጵያስ ? የአለም የነዳጅ ዋጋ መውረዱን አስታኮ የወያኔው አገዛዝ የተጣራ ነዳጅ ለማስገባት የሚከፍለው በአርባ አምስት ፐርሰንት እንደቀነሰ የብሄራዊ ባንክ ሪፖርቶችና መረጃዎች በግልጽ አስቀምጠዋል::ባለፈው አመት ከ2006 የነዳጅ ዋጋ አንጻር ሲታይ የ266 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ እንደነበረው እና የተጣራ ነዳጅ ለማስገባት 317 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም የሃገር ቤት የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ግን ባለበት ተቀምጦ አገዛዙ በብዝበዛ ላይ እንዲሰማራ በር ከፍቶለታል::አሁን ያለውን ሂደት ይዘን የምንጓዝ ከሆነ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን ቢቻልም በነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ግን ምንም አይነት ቅናሽ ባለማሳየቱ እንደማያሳይም የአገዛዙ ሂደት ስለሚጠቁም የትራንስፖርት አገልግሎት ለሕዝቡ የሚሰጡ ባለተሽከርካሪዎች ከባድ የሆነ ብዝበዛ ይደረግባቸዋል::

የአለም የነዳጅ ዋጋ የወረደ ሲሆን አንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋውን ጨርሶ ለችርቻሮ የሚደርሰው ስምንት ብር ነው::አገዛዙ ግን እስከሁን አንድ ሌትር በ17 ብር ከ90 ይቸረችራል::አገዛዙ ከነዳጅ የሚያገኘው ትርፍ፣ ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ ነው።ይህ ደግሞ ከእጥፍ በላይ በማትረፍ ሕብረተሰቡን በመበዝበዝ ይደሃ ደሃ መፍጠር መሆኑን አገዛዙ እየሰራ ያለው ዘረፋ ሲያመለክት ተጎጂው ሕዝብ ግን ዝምታው እስከመች ነው?የፖለቲካው ጫና የፈጠረው

የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ አልመረጋጋቱ ሕዝብ ነጻነቱን ብቻ ሳይሆን ሃብቱንም እያጣ ነው::ይህ በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በተለይ በባለታክሲዎች ሊታሰብበት ይገባል::

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች እና የትራንስፖት አገልግሎት ሰጪዎች የምትዘረፉት በዚህ ብቻ ሳይሆን በትራፊክ ፖሊሶች እና በአገዛዙ የግብር ስራዎች ከፍተኛ የሆነ አደጋ ውስጥ መሆናችሁን አትዘንጉት::ከነፖሊስ ዩኒፎርሙ ቁርጥ እና ቢራ ይዞ በየግሮሰሪው የሚሰየመው ትራፊክ አይን ያወጣ ጉቦ በመቀበል እምቢ ያለውን በማንገላታት በማሰቃየት ህገወጥ ተግባር እየፈጸመባቹ ሲሆን የአገዛዙ የግብር መስሪያ ቤቶችን በልታቸ እንዳታድሩ ከፍተኛ የሆነ ደባ እየተፈጸመባችሁ ሰራታቹ እንዳትኖሩ እንድታማርሩ እየተደረገ መሆኑን አውቃቹ ራሳችሁን ነጻ ለማውጣት አስቸኳይ ርምጃ ልትወስዱ ይገባል:;የአገዛዙን እኩይ ስራዎች ብመቃወም ከስራ ማቆም አድማ ጀምሮ እስከ ህዝብ ማስተባበር ድረስ በመስራት የዜግነት ድርሻችሁን በመወጣት በጋራ ነጻነታችንን እናረጋግጥ ዘራፊዎችን እናውድም::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬