በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የትህዴን ጦር በመሪው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ገባ:: ወያኔ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Mola Asgedom and his troops arrive in Sudan

በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የትህዴን ጦር በመሪው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ገባ:: #Ethiopia ወያኔ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የትህዴን ጦር ክፋይ ትናንት ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ገባ

ከ700 በላይ እንደሚሆኑ የተገመተው የደህሚት ጦር ከነ ሙሉ ትጥቁ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በሁመራ እና በመተማ አድርጎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መምጣቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች ተናግረዋል።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ራሱን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በማለት የሚጠራው እና በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጦር ክፋይ ትናንት ወደ ሀገሩ ገባ።

ጦሩ የንቅናቄው መሪ በሆነው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው።

ቁጥራቸው ከ700 በላይ እንደሚሆኑ የተገመተው የደህሚት ጦር ከነ ሙሉ ትጥቁ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በሁመራ እና በመተማ አድርጎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መምጣቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች ተናግረዋል።

ጦሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በመንገድ ላይ ትንኮሳ ሊፈጥሩበት ጥረት ያደረጉ የሻዕቢያ ሀይሎችን እየደመሰሰ ነው ወደ እናት ሀገሩ የገባው።

ጦሩ በሻዕቢያ እና ግንቦት 7 አስተባባሪነት በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ አደጋዎችን ለማድረስ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግስት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት