• ehln-2

ድምፃችን ይሰማ አዲስ የትግል መለያ አርማ (Struggle Logo) ይፋ አደረገ::

September 8, 2015 – ምኒሊክ ሳልሳዊ — 3 Comments ↓


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።


Minilik Salsawi ድምፃችን ይሰማ በዛሬው እለት ቀጣዩን የሕዝበ ሙስሊሙ የሰላማዊ ትግል አርማ ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት የሰላማዊ ትግላችን አርማ በአካል እንቅስቃሴ ሲገለጽ የጠቋሚ ጣት ሲሆን በጽሑፍ፣ በግራፊክስ እና በግራፊቲ ሲሆን ደግሞ በክብ ቀለበት ውስጥ የሚቀመጥ 1 ቁጥር መሆኑን ገልጿል::ድምፃችን ይሰማ በይፋዊው መግለጫ እንዳለው ጠቋሚ ጣት ቢላል በሃይማኖቱ ሲጨቆን ጽናቱን የገለጸባት የ‹‹አሃዱን አሃድ›› መፈክር ተምሳሌት እንደመሆኗ እኛም በዚችው የ‹‹አሃዱን አሃድ›› ምልክት እንደህዝብ የሚደርስብንን ጫና ለመቋቋም ቁርጠኛ መሆናችንን እናሳይባታለን!ብሏል::

ጠቋሚ ጣት ሃይማኖታችን ላይ የሚሰነዘርን ህገወጥ ጥቃት ለመከላከል በገባንበት ትግል ያሳየነው አንድነትታችን ከምንም በላይ የጥንካሬያችን ምንጭ ሆኖ መቆየቱን ትመሰክራለች!ያለው ድምጻችን ይሰማ ጠቋሚ ጣት እስካሁን በነበረው ትግላችን ተቃውሟችንን ስንገልጽባቸው ከነበሩ መንገዶች አንዷ ናት!ሲል አስታውሶ እንደሚታወቀው መለያ ምልክት (አርማ – ሎጎ) ታጋዮች አንድን ትግል ለመወከል እና በሩቁ ለመግባባት፣ የትግላቸውን ዓላማም ለሌሎች ግልጽ ለማድረግ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡ በየትኛውም የሕዝብ ትግል ውስጥ የጋራ አርማ መኖሩ ልቦችን ከሩቁ ያግባባል፡፡ ለጋራ የተሰለፉለት ዓላማ በብዙሃን መካከል የተንሰራፋ የጋራ ቋንቋ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ያውጃል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎችም ትግሉን ወክሎ ለመግለጽ አመቺ መንገድን ይፈጥራል፡፡ ሲል አስታውቋል::

ይህንን የአንድ ጣት ምልክት መጠቀም የምንችለው በአካል እንቅስቃሴ ብቻ እንደመሆኑ መጠን በጽሁፍና በግራፊክስ፣ እንዲሁም በግራፊቲ ስራዎች ወቅት የበለጠ ቀላል ለማድረግ የቁጥሩን ምልክት እንጠቀማለን፡፡ ለዚህም ሲባል ነው ለጽሁፍ እና ግራፊክስ ስራዎች ተመሳሳይ መልእክት የሚያስተላልፈው በቀለበት ውስጥ ያለ የአንድ ቁጥር ምልክት የተመረጠው፡፡ ሁለቱም ምልክቶች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሲሆኑ የሚወክሉትም ተመሳሳይ ሃሳቦችን ነው፡፡ በማለት ብመግለጫው አሳስቧል::

ለበለጠ መረጃ https://www.facebook.com/DimtsachinYisema/photos/a.325745250810171.103256.324725940912102/1026967464021276/?type=1&theater


    © 2025 Amharic News & Opinion        
    ↑