በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የሚደርሰው ግፍ አንደቀጠለ ነው። በጋምቤላ የወያኔ ታጣቂዎች ዘረፋ ሲቀጥል በደደር ቆቦ ኣንድ የወያኔ ባለስልጣን ተገደለ። (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የሚደርሰው ግፍ አንደቀጠለ ነው። … በጋምቤላ የወያኔ ታጣቂዎች ዘረፋ ሲቀጥል በደደር ቆቦ ኣንድ የወያኔ ባለስልጣን ተገደለ። …
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) …. የጦርነት ቀጠና በሆነው በምስራቅ ኢትዮጵያ ሰፍሮ የሚገኘው እና ጄነራል ኣብርሃ የሚመራው የደቡብ ምስራቅ እዝ ክፍለጦር ውስጥ በመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ላይ የሚደርሰው ግፍ የጨመረ ሲሆን በየቀኑ ሶስት አና ኣራት የሰራዊቱ ኣባላት በጥርጣሬ ብቻ አየተጠሩ ምርመራ እንደሚደረግባቸው እንዲሁም ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጣቸው ብምርመራው ላይ የተሰማሩ ወታደራዊ ደህንነቶች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል። የመከላከያ ሰራዊት ኣባላቱ ህገመንግስቱን አና ወታደራዊ ህጎችን ጥሳቹሃል በሚል ሰበብ ተጠርተው ምርመራው ግን ሌላ አንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ምርመራው የሚያተኩረው በአከባቢው ከሚገኙ ታጣቂ ሃይላት ጋር ትገናኛላቹ ፣ ለኦነግ መረጃ ትሰጣላቹ ፣ በመከላከያ ሰራዊቱ መሃል ሽብር ትነዛላቹ ፣ስለ ሕገ መንግስት አና ስለ ሰራውቱ ጥቅማጥቅም የምትጠይቁት ጥያቄዎች የተዛቡ አና ተቃዋሚዎች ያመነጩት ነው፣ስለ ሱማሊያ ዘማች የሰራዊቱ ኣባላት ጉዳይ ትወያያላቹ ስለ ቤተሰቦቻቹ እና ዘመድ አዝማዶቻቹ ጠቅላላ ሁኔታ መረጃ ኣምጡ፣ከዘመዶቻቹ የተቃዋሚ ፓርቲ ኣባል የሆነ ኣሊያም በውጪ የሚኖር ዲያስፖራ ዘመድ ካላቹ መረጃ ኣምጡ የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ምርመራ ብመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ምርመራ እንደሚደረግ ምንጮቹ ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊቱ አጅግ ተማሮ አንደሚገኝ እና ጠንካራ የሆነ ኣመራር ካገኘ የወያኔን ጉጅሌ ኣገዛዝ በመክዳት ክሕዝብ ጎን ለመሰለፍ ዝግጁ አንደሆነ ምንጮቹ ጠቁመው የተቃዋሚ ሃይላት ከፖለቲካ ሽኩቻ እና ከፕሮፓጋንዳ ወጥተው ለውጥ እንዲመጣ ጠንካራ ስራ መስራት ቢጀምሩ ሰራዊቱ ካለምንም ማወላወል ከጎናቸው እንደሚቆም ምንጮቹ ገልጸዋል፥የመከላከያ ሰራዊቱ ከብዐተሰቦቻቸው አና ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ሮሮ ሰላም እና እረፍት እንደነሳቸው በተለያይ ጊዜያት ተነግሮዋል።
በጋምቤላ ዲማ ወረዳ ነዋሪዎች በወያኔ ታጣቂዎች አየተዘረፉ መሆኑ ሲሰማ ጉዳዩን ለወያኔ ባለስልጣናት ቢያሳውቁም ባለስልጣናቱ ጭራሽ ሕዝቡ ኣርፎ አንዲቀመጥ እያሽማቀቁ ይገኛሉ። የድረሱልኝ ጥሪ ያሰማው የዲማ ወረዳ ነዋሪ በመንግስት ባለስልጣናት አከባቢን ሰላም እና ጸጥታን በማደፍረስ ወንጀል አየተከሰሰ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ አንዳለ በምስራቅ ሃረርጌ በደደ ቆቦ ከተማ ኦቦ ኢብራሂም የተባለ የኦሕዴድ ኣባል የወያኔ ሹም መገደሉ ታውቋል፥ይህ የወያኔ ባለስልጣን በሰባት ጥይት ተደብድቦ የተገደለ ሲሆን የገደሉት ታጣቂዎች ከኣከባቢው ወዲያው ተሰውረዋል።#ምንሊክሳልሳዊ