ቴዲ አፍሮ ጷግሜ 6 ቀን 2007 በአዲስ አበባ ላፍቶ ሞል ሊያደርግ የነበረው ኮንሰርት መከናወኑ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ቴዲ አፍሮ ጷግሜ 6 ቀን 2007 በአዲስ አበባ ላፍቶ ሞል ሊያደርግ የነበረው ኮንሰርት መከናወኑ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ግምት ኮንሰርቱ የመከናወኑ ዕድል 1 ፐርሰንት ብቻ› ነው፡፡ የኮንሰርቱ አዘጋጆች ለድምፃዊው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የከፈሉ ቢሆንም ለኮንሰርቱ ፈቃድ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ለ6 የተለያዩ ቀናት ቀጠሮ እየተሰጣቸው አዲስ አበባ ፖሊስ የተመላለሱት አዘጋጆቹ ምንም ምላሽ እስካሁን አላገኙም፡፡

በተለይም ባለፈው በጊዮን ሆቴል ቴዲ ኮንሰርት ባቀረበበት ወቅት ‹‹ጃ ያስተሰርያል›› የተሰኘ ተወዳጅ ሙዚቃውን እንደማይዘፍን ቀድሞ ቃል ገብቶ መዝፈኑ አሁን ፈቃድ እንዳያገኝ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡ በመሆኑም የላፍቶ ሞሉን ኮንሰርት ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ቴዲ ኢትዮጵያ ውስጥ ኮንሰርት እንዲሰራ ላይፈቀድለት ይችላል፡፡