የማለዳ ወግ…የባለስልጣኖቻችን ጉብኝትና የእኛ ኑሮ…. ! ” ባለስልጣናቱ የሚመጡት በስራ ስም ለገብያ ነው! ” ነቢዩ ሲራክ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የማለዳ ወግ…የባለስልጣኖቻችን ጉብኝትና የእኛ ኑሮ…. ! ነቢዩ ሲራክ
================================
* ከገበያ ያላለፈው የባለስጣኖቻችን የሳውዲ ጉብኝት …
* የባለስልጣኖቻችን ጉብኝቱ ትናንትና ዛሬ ..
* ባለስልጣኗ ብላቴናው መሀመድን ሳይጎበኙት ሄዱ …
* የሽሜሲው ውይይትና የሳውዲ ባለስልጣን ምላሽ
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በምንገኝበት በሳውዲ አረቢያ በአለማችን በመንግስት ባለስልጣናት ከሚጎበኙት ቀዳሚ መሆኑ አሊ አይባልም። ከጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ ባለስልጣል ጀምሮ በሚኒስቴር ፣ በሚኒስቴር ዴታና በዳይሬክቶሬት ኃላፊነት ያሉ ከፍተኛ ሹሞቻችን እያሰለሱ ጎብኝተውናል ። ምንም እንኳን ኃላፊዎች ሲመጡ ተራው ነዋሪን ለማነጋገር ባይችሉም በአደረጃቸት የታቀፉትን የገዥው ፖርቲ አባላት ፣ ማህበራትንና ኮሚኒቲውን በተደጋጋሚ ሰብስበው አነጋግረው ያውቃሉ። ለመንግስት አስተዳደር በታቀፉት ድርጅት በኩል ቀረቤታ ካላቸው ካደሬዎች ፣ በልማት ማህበር ተብየዎችና በኮሚኒቲው ኃላፊዎች የተሸራረፈም ቢሆን ነዋሪው ስላለበት ችግር ፣ በቆንስልና በኢንባሲ ተወካዮች ስላለው የመብት ማስጠበቅ ህጸጽ ሳይናገሩ የቀሩበት ጊዜ የለም ።
ዳሩ ግና የሚመጡት ባለስልጣናት ሁሉ ብሶት መከራው ን ሰምተው ” እርማት ይደረግበታል !” ብለው ቃል ከገቡት የሚጨበጥ ለመጥፋቱ ብዙዎችን ለነዋሪው ሳይሆን ለድርጅት ታማኝ አገልጋይ የሆኑ ካድሬዎች ሳይቀር ተስፋ አስቆርጧቸዋል ፣ አስከፍቷቸዋል ! እውነቱ ይህ ሆነና ሀገሪቱን ከፍተኛ የአስተዳደር ከፍ ያለ መቀመጫ ያላቸው ባለስልጣናት የህዝብና ሀገር ገንዘብ ተደርጎ የሚያደርጉት ጉብኝት ” ባለስልጣናቱ የሚመጡት በስራ ስም ለገብያ ነው! ” ወደ ሚል መደምደሚያ እንዳደረሳቸው ” መረጃው በእኔና ባንተ ይቅር! ” ያሉኝ አንዳንዴ ከፖለቲካው ሰብዕናው እያጠቃቸው አሾልከው መረጃ የሚያቀብሉኝ ከፍተኛ የኢህአዴግ ድርጅት ኃላፊዎች ሹክ ብለውኛል …
ከወራት በፊት ወደ ጅዳ መጥተው በአካል ያገኘኋቸ ው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ጋር ባረፉበት ሆቴል ተገኝቸ ብዙ በማህበራዊ ህይዎቱ ዙሪያ ስለሚታዩ የመብት ጥሰትና ተዛማጅ ጉዳዮችን ከነመረጃ ማስረጃው አቀብያቸውም ነበር ። በተለይ በተለይ ካረፉበት ሆቴል የአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ካለው የዶር ፈቂ ሆስፒታል ስለተኛው ስለ ብላቴናው መሀመድን እና በቤተሰቡ ላይ ያረፈውን የመከራ ቀንበርና በብሪማን እስር ቤት ለወራት በታሰርኩበት አጋጣሚ በአካል ያየሁትን ወንድም የከፋ በደል በተጨባጭ ማስረጃ አጫውቻቸው በጥልቅ አዝነውና እንባ ተራጭተናል …
በወቅቱ እጅጉን የከፋው በደል የከብትና ግመል እረኛ ሳለ ” ከብት አጥፍተሃል ” ተብሎ የታሰረው ” እረኛ “ወንድም በህግ ከለላ በእስር ላይ እያለ በአንድ አዕምሮ እስረኛ የባለቤቱን ነፍስ አጥፍቶ በታሰረ ያገር በደረሰበት ድብደባ አካሉን የረገፈው ጎልማሳ አሳዛኝ ህይዎት አሻውቻቸዋለሁ። ይህ ወንድም ፍትህ ርትዕ ማግኘቱ ቀርቶ በቂ ህክምና ሳይደረግለት በግፍ ከሳውዲ መሸኘቱን አግባነት የሌለው ስራ መሆኑን ለዶር ደስታ ከፎቶ ማስረጃ ው አሳይቻቸዋለሁ አብረን ተላቅሰናል ። ጉዳዩ እንዲጣራ ያደርጉ ዘንድ ያ ግፉኡ ወንድም የረባ ህክምና ሳያገኝ ለምን ተሸኘ ? አካሉ ረግፎ ሀገር እንዲገባ ከጅዳ ቆንስላ የመጓጓዣ ሰነድ ሊሴ ፖሴ ማን ሰጠው ? መጓጓዣ ከመሰጠቱ በፊት በህግ ከለላ ያለ ሰው ህግ በአስከባ ሪዎች እንዝህላልነት በደል ሲደርስ በት ለተፈጸመበት ወንጀል ተጠያቂዎች ለምን ለፍርድ እንዲቀርቡ አልተደረገም ? ቁስሉ ሳይሽር አዋክቦ ለመሸኘት ተፈለገ ? ለምን ተበዳይ ለተበደለው ካሳ አግኝቶ ይሂድ ተብሎ አልተጠየቀም ? ለሚለው ጥያቄ መልስ እንደ ሚያስፈልገው ከዶር ደስታ ወ/ ዮሃንስ ጋር ተስማምተን ፣ ባለስልጣኗ ይህንን ለማጣራት ቃል ገብተውልኝ ተለያየን ። ያ ከሆነ ቀናት ሳምንታትን ፣ ሳምንታት ወራትን እየወለዱ ጊዜው ነጉዶ ዛሬ ላይ ስንደርስ ” አዲስ አበባ የገባውን ወንድም እከታተላለሁ ፣ በመንግስት ሆስፒታል እንዲታከም አደርጋለሁ ፣ ጉዳዩን አጣርቸ ተጠያቂዎችን አጣራለሁ! ” ብለው ቃል ከገቡልኝ እመቤት ከዶር ደስታ ጠብ የሚል መልስ አላገኝ አልኩ .. ያ የፈረደበት ምስኪን መከረኛ ” እረኛ ” ወንድምም ህክምና ሳያገኝ ከነቁስሉ ተሸኝቷልና የድሃ ቤተሰቦቹ ሸክም ሆኖ ቀረ ፣ የዶር ደስታ ቃል እንደ ሀምሌ ጉም በኖ ጠፋ … ” ቄሱም ዝም ፣ መጽሐፉም ዝም! ” እንዲሉ ዶር ደስታ ቃል የገቡትን ሳይፈጽሙ እነሆ ግራ ያጋባ ለሁለተኛ ጊዜ የጅዳ ጉብኝታቸውን ከዋውነው ትናንት ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል ! የባለስልጣኗ ጉብኝት ምን ይመስል ነበር ? ካላችሁ ደግሞ ወደዚያው እናቅና …
የዶር ደስታ የንጉስ ፋአድ ሆስፒታል ጉብኝት …
=============================
በአዲሷ የሴቶች ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሁሴን አጋፋሪነት በንጉስ ፉአድ ሆስፒታል የተኙትንና ሶስት ታህል ታማሚዎች የጎበኙት ዶር ደስታ ምንም እንኳን የጉብኝታቸው መቋጫ ውሉ ባይገባኝም ሶስት ታማሚዎችን መጎብኘታቸውን በቦታው ከነበሩት ሰምቻለሁ ። በንጉስ ፉአድን ሆስፒታል ከተጎብኙት ታማሚዎች መካከል ባንድ ወቅት የጅዳ ቆንስል ከአፍንጫው ስር ለአመታት በሰመመን ውስጥ ስላለችው እህት ይጎብኝ ብየ መረጃ በማቀበሌ እኔና የመረጃ አቀባየ በቆንስሉ አንድ ዲፕሎማት የተወረፍንባት ማንነቷ ሳይታወቅ በንጉስ ፉአድ ለአመታት የተኛችው እህት ትገኝበታለች። ግራ ቢገባኝ ዶር ደስታ የዚህች እህት ማንነትና ይታወቅና ቤተሰቦቿ ይፈለጉ ዘንድ ትዕዛዝ በሉት መመሪያ አለመስጠታቸውን ስሰማ አዝኛለሁ ! የሴቶች ዳይሬክቶሬት ከሆስፒታሉ ኃላፊዎችም ሆነ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር ግንኙነት ፈጥረው የጎበኟቸው እህቶች ህክምናቸው ይሻሻል ስለማለታቸውም ሆነ አድራሻቸው የማይታወቀውን ለማጣራት ስላደረጉት ጥረትም ውጤት አልተነገረምና ፣ አልሰማሁም … ታላቋ ባለስልጣን መጎብኘታቸውን ብቻ ሰምተናል !
ክፍል አንድ በዚህ አከተመ …
የቀጣይ ወጎች ቅምሻ …
================
በዶር ደስታ ክፍል 2 …ዳሰሳየ
ሀሙሱ ፣ ሰኞ ፣ የሽሜሲ እስር ጉብኝት ውይይት …
===============================
በሳውዲ መንግስት በኩል ” ህገ ወጥ” ተብለው በሌሊት ቤት ሰበራና አፈሳ የታሰሩ ዜጎች የሚገኙበትን የሽሜሲ እስር ቤት ዶር ደስታ ሀሙስ ታሳሪዎችን ፣ ሰኞ የሳውዲውን ባለስልጣን ጎብኝተዋል …ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ እያላቸው ያለ አግባብ ለተያዙት ” መብታችን ተጥሶ ወደ ሀገር ለመግባት ፎርም አንሞላም!” ያሉትን በርካታ ኢትዮጵየ ያን እንዳገኙና እንዳወያዩዋቸው የጨነቀ የጠበባቸው ሁሌም እያለቀሱ ብሶት ምሬታቸውን የሚነግሩኝ ታሳሪዎች ያቀበሉኝ መረጃ ያስረዳል …
በዶር ደስታ ክፍል 3 4 … ዳሰሳየ
እያልኩ በማቀርበው ዳሰሳየ የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ የሴቶች ስብሰባን ይሆናል… ለቅምሻ ስቀጥል smile emoticon
=================================
የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ጉብኝት አስመልክቶ ጉብኝቱን ስዳስስ ይህም አይቀር ላንሳው ብየ እንጅ ውይይት ምክክሩ የረባ እንዳልነበር ተነግሮኛል። ዲፕሎማቶች በሞሉበት የሴቶች ስብሰባ የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሶስተኛ ሙት አመት በሻማ ማብራት ታስቧል ። ከዚህ ቀደም አዳራሹን የሚያደምቁት የድርጅት ማህበር አባላት ፣ የጅዳ ቆንስል ” ነጭ በሬ” ሴቶች ወይዛዝርት በዚህ የሴቶች ስብሰባ አልተሳተፉም። በጣት የሚቆጠሩ እህቶች በታደሙበት የቀዘቀዘ ውይይት ተደርጎም የብዙሃኑ ነዋሪ እህቶች ብሶት በስብሰባ ውይይቱ አልተንጸባረቀም …
****************
እልና በሴቶች ስብሰባ ስላልተወሳው በርካታ የሴቶች ጉዳይ ብላቴናው መሀመድ በባለስልጣኗ እንዳይጎበኝ ግፊት አለመደረጉን አነሳለሁ …
****************
..ቢረሳ ቢረሳ መዲና ለሁለት አመታት ያለ ጠያቂ በአንድ ሆስፒታል ተጥላ ያለችውን እህት ጉዳይ እንኳ ማንሳት ለምን አልተቻለም? ከአሰሪያቸው ተፈናቅለው ፣ ተባረውና ተጥለው በመጠለያው ስለሚገኙ እህቶች ፣ በኩንትራት መጥተው ስለሚሰቃዩ ፣ ስላበዱ ፣ ስለተደፈሩ መናገር አለመቻሉ ፣ በዘገየው ፖስፖርት መኖሪያ ፈቃዳቸው ስለወደቀባቸው ሴቶች እና ሌላም ሌላም መወያየት መረጃ ጠፍቶ ሳይሆን” ያገባኛል !” ባይ ለነፍሱ ያደረ ደፋር ጠፍቶ በስብሰባው ጥልቅ ውይይት ሳይደረግበት ተዘሏል ! ….
የሴቶች ዋና ዳይሬክቶሬት በተገኙበት ስብሰባ የመሀመድን ጉዳይ ለምን ማንሳትና መወያየት እንዳልቻሉ አልገባኝም ! ” ነግ በኔ !” ነውና ቢያንስ ማህበሩ የመሀመድን እናት በቤት ኪራይ ፣ በትራንስፖርት በመሳሰሉት እንደግፍ ብሎ መም ከር ያልቻለበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው ! ስል የሰላ ሂሴን እሰነዝራለሁ …
ለሁሉም የፈቀዳችሁ ተከተሉኝ …
ይቀጥላል ብያለሁ !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 19 ቀን 2007 ዓም


