የቴዲ አፍሮ ጉዳይ እያነጋገረ ነው::የደህንነቶች ጫና በርትቷል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የቴዲ አፍሮ ጉዳይ እያነጋገረ ነው::የደህንነቶች ጫና በርትቷል::
የእውቁ እና ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሕወሓት የሚደረግበት ጫና ኢትዮጵያ ውስጥ መነጋገሪያ መሆኑን ለመኖሪያ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ያላኩት መረጃ ይጠቁማል:ቴዲ አፍሮ በተለያየ ጊዜ በመገዱ ላይ እና በመኖሪያ ቤቱ አከባቢ የተመደቡ ደህንነቶች ሃገር ለቆ እንዲወጣ ጫና እያደረጉበት ሲሆን በከፍተኛ ፍተቻ እና የውጪ ጉዞ በማስተጓጎል ግፍ እየሰሩበት ይገኛሉ::
ለአዲስ አመት በላፍቶ ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ዘፈኑን መምረጥ ያለብን እኛ ነን በሚል የሕወሓት ደህንነቶች በድምጻዊው ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ላይ ሲሆኑ የቀን ተቀን እንቅስቃሴውን በመከታተል እና መኪናውን በማስቆም እያንገላቱት እንደሚገኙ ምንጮች ጠቅሰዋል::ቴዲ አፍሮ በመማረር ከሃገር እንዲወጣ እየጣሩ የሚገኙት ሕወሓቶች ምን ያህል በፍራቻ ድባብ ውስጥ እንዳሉ ያመለክታል::