እግዚአብሔር ካንች ጋር ይሁን ሃሊማ !! …. በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ !
#JusticeForMohammed #Ethiopia #SaudiArabia Nebiyu Sirak
የብላቴናው መከራና የትጉህ እናቱ ፍትህ ፍለጋ በጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ አዋዜ ሲወሳ ! (VIDEO)
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=P4TLDM9F_C8]
እግዚአብሔር ካንች ጋር ይሁን ሃሊማ !!
(አሌክስ አብርሃም)
ይሄ ድንቡሸ ህፃን መሃመድ ይባላል ….መሃመድ የሃሊማ ልጅ ነው ! ሃሊማ ኢትዮጲያዊት ናት ኑሮዋን መካ ያደረገች ….. አንድ ቀን ታዲያ የዛሬ ዘጠኝ አመት አካባቢ ይሄ ልጅ ታመመና እናቱ ወ/ሮ ሃሊማ ከመካ ወደጅዳ ወሰደችው ለህክምና …..ጅዳ በሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥም የታመመው ቶንሲል ነው ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል አሉ ሃኪሞቹ ይች ኢትዮጲያዊት እናት የልጇ ደህንነት አጓጉቷት ፈቀደች ….
ቀዶ ጥገናው ተካሄደ ! ውጤት ….. የአራት አመቱ መሃመድ ራሱን ከሳተበት ሊነቃ አልቻለም ! አንደ ቀን አይደለም ሁለት ቀን አይደለም ሳምንታት ወራት አይደለም …ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በቃ ልጁ በድን ሆነ!! (ከሞቱት በላይ ካሉት በታች እንደሚባለው) …እናት ይሄን ሁሉ ዓመት ከልጇ አልጋ ስር አልተለየችም ….ይባስ ብሎ በራሱ ችግር ይህን መዓት ያስከተለባት ሆስፒታል ከሰሞኑ ሆስፒታሉን ለቃ እንድትወጣ አዘዛት …. በእርግጥ 2.4 ሚልዬን የሳውዲ ሪያ. ካሳ ሊከፈላት ሆስፒታሉ ጠይቋታል …የወ/ሮ ሃሊማ ምላሽ ግን አንድና አንድ ሆነ
‹‹ብራችሁን አልፈልግም ልጀን አድኑልኝ !!››