ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ “ዋይት ሃውስ” እስር ቤት ተዘዋወረ:: ሁለት ነብሰ ገዳይ ወንጀለኞች አብረውት ታስረዋል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከየመን አየር ማረፊያ ትራንዚት ላይ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እስከዛሬ በማይታወቅ ቦታ ታስሮ ከፍተኛ ቶርች እየተፈጸመበት ሲሆን ባለፈው ሊጠይቁት የሄዱት የእንግሊዝ አምባሳደር እንዳሉት አንዳርጋቸው ካለሁበት ሁኔታ ይልቅ ሞትን እመርጣለሁ እንዳላቸው የሃገራቸው ጋዜጣ አምባሳደሩን ጠቅሶ ማውጣቱ ይታወሳል:: http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=102550
ከዚህ ቀደም የውጪ ሃይሎች ጫና የበረታበት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ወደ ቃሊቲ ለማዘዋወር እስክንድር ነጋ ታስሮበት የነበረበትን ክፍል ሲያድሱ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እስከዛሬ ሳይዘዋወር ቆይቷል::በዚህ ሰሞን የአሜሪካ የአውሮፓ ሕብረት እና የእንግሊዝ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናት የጻፉትን ደብዳቤ እና የአልጀዚራን ዘገባ ተከትሎ ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እነ አንዱአለም አራጌ ያሉበት አከባቢ ሆኖ ለብቻው ከሁለት ሰዎች ጋር ቃሊቲ እስር ቤት ዋይት ሃውስ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ መዘዋወሩን መረጃዎች ጠቁመዋል::
አንዳርጋቸውን ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስገብተውታል፡፡ እነ አንዷለምአራጌ በታሰሩበት ክፍል ሆኖ ለሱ ብቻውን የተሰራለት ክፍል አለ፡፤ ሃይት ሃውስ (white house) ይባላል፡፡ እዛ ውስጥ ነው ታስሮ የሚገኘው፡፡ አብረውትም አደገኛ ነፍሰገዳይ ወነጀለኛ የሆኑ ከዞን 8 ከሶስተኛ ቤት እና ከዞን 6 ከአንደኛ ቤት ሁለት ሰዎችን አብረውት እንዲታሰሩ አድረገዋል፡ ስማቸው
1ኛ አሰፋ ኮሴ ረታ እና
2ኛ ዳዊት ብርሃኔ
የሚባሉ ሰዎችን አብረውት እንዲታሰሩ አድረጋል፡
ሁለቱ ሰዎች እጅግ በጣም አደገኛ ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኞች ናቸው፡፡ በማረሚያ ቤቱ በልዩ ጥበቃ የሚታዩ ናቸው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ስራቸው አንዳርጋቸው ፅጌን የሚሰራውን.የሚለውን የሚበላውን ባጠቃላይ የሱን ሙሉ እንቅስቃሴ ከውጪ ለሚመጡት የደህንነት ሃይሎች ርፖርት የሚያደርጉ ናቸው፡፡
ከነዚህ ነፍሰገዳዬች ጋር ያሰሩት እሱን ለማሸማቀቅ እና እሱ ላይ የፈለጉትን ነገር ቢየደርጉት በነሱ ለማሳበብ ነው፡፡ እሱ በጣም መጥፎ ሰቆቃ ላይ እንዳለ ነው መረጃው የጠቆመው::