አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ወንጅለዋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ወንጅለዋል::

Minilik Salsawi የሕወሓት ሆድ አደር ሹመኞች በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ላይ አንሳተፍም ሲሉ አጉረመረሙ:: – በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተከሰተውን አለመተማመን ለመቆጣጠር በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀመረ:: በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ግምገማ አዳዲስ ምድብ የደህንነት አባላት መረጃዎችን በግል ጥቅም በመለወጥ አሳልፋቹ እየሸጣችሁ ናቸው በሚል መገምገማቸውን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።እንደ ምንጮቹ ከሆነ መረጃን ያለምንም ርሕራሔ እየቸበቸባቹ የድርጅታችንን ምስጢራዊ ጉዳዮች የያዘ መረጃው በአምስት ደቂቃ ውስጥ ጠላት እጅ ገብቶ ያገኘነው ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ተናግረዋል።በዚህ ግምገማ የተከፉት የደህንነት አባላት በመንግስት ባለስልጣናቱ እየተናጡ ቢወረፉም ዝምታን መርጠዋል።

የሕወሓት ሆድ አደር ሹመኞች በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ባለመሳተፋቸው ማማረራቸው ተሰምቷል በሃገሪቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መንግስት እንቅስቃሴ ውስጥ ከወያኔ ባለስልጣናት ውጪ ለበታች ተከታይ ባለስልጣናት ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደቆመ ሲታወቅ ማንኛውም ሃገራዊ ጉዳይ አልቆ እና በአፈጻጸም ደረጃ ላይ ሆኖ እንደማንኛውም ሰራተኛ እንደሚሰሙ ባለስልጣኖቹ በመናገር ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተከሰተውን አለመተማመን ለመቆጣጠር በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀመረ::የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ ከሃገሪቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በማበር አደጋ ሊፈጥር ይችላል ሲል መፈራቱ እንዲሁም ሰራዊቱን እየከዱ የሚሄዱ መበራከታቸው አለመተማመኑን ከማስፋቱም በላይ በሕወሓት የጦር እና ደህንነት ክፍሎች ውስጥ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል ሲሉ ውስጥ አውቂዎች ይናገራሉ::

ክዚህ ቀደም ተሞክሮ እንዳልተሳካ እና አሁንም ከባለፈው አካሄድ እና ግምገማ በተሻለ መልኩ በወያኔ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ አዳዲስ የሆኑ ውስጣዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ በሰራዊቱ መካከል እየተከሰተ ያለውን አለመተማመን ለመቆጣጠር የሚረዱ ግምግናዎች እና የማጣሪያ ስብሰባዎች በስፋት መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በፖሊስ ክፍሉ ውስጥ በተለይ በቡድን የሚያሴሩ ሰዎች አሉ እየተባለ ስለሚነገር የወያኔ አንድ ብሄር ሰዎችን በስፋት በመመደብ እንዲሁም ከዚህ ቀደም እንደተደረገው የቢሮ ሰራተኛውን ከደህንነት ቢሮ በሚመደቡ የሕወሓት ደህንነቶች ለመተካት የታቀደ ሲሆን ቀሪውን ከቢሮ ውጭ የሚሰራውን የፖሊስ አካል ለመቆጣጠር አዲስ ሃይል እንደሚመደብ ታውቋል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬