ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የጋሞ ብሔር ተወላጆችና ሌሎች ነዋሪዎች በተገኙበት አርባ ምንጭ ከተማ በደማቅ መልክ ተደረገ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Arbaminch

ሕዝብ ጨዋነቱን ነገር ግን እጅጉን መቆጣቱን የገለፀበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ፡ታሪካዊና እጅግ በጣም አስደማሚ የሆነ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ከ 80 – 100, 000 የሚቆጠሩ የጋሞ ብሔር ተወላጆችና ሌሎች ነዋሪዎች በተገኙበት ሐምሌ 29/2007 ዓ.ም በውቧ አርባ ምንጭ ከተማ በደማቅ መልክ ተደረገ፡፡ በሰልፉ አያሌ መልዕክቶች ከመሰማታቸውም በላይ ስለ ጋሞ ብሔር ጀግንነትና ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ልጆች ጋር ተከባብሮና ተፋቅሮ ስለመኖሩ ተወድሷል፡፡ ስለ አንድነቱም ተዚሟል፡፡ ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ጥገኞችና ሰርጎ ገቦች ታደላ ቱፋና ግብረ አበሮቹን ጨምሮ ስለጋሞ ሕዝብ የመናገር ስብዕናም ሞራልም የላቸውም፣ ቁጫ – ዶርዜ – ምን ምን እያላችሁ አትከፋፍሉንም፣ አንደ ጥንቱ ዛሬም እኛ ጋሞዎች አንድ ነን (ኑኒ ኢሲኖ)፣ ጋሞይ ጊታኮ፣ የመፅሐፉ ፀሐፊና ግብረ አበሮቹ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ የሚሉና ሌሎች መፈክሮች የተደመጡ ከመሆናቸውም በላይ አርባ ምንጭ የምትወድም ሳትሆን በሕዳሴ ጉዞ ላይ ያለች ከተማ ነች፣ እሷ ሳትሆን አውዳሚዎቿ ራሳቸው ይወድማሉ፣ እናም ታደለ ቱፋና ግብረ አበሮቹ እርማችሁን አውጡ ዓይነት መፈክሮች ከተማዋ ካላት የተፈጥሮ መስህቦች ውዳሴ ጋር ተዳምረው በሰፊው ተስተጋብተዋል፡፡

በመጨረሻም ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ በተጨማሪም በሃገር ባህል ሽማግሌዎችና በሐይማኖት አባቶች፡- በጥገኞች፣ በሟርተኞች፣ በስድብ ደራሲውና በግብረ አበሮቹ ላይ ያቶኮረ ውግዘት ታክሎበት በሰላም ተጠናቋል፡፡

ተለብሶ ቀይ ብጫ እንዲሁም ጥቁር፤
በቲሸርት ድንጉዛው አቤት ሰልፉ ሲያምር፡፡
ካልነኩት ማይነካ ከነኩትም ማይለቅ
ሆላ ጋሞስ ሆላ ጠላቱን የሚያደቅ!!! ሐምሌ 29/2007 ዓ.ም