በአንዳርጋቸው ጽጌ ስም ሊወጣ የታቀደውን መጽሀፍ ያዘጋጁት አቶ በረከት ስምዖን መሆናቸው ታውቋል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከብአዴን ቁልፍ ባለስልጣናት የተገኘው ጥብቅ መረጃ ላይ እንደተብራራው አቶ በረከት መጽሀፉን እንዲያዘጋጁ ከተወሰነ በሁዋላ ከመንግስት መደበኛ ስራም ሆነ ከመድረክ ለረጅም ወራት ጠፍተዋል:: መጽሀፉ በጥንቃቄ እንዲዘጋጅ ከፍተኛ ሃላፊነት የተሰጣቸው አቶ በረከት ከደህንነት መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን መረጃዎችን ሲሰበስቡ ከርመዋል:: የአቶ አንዳርጋቸውን ግላዊ ህይወት ከማጥናት አንስቶ የቤተሰባቸውን ሁኔታ በኤርትራ የነበራቸውን ቆይታ በአጠቃላይ የአቶ አንዳርጋቸውን የአጻጻፍ ስልት ሳይቀር በማጥናት የሰዉን ጥርጣሬ በሚያጠፋ መልኩ እያዘጋጁት እንደሆነም የተገኘው መረጃ ያመለክታል::
የግንቦት ሰባት አመራር ውስጥ የነበሩና ሀገር ቤት የገቡት(ቪላ ቤት ተሰጥቷቸው እየተቀለቡ ያሉት) 3 ግለሰቦች የድርጅቱን መረጃና በኤርትራ የአቶ አንዳርጋቸውን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ምን እንደነበረ መረጃውን በዝርዝር ለአቶ በረከት እንዳቀበሉም ይነገራል:: የመጽሀፉን ይዘት በተመለከተ በዝርዝር መረጃው የሚወጣ ይሆናል:: አቶ አንዳርጋቸውን በተቆራረጠ ምሥልና ድምጽ መጽሀፉ የራሱ መሆኑን ሲገልጽ የሚያሳይ ቃለመጠይቅም ሊዘጋጅ እንደታቀደም ከውስጥ የመጣው መረጃ ያመለክታል::