ሊቢያ ውስጥ በአይሲስ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በተለያዩ ሰዓቶችና ቦታዎች በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስም ስለተካሄዱት መታሰቢያዎች አጭር ዘገባ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


zebene

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያኖች በዋሽንግተን ሞኑመንት ላይ “የታረዱት ነፍሳት ጩኸት” በሚል ርእስ አቅርበዋል።  “ዲያብሎስን እምቢ በል” በሚል ርእስ በመምህር ዘበነ ቀርቧል።  ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባው ሲኖዶስ በገለልተኝነት ራሳቸውን ያሰለፉ ተመሳሳይ አቋም ያላቸው አካላት ናቸው። የሁለቱም  መነሻ  በአይሲሲ ስለ ተገደሉት ኢትዮጵያዉያን  ሀዘንና ወገናዊነትን ለመግለጽ ነው። ለምን ተለያዩ?ለሚለው ጥያቄ  መልሱ ከሁለቱም የሚጠበቅ መሆኑን  ሳንዘነጋ፤  ሁለቱም በዝግጅታቸው  ለታዳሚው ህዝብ ራሳቸው የሚጠኑበትን እና ከትዝብት ላይ የጣላቸውን አቅርበዋል።

የሁለቱም አሰላለፍ ስለተገደሉት ወገኖቻችን ሲሆን፤   በታሪክ በእምነት በሞራል፤ በሰባዊነትንና በዜግነት ከመመዘን የማያመልጠውን አቋማቸውን በሰማእታቱ ህልፈት ላይ አንጸባርቀዋል።  ኢትዮጵያ ሪቬው  በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ ያስነሳውን ህዝባዊና ወገናዊ ስሜት በጥንቃቄ በመመልከት በሰጠው ዘገባ፤ ሌሎች ብዙ  አስገራሚ ክስተቶች    በማከታተል አቅርቧል ።

የኢትዮጵያ ሪቪው በመጀመሪያ በ May 10, 2015, ዋሽንግተን ዲሲ ብሔራዊ  አደባባይ ላይ “የታረዱት ነፍሳት ጩኸት”  በሚል ርእስ  የተፈጸመውን ዝግጅት እያሳየ፤  እንደገና  በ June 14, 2015 በኬና ቴምፕል ይደረጋል እየተባለ  በመምህር ዘበነ ይነገር  የነበረውን አንባቢ በማስተዋል ተመልክቶ የራሱ ግንዛቤና ትዝብት እንዲኖረው የሚያሳስብ ፍንጭም  ሰጥቶ ነበር። በሞንመንቱ ላይ በተካሄደው ዝግጅት ላይ ከመምህር ዘበነ እና ከተስፋየ መቆያ በቀር ያልተሳተፈ  ድርጅት አልነበረም።  እነ መምህር ዘበነ በሞኑመንቱ ዝግጅት ላይ ያልተሳተፉበት ምክንያት አይሲስ ገደላቸው እያልን እንናገረ  እንጅ፤ ተሰደዱ የሚለውን ካነሳን ከወያኔ ጋራ ያጋጨናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የጀመርነውን ሥራ ያደናቅፍብናል ብለው ራሳቸውን ከመደበቃቸው ባሻገር፤   ለማደናቀፍ ብዙ ጥረት  አድርገዋል።  ለህዝብ እንዲሰራጭ የተዘጋጁትን ካርዶች ለህዝብ እንዳይደርሱ ወደ ቆሻሻ ጥለዋቸዋል፣ “የፖሊቲካ  ነው” የሚል የሐሰት ወሬም አሰራጭተዋል።

በሞንመንቱ ላይ እንዲካሄድ ታስቦ በጥናት ላይ በነረበት ወቅት የፖለቲካ ነው እያሉ እነ ዘበነ አስወሩ።  በመምህር ቀሲስ ዘበነ ለማ  የሚመራ ዋሸንግተን ዲሲና በአካባቢዋ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ጉባኤ በሚል ስም የተሰየመ ቡድን ብቅ አለ። ራሱ ዘበነ በሚያቀርበው ሬድዮ ፕሮግራም ጥያቄና መልስ ላይ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን አባት “እኔ ቆራቢ ነኝ። ያልሆነ ነገር በጭንቅላቴ ቋጥሬ መዋልና ማደር ህሊናዬ  አይፈቅድም። ባለፈው በዋሽንግተን ሞኑመንት ላይ በተደረገው ላይ ተስፋየ መቆያና አንተ (መምህር ዘበነ) እኛ አገር ቤት የተለየ ስራ አለን፣ ይህ ስራችንን ያበላሽብናል ብላችሁ እንዳልተገኛችሁ ስማቻለሁ።  ይህ የሰማሁት እውነት ነው? ወይስ ውሸት ነው?ብለው  ጠየቁት።  መምህር ዘበን የአዛውንቱን ጥያቄ አድበስብሶ  ለማለፍ  ሞከረ። እኒህ አዛውንት ተልእኴቸው እውነትን ማወቅ ነውና “የምጠይቅህ  ለሁሉም የሚጠቅም ስለሆነ አድበስብሰህ ልታልፈው አይገባም” በሚል አባታዊና  ክርስቲያናዊ በሆነ ድምጽ ተቋቋሙት። የሚገርመው ነገር ላዛውንቱ መልስ ለመመለስ ሲሞክር ሁለት ስህተቶችን ፈጸመ።

1ኛ  በሞንመንቱ እንዲደረግ ስለተጀመረው ዝግጅት አልሰማሁም አለ። 2ኛ ከሁሉ በፊት አስቀድሞ  የጀመረው አሱ እንደሆነ ተናገረ። ዝግጅቱ  በቅድስት ማርያም የተጀመረው ሰማእታቱ በተገደሉበት እለት የዳግም  ትንሳኤ (April 19, 2015) ነው። በዚሁ ቀን በርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለህዝብ ተገለፀ።   ነገር ግን የሰማእታቱ መገደል በመምህር ዘበነ ዙሪያ ላሉ የሰዎች  ተነግሮ  ነበር። መምህር ዘበነ ግን ለህዝብ አላቀረበም። በየርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም የቤተ ክርስቲያን ዜናው እንደተሰማ ለምእመናን ተነግሮ ስለሚቀጥለው ዝግጅትም  ወደፊት እንደሚገለጽ ተነገረ። በሚቀጥለው ዓርብ (April 24, 2014)  በቅድስት ማርያም የሀዘንና የመታሰቢያ ጸሎት ተደረገ።  በዚያው እለት መምህር ተስፋዬ  መቆያ  “በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያደረገነው ጸሎት ለእግዚአብሔር ነው። ይሁን እንጂ  በአደባባይ ለዓለም ህዝብ እናቀርባለን” ብሎ ደጋግሞ  ተናገረ።  ይህንንም ሲናገር  ከዚያ በፊት በማርያም ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ጊዜ መጥቶ  የማያውቀው መምህር ዘበነ ነበር።

ይህ  ዝግጅት በተለያዩ  መገናኛወች ተገልጾ ሳለ፤  በራሱ ሳምንታዊ የራዲዮ  መርሀ ግብር ላይ ከአዛውንቱ የቀረበለትን ጥያቄ እልሰማሁም በማለት ዘግቶት አለፈ። ለሚመለከታቸው ሁሉ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች በታሰበው መሰረት እንደሚፈጸም መገለጹ መካድ የሚቻል ባይሆንም፤ መምህር ዘበነ” በመኑመንቱ ስለሚደረገው አልሰማሁም”  አለ።  ለመስማቱ ላሰሙት ወገኖች  ኃላፊነቱን ትተን፤ ያዛውንቱን  ጥይቄና የመምህር ዘበነን መልስ  በጥሞና ለማዳመጥ የሚቀጥለውን  ለመስማት ይህን ሰንሰለት ይጫኑ። http://www.mereja.com/amharic/456601

በአዛውንቱና በመምህር ዘበነ መካከል የተካሄደውን ካደመጥን፤   እያየን እየታዘብን እንለፈው ካልተባለ  በቀር ጥያቄ ያፈለቀችውን የአዛውንቱን ህሊና ተገንዘበናል። ካዛውንቱ የፈለቀችውም ጥያቄ ንጽህ ህሊና ያላቸው ሁሉ ዜጎች የሚጠይቁት ነው። በዘመናችን ተደብቆና ተሸፍኖ የሚቀር ስለሌለ በሁለቱም የተከናወኑት ዝግጅቶች ተቀርጸው ቀርበዋል። ተመልክተው የራሰዎን ግንዛቤ ይውሰዱ።

1ኛ፦በሞንመንቱ ላይ የተካሄደው በሁለት ክፍል  ተዘጋጅቶ  የቀረበው

ክፍል 1 https://www.youtube.com/watch?v=sBf3bV8qnA4

ክፍል 2  https://www.youtube.com/watch?v=gRuJBhrm5O4

2ኛ፦በመምህር ዘበነ ለማ የቀረበው ዝግጅት https://www.facebook.com/misikir.tadele.1/videos/912237365500211/

ይቀጥላል