ጽንስ የሚያጨናግፍ ወረተኛ ምላስ! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሰው ልጅ በባህሪው ንጹሕ ፍጥረት ለመሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ከልደት በኋላ ህይወት የማይገኝበት ኃይማኖት ጨምሮ በተለያዩ ውጫዊ ተጽዕኖዎች ራሱ እኔሲል የሚገልፀው/በሚቀርጸው ማንነት ግን ስብዕናው ከእውነት ይልቅ ሁለመናው ለሐሰት/ለስህተት እጅግ ቅርበት ያለውና በእንግዳ ነፋስ ለመወሰድም ጊዜ የማይፈጅበት ፈጣን ፍጥረት ለመሆኑ አንባቢ ይህን ጽሑፍ በሚያነቡበት ቅጽበት ለአፍታ ቆም ብለው የገዛ ራስዎትን ህይወት ቢመረምሩ ነገሩ በቀላሉ ሊያረጋግጡት የሚችሉት ሐቅ ነው።  ሐሜተኛ ሰው ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሸኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ይወርዳልእንዲል።

ውሸትና በውሸት የሚፈጸሙት ወንጀሎች፣ እንዲሁም ውሸት በቁሙ ከአንድ ግለሰብ/ዜጋ ህይወት አልፎ በቤተሰብና በሀገር ደረጃ የሚያደርሰውና/የሚያስከትለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት አንስተን ተወያይተናል። በዛሬ ዕለት የመወያያ ርዕሳችንም በተመሳሳይ ሚድያና የሚድያ ሰዎች የተበላሽች፣ ሰላምና አንድነት የራቀባት በአንጻሩ ትርምስ ሁከትና የእርስ በርስ ጦርነት የማይለይባት ሀገርና ዓላማ የለሽ፣ ነህዘላል፣ ቀቢጸ ተስፋ ከዚህም አልፎ ወንድሙን አጋድሞ አንገቱን ከመቀንጠስ የማይመለስ በደም የሰከረና ደም የተጠማ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ትውልድ በመፍጠርና በማፍራት ረገድ ሚድያ እያበረከተው ያለና የሚድያ ሰዎች የሚያበረክትቱን የጎላ አስተዋጽኦ/ድርሻ በመጠኑ በመዳሰስ በተለይ በያዝነው ዓመት የእምነት ተቋሞችን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎችና የውስጥ ሃይማኖታዊ አሰራሮችን በማነጣጠር ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸውን የሚያመዝኑ ሥራዎችን በመስራት ስም እያተረፈ የሚገኘው ኢሳትበመባል የሚታወቀው የዜናማሰራጫ ማዕከል ሥራዎች መካከል የኢ////ያን ወቅታዊ ሰጣ ገባ በተመለከተ በዚህ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ያሰራጨውን መሰረተ ቢስ ውንጀላ የሚያነጥን ይሆናል። ሙሉ የሐተታውን ይዘት ለማዳመጥ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ሊያዳምጡት ይችላሉ http://ethsat.com/video/?tubepress_video=HU2rYkmS3-c&tubepress_page=1

የራስህ ያልሆነ፣ ያልተገባህ ረብና የግል ጥቅምም ለማስጠበቅ/ለማግበስበስ፣ ከመቃብር የማያልፍ ጠፊ ሀብተ ንብረት ለመሰብሰብ ሲባልም ከምንም በላይ ደግሞ ቅንና የዋህ ልብ በቀላሉ ማዋለል ይቻል ዘንድ ጠማማ/ዋሾ አንደበት የጎላ ሚና ይጫወታል። በሰለጠኑ የዓለማችን ምዕራቡ ክፍል እንዲህ ዓይነቱን የሥራ መስክ ማለት መረጃዎችን ከማዛባት ጎን ለጎን የፈጠራ ወሬዎችን በመንዛት ረገድ በሚኒስትር ቢሮ ደረጃ የሚመራ ሲሆን በዘርፉ የሰለጠኑ፣ የፈጠራ ታሪክ በመስራት የተካኑ፣ የራሳቸውን ጥቅም እንጂ የሌላውን ሰው መጎዳት ትርጉም የማይሰጣቸው፣ ሐዘኔታም ሆነ ርህራሄ ብሎ ያልፈጠረባቸው፣ ማንኛውም ትልቅም ሆነ ትንሽ የሚሹትን ነገር ለማግኘት ሲባል ብቻ ነፍስ መጣል ካለባቸው በተፈጥሮው ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ መግደል ማለት ንጹሕ ውኃ ከመጠጣት የተለየ ስሜት በማይፈጥርባቸው ባለሞያዎችም የተደራጀ ነው።

ኢሳት በኢ////ያን ጉዳይ ላይ መልኩና አቀራረቡ እየለዋወጠ ሲያሻው ለቤተ እምነቱ ተከታዮች ልዩ ጠበቃና ተቆርቋሪ በሚመስል በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ገለልተኛ ቢጤ በሚመስል አቀራረብ የማይገናኘውን ሁሉ እያገናኘ እንደ ድንግል መሬት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ አንድ ጊዜ የተከለውን ማረሻ እያመላለሰ በቤተ እምነቱ የኃይማኖት መሪዎች ያለውንና የሚታየውን አለመግባባትና አለመደማመጥ በተመለከተ ጉዳዩ ከቤተ እመነቱ ተከታዮች አልፎ በመላ ዜጎች አእምሮ ውስጥ የተሳሳተ ምስል ለመቅረጽ ቀን ተሌሊት ዓይኔን ግንባርያድርገው!” በማለት የመውጋት ዘመቻው ገፍቶበታል።

በነገራችን ላይ ይህ ወደ አሥራ አራት ደቂቃዎችን አከባቢ የሚጠጋ አጭር ሐተታ ጭብጥና ማዕከል ሁለት ነገሮችን አልሞ የተሰራ ሥራ ነው። አንደኛ ላይመለስ አንድ ጊዜ ፈጽሞ የተበነውንና የተሰራጨውን የኢ////ያን ከድህረ ቅዱስ ፓትሪያርክ አባ ጳውሎስ ዕረፈተ ሥጋ በኋላ የተገጠማትን የኃይማኖት መሪዎች የሥልጣን ሽኩቻ ነገሩ ከሰማይ እንደወረደ ህብስት አድርጎ አጋጣሚውን ለመጠቀም ምጦ የነበረውን ኃይል ቅስም የሰበረ ከኢፈድሪ መንግሥት ፕረዚደንት ቢሮ ተፈርሞ የወጣውን ደብዳቤ ለማሳጣት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላልብሎ ፈሊጥ እንደ መርህ በመውሰድ አሁን ባለው ነባራዊ የኃይማኖት መሪዎች የእርስ በርስ በማነካከስ በኩል ትልቁና የተጣለውን መልአክ የክንፉ ስብርባሪው ማኅበረ ቅዱሳንበማለት ራሱን የሚጠራ ግብረ እኩይ ስመ መንፈሳዊ ድርጅት ትቶ ያለ አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ የተለመደው መንግሥትን የመወንጀል አባዜ ለመወጣት ያክል ነው። ብርቄም ተንታኝ! ጥበብ በዚህ አለ።

ክቡራን አበው ካህናት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭው ዓለም የምትገኙ የምሥራች ቃል ተናጋሪዎች አግብርተ እግዚአብሔር መምህራን: የጌታ ሐዋሪያ የሆነው ቅዱስ ያዕቆብ በጻፈው መጽሐፍ ምዕራፍ ሦስት እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን። እነሆ፥ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ። እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።ሲል ስለ ጠማማ አንደበት አደገኝነት ማብራሪያ በማያስፈልገው ሁኔታ በማያሻማ አገላለጽ ፍንትው አድርጎ እንደ ገለጸው ብርሃናተ ዓለም ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም በበኩሉ እንዲህ ያለውን ፈረሰኛ የማይመልስው ቆማጣ ከሚነዛው ወሬና አሉባልታ በተጨማሪም ከሥራ ፈቶች ውሸትና ጠማማ አንደበትም የተነሳ የሚነደው እሳት/ሰደድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ጉባኤ መታደግ ይቻለን ዘንድ እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል” ሲል እንዳስተማረን በዋናነት ብቸኛ የደህንነት መንገድ የሆነውን ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ከመመስከር ጎን ለጎን የነውጠኞችና የሲዖል መልዕክተኞች (መልካም ነገር የማይወጣበት/የማይገኝበት ለማለት ተፈልጎ ነው።) አንደበትም ጥበብ የተሞላበትን ቃል በሥልጣን በመናገርና በመግለጥ ዝንጉ ምላስ ዝም የማሰኘት ግዴታ አለብን።

ከለበሱት ልብስ በስተቀር የሚታይ ነገር የሌላቸውና እናንተን ብሎ መንፈሳውያን/ሊቃነ ጳጳሳትሲል ምእመን ዕንባውን እያፈሰሰባቸው የሚገኙ የኃይማኖት መሪዎች ልብ ይገዙ ዘንድ፣ የቆሙበትም መንገድ ይሰልሉና ከእልከኝነትም ይልቅ ነን የሚሉት የተቀመጡበትን መንበር ይመስሉ ዘንድ፣ ልባቸውም ለሰላምና ለአንድነት ያነሳሱ ዘንድ በተለይ በምዕራቡ ዓለም የምትገኙት አብያተ ክርስቲያናት የተጀመረውን ምእመናንን የማስተማር፣ የማንቃትና የማደራጀት እንቅስቃሴ ሌላ እክል ሸልኮ እስካልገባበት ድረስ ጅማሬው የሚበረታታና በተጠናከረ መልኩም ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተመክሮበመቅሰም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ የሚገባቸው ሲሆን እንቅስቃሴው/መሰባሰቡ ከዚህ ባለፈ መልኩ መጽሐፍ እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ ሐሜት ከሌለም ጠብ ይቆማል፡፡ ከሰል ፍምን፣ እንጨትም እሳትን እንደሚያበዛ ሁከተኞችም ጠብን ያባብሳሉ፡፡ (ምሳ. 2620- 22)እንዲል ትመሩት፣ ታስተምሩትና ትመግቡትም ዘንድ አደራ በተጣለባችሁ ሕዝብ መካከል ላይ የመቃብር አፈር የሚነሰንሱ፣ ጥርጣሬና ጥላቻ ይነግስ ዘንድም ቀለብ እየተሰፈረላቸው ነገርን በማሴርና ወሬንም በማጠንጠን የቅኖችን ልብ ለመስለብና ለማዋለል የማይተኙ ሁከተኞች ላይም የቤትህ ቅናት ይበላኛል!” ስንል ፊት ለፊት ተመሳሳይ የሆነ እርምጃዎችን እንወስድና ወረተኛ ምላስም ዝም እናሰኝ ዘንድ ጥሬዬን አቀርባለሁ።

ሌላ እንዲህ ያለውን የመንታ ምላስ ውጤት የሆነውን ድምጽ ለቤተ ክርስቲያን ቁመናልበሚሉ ድረ ገጾች ሳይቀር ሲስተጋባ ማየቱ እጅግ የላቀ የልብ ሐዘን እንደሚሰማኝ ስገልጽ በእግዚአብሔር መንፈስ፣ ህይወት ይሆነን ዘንድም በተሰጠን ቃል መነጽር ድርጊቱ የተመዘነ እንደሆነ ነገሩ የዕድገት መገለጫ መሆኑ ቀርቶ መንፈሳዊ ክሳራ/ዕውርነት ተከትሎ የሚመመጣውን ዝቅጠት መሆኑ ስገልጽ በአክብሮት ነው። መንፈሳዊ ሥራ የሚሰራም በሞቅታ፣ በስሜት፣ እኔስ ብሆን ከማን አንሼ ነውበማለትና በስማ በለው ሳይሆን እግዚአብሔርን በመጠየቅ፣ በቃሉ እንደ ተፃፈም ባለው ሳንጨምርና ሳንቀንስ እንደ መልዕክተኛ እንዲሁ ማስተላለፍ እንደሚገባን በአጽንዖት ለመግለጽ እወዳለሁ።       

በመጨረሻ በሀገሬ ሳለሁ በቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአንደኛ ዓመት የሥነ መለኮት ተማሪ ሁኜ አራት ኪሎ አከባቢ ከምትገኘው በደንበኝነት ጸጉሬን ከምስተካከልባል አነስተኛ የጸጉር ቤት አስተካካል ጠረጴዛ ያገኘኋትን የክርስትና ቤተ እምነት መጽሔት መንፈሳዊ ግጥም መጠነኛ ማሻሻያ በማድረግ ያዘጋዠኋት ግጥም በማስነበብ ልለያችሁ።

የማያስተውል ዝንጉ ምላስ፣

የሚዘለዝል እንደ መቀስ፣

ያልተቀደሰ ተራ አንደበት፣

ሹክታው ሃሜት፣

ጩኸቱ ኩራት የሆነበት፣

ከመሃል ገብቶ እንዳያምሰን፣

እንዲህ አይነቱን እሳት አርቀን አይተን፣

ልናስተምረው ይገባል ቆርጠን፤

ልንገስፀው ይገባል ደፍረን።

ጥብቅ ማሳሰቢያ

በጥቂት ሰዓት ልዩነት ውስጥ ጽሑፎቼን ከተስተናገዱበት ድረ ገጾች እያደንክ በመንቀልና በማስነቀል እንዲሁም በእከክልኝ ልከክልህ የተመሰረተ ተራ ጓደኝነትና ጌዚያዊ ወዳጅነት የተነሳም ኢሳትን እንደ ታቦት አትንኩብኝ በሚል የልጅነት መንፈስ በአንዳንድ መካነ ድሮች ሥራዎቼን ላለማስተናገድ እየተደረገ ያለው ኢዲሞክራሲያዊ አካሄድና የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አፈና ውሎ አድሮ ሌላ የከፋ ችግር ይወልድ እንደሆነ እንጂ የሚመጣው መፍትሔ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። በዚህ አጋጣሚ ለኢሳት የዜናማሰራጫ ማዕከል እንደ ተቋም፣ ለድርጅቱ ቅጥረኞችም እንደ ባለሞያዎችየማስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ጉልህ የሆኑ የማዕከሉ ሕጸጾች፣ ግድፈቶችና ሆነ ተብለው የሚፈጸሙ የማሳሳት ስራዎች ሲነቃና ሲደረስበት ራስህን ከማስተካከል ይልቅ የአድማጮች አስተያየቶችእየተባለ በሚቀርበው ቅንብር ሕዝብን ማደናገር፣ ሀገርን ከመክዳትና ራስህንም ከማታለል አልፎ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልምና ከታሰበበት አሁንም ቢሆን ሀገርንና ትውልድን የሚጠቅም ስራ ለምስራት ጊዜው እንዳልመሸ ለመጠቆም እወዳለሁ።

/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

E-mail: [email protected]

Las Vegas, NV

December 16, 2012