የወያኔው ፓትሪያርክ ለሕክምና ወደ አሜሪካ አመሩ፤ ከፍተኛ አካላዊ ድካም እና የሰውነት መዛል ታይቶባቸዋል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አቡነ ማትያስ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አሜሪካ ማምራታቸውን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች ገለጹ።
ከትላንት በስቲያ፣ ሰኞ ማምሻውን ከምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ሌላ ረዳታቸው ጋር የተጓዙት ፓትርያርኩ፣ ከኹለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በሕክምና እንደሚሰነብቱ ተገልጧል።
ፓትርያርኩ በሀገር ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የጤና ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን የጠቀሱት የዜናው ምንጮች፤ የሕመማቸው መንሥኤ ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር የተያያዘ መኾኑን ጠቁመዋል።
ባለፈው ሳምንት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አኲስም ጽዮን ማርያም ካቴድራል ተገኝተው የክብረ በዓሉን ጸሎተ ቅዳሴ በመሩበት ወቅት ከባድ የሰውነት መዛል እንደታየባቸው የዜናው ምንጮች ተናግረዋል፤ ከዚያም በኋላ የሚሰማቸው ከፍተኛ አካላዊ ድካም የዕለት ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ እክል እንደፈጠረባቸውና የተሻለ ሕክምና በማስፈለጉ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን አስረድተዋል።