የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን?
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የአረቡ ዓለም የጸደይ አብዮት እ.ኤ.አ ታህሳስ18/2010 የቱኒስያን አብዮት በማቀጣጠል ይጀምራልብሎ የገመተ ማንም ሰው አልነበረም፡፡
መሐመድ ቡአዚዚ የሚባል በመንገድ ላይ እየተንቀሳቀሰለዕለት ኑሮው መደጎሚያ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘትጥቃቅን ሸቀጦችን የሚሸጥ ወጣት በከተማው ማዘጋጃ ቤትእና በፖሊሶች ኃላፊነት የጎደለው አሰራር መሰረት በዜጎችላይ እየተፈጸመ ያለውን የማሸማቀቅ፣ ከሕግ አግባብ ውጭስልጣንን የመጠቀም እና የማዋረድ ዕኩይ ድርጊቶችንበመቃወም በእራሱ ላይ እሳት በመለኮስ እራሱን በማቀጣጠል በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ላይየአብዮት ማዕበልን ያስከትላል ብሎ የገመተ ማንም ሰው አልነበረም፡፡
ለህዝቦች ነጻነት ሲል እራሱን በእሳት ያቀጣጠለው ዜጋ ዚን ኤል አቢዲን ቤን አሊን በቱኒስያ፣ ሆስኒ ሙባረክን በግብጽ፣ሙአመር ጋዳፊን በሊቢያ፣ አሊ ሳለህን በየመን እና ሌሎችንም በእሳት ተቃጥለው ዶግ አመድ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
ሶቭየት ህብረት በብርሀን ፍጥነት እና ከመቅጽበት ፍርክስክሷ ይወጣል ብሎ የገመተ ማንም አልነበረም፡፡ እ.ኤ.አ ታህሳስ25/1991 ሚካኤል ጎርባቾቭ እራሳቸውን ከፕሬዚዳንትነት ያገለሉ መሆናቸውን በማወጅ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብየገና ስጦታ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ጎርባቾቭ ለሰባት አስርት ዓመታት ያህል በሶቭየት ህብረት ውስጥ ነግሶ የቆየውንየኮሙኒስት አገዛዝ ገመድ ውጤታማ በሆነ መልኩ ስበው በጥሰው በመጣል ለዓለም ህዝብ አስደናቂነታቸውን በተግባርአስመስክረዋል፡፡
ትላንት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “በኢትዮጵያሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንደገና ሌላ ደም አፋሳሽ የኃይል ጥቃት“ በሚል ርዕስ በድረ ገጹ ላይ በመልቀቅ ህዝብእንዲያውቀው አድርጓል፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “የተማሪዎች ተቃውሞ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎችውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ ይገኛል… የማህበራዊ ድረ ገጾች በደም በተነከሩ እና በተጨማለቁ ሰላማዊሰዎች ፍቶግራፎች ተሞልተዋል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ላይ በርካታ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኞች እና በቁጥጥር ስርየዋሉ በርካታ ሰዎች የሚገኙ መሆኑን ታማዕኒነት ያላቸው ምንጮች ዘግበዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የአካባቢ ፖሊሶችእስከ አሁን ድረስ ሶስት ተማሪዎች መሞታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡“
ሂዩማን ራይትስ ዎች በአሁኑ ጊዜ በተማሪዎች እየተካሄዱ ላሉት ሰላማዊ ሰልፎች አንቀሳቃሽ ምክንያቶች ናቸውያላቸውን ጉዳዮች እንደሚከተለው አቅርቧቸዋል፡
“ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች እውነትነት ያለው በሚመስል መልኩ እና ሆኖም ግን ከጥርጣሬ ውስጥ በሚጥል መልኩየአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ወሰን ከድንበሩ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተስፋፋ በመሆኑ እና የኦሮሞን አርሶአደሮች ከመሬታቸው የሚያፈናቅል መሆኑን ከመፍራት አንጻር ነው፡፡ በርካታ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ላይ ስልጣን በያዙተከታታይ ነገስታት የማግለል አድልኦ እንደተፈጸመባቸው አድርገው ይሰማቸዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በኢትዮጵያተከታታይ መንግስታት ሁልጊዜ በመንግስት ፖሊሲዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ እንደማይችሉ እና ድምጽ እንዳይኖራቸውአድርገዋል የሚል እምነት አላቸው፡፡”
በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሀት)እንደዚህ ያለ መጥፎ ዜናን የሚያሰራጩ ዜናዎችን ወዲያውኑ ማጥፋት ተቃውሞዎችን ጸጥ ማድረግ በሚለው ስልታቸውላይ ሁልጊዜ ትክክል እና ውጤታማ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ፡፡ ሆኖም ግን ዜጎች በሰላማዊ መንገድተቃውሞዎቻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ መግለጽ እንዳይችሉ ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ ማለት ነገሮችን ከማወሳሰብ ባለፈመልኩ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች በተደጋጋሚ ለአካባቢያቸው ማህበረሰቦች ሲሉ ወደ አደባባይ በመውጣትየሚፈጽሙት እና የማያቋርጥ ትግል ስለሆነ በአንድ ወቅት እውነታው ቁልጭ ብሎ ሊወጣ ይችላል፡፡
ጥያቄው እውነታው ፍንትው ብሎ የሚወጣው መቼ ነው የሚለው ብቻ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበውዘ–ህወሀት እውነታን መያዝ ይችላል ወይ? የሚለው ነው፡፡
በእርግጠኝነት እውነታው ምንድን ነው?
እውነታው ሁሉም ሊመልሰው በሚችልበት መልኩ እንዲህ በሚሉ ጥያቄዎች ዓይነት ሊቀርብ ይችላል፡
1ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት ከ100 ሚሊዮን በላይ ቁጥር ያለውን ህዝብ የመሬት ላይ ባሮች በማድረግ እንደ ሰም አቅልጦእንደ ብረት ቀጥቅጦ የሚገዛው እስከመቼ ድረስ ነው?
2ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት እራሳቸው ጌታ እና እያንዳንዱ ዜጋ ደግሞ ገባር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ የመሬት ማሳ ላይጢሰኛ ባሮች አድርገው የሚቆዩት እስከምን ያህል ጊዜ ነው?
3ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት አርሶ አደሮችን ከእራሳቸው መሬት ላይ በማፈናቀል በድህነት አረንቋ ማዕበል ውስጥ እየዘፈቁበችጋር ሲያሰቃዩአቸው የሚኖሩት እስከ መቼ ድረስ ነው?
4ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት የመኖሪያ ቤት ያላቸውን ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው እያፈናቀሉ፣ የንግድ ስራ ባለቤቶችንከንግድ ስራዎቻቸው በግፍ እየነቀሉ እና እያባረሩ በእራሳቸው፣ በደጋፊዎቻቸው እየተኩ እና የተቀደሱትን የእምነትማደሪያ የሆኑትን ቤተክርስቲያኖችን እና መስጊዶችን እያረከሱ እና መሬቶቻቸውን እየነጠቁ የእነርሱን የማይሞላኪሳቸውን በገንዘብ ሲያጭቁ የሚኖሩት እስከ መቸ ድረስ ነው?
5ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምሮ የኢትዮጵያውያን የነበረውን በርካታ መጠን ያለውንመሬት እየነጠቁ እና እየዘረፉ ለቻይኖች፣ ለህንዶች፣ ለሳውዲዎች፣ ለቱርኮች እና ለሌሎችም የጥቅም ተጋሪዎቻቸውበቁርጥራጭ ሳንቲም እየቸበቸቡ ኪሳቸውን ሲሞሉ የሚኖሩት እስከ መቼ ድረስ ነው?
6ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ተቃውሟቸውንበሚገልጹበት ጊዜ በጥይት እየተደበደቡ የሚገደሉበት ጊዜ የሚዘልው እስከ መቼ ድረስ ነው?
7ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት የ100 ሚሊዮኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ አፍኖ ጸጥ ረጭ በማድረግ በድንቁርና አገዛዙየሚቀጥልበት እስከ መቼ ድረስ ነው?
8ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት የ100 ሚሊዮን ህዝቦችን አንገት እረግጦ የያዘውን ጫማውን ዘለቄታዊ እንዲሆን በማድረግቀጥቅጦ የሚገዛው እስከ መቼ ድረስ ነው?
እኮ እስከ መቼ?
ሩቅ አይሆንም እላለሁ!
ሩቅ አይሆንም!
አሁን እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ላይ ሆኘ ዘ–ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ መቼ እንደሚወድቅ ለመተንበይ አልችልም፡፡
ሆኖም ግን የውድቀት የእጅ ጽሁፉ በግድግዳው ላይ ነው፡፡
የዘ–ህወሀት አድራጊ እና ፈጣሪ ዘዋሪ የነበረው ከስልጣን ኮርቻው ላይ እ.ኤ.አ ነሐሴ (?) ተሽቀንጥሮ ለዘላለሙይጠፋል ብሎ ያሰበ ማንም አልነበረም፡፡
አሁንም በስልጣን ኮርቻ ዙፋኑ ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ዘ–ህወሀት ይወድቃል፡፡ ብን ብሎም ይጠፋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ መቅረብ ያለበት ጥያቄ ዘ–ህወሀት ይወድቃል ወይ የሚለው ሳይሆን መቼ ነው የሚወድቀው የሚለውነው፡፡
ይኸ አስደማሚ እና አሳሳቢ የሆነው የዘ–ህወሀት ረዥሙ የጨለማ ጉዞ የአገዛዝ ጥቄያ በጀግኖቹ ኢትዮጵያውያንእየተብላላ እና እየተሰለቀ ቆይቶ ተገቢውን ምላሽ የሚያገኘው መቼ ነው? ይህንን ጉዳይ አንድን ህጻን በዛፍ ጫፍ ላይበተሰራለት የመኝታ አልጋ ላይ መተኛት እንዲችል እንድናባብለው ከሚደረግ የዋህ ድርጊት ጋር በማመሳሰል እስቲ በዚህየግጥም ስንኝ እንቃኘው፡፡
ህጻኑን አባብለው ከዛፍ ጫፍ ይተኛ፣
በተሰራው አልጋ ለሷም ሳይሆን ለኛ፣
መጠበቅ አትችልም ከነፋስ ቀበኛ፣
ከማት ልታድነው ከኃይል ሞገደኛ፡፡
ነፋስ በሰዓቱ በነፈሰ ጊዜ፣
ቢነቃም ባይነቃም ከያዘው አባዜ፣
ወድቆ መንኮታኮት በደረሰ ጊዜ፣
ሁሉም መልክ ይይዛል የልጁ ኑዛዜ፡፡
የዛፉ ቅርንጫፍ ዘንበል ያለ እንደሆን፣
የህጻን መኝታው እንዳይሆን እንዳይሆን፣
ከመሬት ተላትሞ አፈር ትቢያ ሊሆን፣
ከማይቀረው ዓለም ምንም ጊዜ ቢሆን፣
ህጻን ተሸክሞ ያያታል ሲኦልን፡፡
አይ የህጻኑ አልጋ በዛፍ ላይ ያለኸው፣
ይህንን ሞኘ ህጻን አታለህ የያዝኸው፣
ምቹ በማስመሰል እንዲተኛ አርገኸው፣
ትንሽ እንደተኛ እውነት አልጋ መስሎት፣
ከመቅጽበት ወድቆ ከዛፉ ስር አለት፣
ሳይበቃ ቀረ አሉ ለኑዛዜ ስርየት፡፡
አወይ በሬ ሞኙ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ፣
እልም ካለው ገደል ወድቀህ ቀረኽ ወይ፣
የሚባለው ተርት ይህ አይደለም ወይ?
የህዝቡን ደስታ ያራቀ፣ ከፍተኛ የሆነ ቁጡነት እና ብስጭትን የተላበሰ ህዝባዊ ማዕበል በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እየነፈሰነው፡፡
ይህንን ህዝባዊ ማዕበል በመጋፈጥ የዘ–ህወሀት ዛፍ ታላቁ ቅርንጫፍ መቋቋም አቅቶት ተቆርጦ የሚወድቀው መቼነው?
አሁን ይህ ነው ለማለት አልችልም፡፡ ሆኖም ግን ቅርንጫፉ ተገንድሶ የመውደቂያ ጊዜው እየደረሰ ነው ለማለትእችላለሁ፡፡
ታላቁ ቅርንጫፍ ተገንድሶ ሲወድቅ ምን ይከተላል የሚለውን ጥያቄ መመለስ ቀላል ነገር ነው!
የዘ–ህወሀት ታላቁ ቅርንጫፍ ተዘንጥሎ ሲወድቅ የሙስና አገዛዝ ከነጉግ ማንጉጉ ተንኮታኩቶ ይወድቃል፣ ሰይጣናዊውአገዛዝ እና አልጋውም ሁሉም ነገር ተንኮታኩቶ ወድቆ አፈር ድሜ ይበላል፡፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ነገሮች ሁሉ ሲታዩ ሚስጥራዊ የሆነ ብሩህ ቁስ አካል በሰማይ ጨለማውን ሰንጥቆ የሚሄድመስሎ ይታያል፡፡ ምልክቱን ማየት ቀላል ነገር ነው፣ ሆኖም ግን ሁኔታውን ለማወቅ እና ግንዛቤ ለመውሰድ በጣም ከባድነገር ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት የዘ–ህወሀት የኃይል እርምጃ እና የቁጣ መንስኤ የሆኑት እና የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጣው አመጹንየቀሰቀሱት የተማሪዎች ጉዳይ ብቻ አልነበረም፡፡
በአንድ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ከፍል በአንድ እስር ቤት ላይ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከአደጋው ለማምለጥ በሚንቀሳቀሱ የህግእስረኞች ላይ የዘ–ህወሀት ታማኝ የሆኑ ፖሊሶች ተኩስ በመክፈት ግድያዎችን እንደፈጸሙ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛውአገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡ (የቪዲዮ ምስሉን ለማየት እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)
ይኸ ዕኩይ የአረመኔዎች ድርጊት እ.ኤ.አ ህዳር 2/2005 በቃሊቲ እስር ቤት ግቢ ውስጥ አሁን በህይወት በሌለውበአምባገነኑ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ታጣቂዎች ተኩስ በመከፍት በርካታ እስረኞች እንዲሞቱ እና ብርካታዎቹ ደግሞቁስለኛ እንዲሆኑ የተደረገበትን ዘግናኝ ክስተት አስታወሰኝ፡፡ (እልቂቱ የተፈጸመባቸውን እስረኞች ስም ዝርዝር ለማየትእዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)
እ.ኤ.አ ህዳር 1983 የዩኤስ አሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ኸርበርት ኢ. ሜየርየዩኤስኤስአርን/USSR መንኮታኮት ዋና ዋና ምክንያቶችን አስቀድመው በማወቅ ያቀረቡት ምልከታ እ.ኤ.አ ታህሳስ2015 እየተከሰተ ካለው እውነታ ጋር ልዩ የሆነ መስተጋብር እና ጠቀሜታ አለው የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሜየር ሁሉም ነገር በራሽያ የቁጥጥር አስተዳደር ምክንያት አንድም ብሄራዊ የሆነ ድርጅት ደስ ተሰኝቶ በማይኖርበትሁኔታ ዩኤስኤስአር ፍጹም በሆነ መልኩ ተንኮታኩታ ትወድቃለች የሚል ጽሁፍ በማዘጋጀት የክርክር ጭብጣቸውንአቅርበው ነበር፡፡
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተስማሚ የሆነ የምጣኔ ሀብት እና የስነ ተዋልዶ ሁኔታዎች በሌሉበት እና በማይኖሩበት መንገድየዓለም የመጨረሻዋ ግዛት የሆነችው ሀገር ህልውና ሊኖራት እንደማይችል አረጋግጠዋል፡፡
ሜየር እንዲህ በማለት አውጀው ነበር፣ “የሶቭየት የምጣኔ ሀብት ወደ አደገኛ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብቷል፡፡“ ከዚህምበተጨማሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሶቭየት ዩኒየን የስነ ተዋልዶ ቅዠት ነው፡፡“
ሜየር እንዲህ የሚል የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተው ነበር፣ “የሶቭየት አመራር አስፈላጊ የሆኑትን ለውጦች ለማምጣትወይም ደግሞ እነዚህን ሁኔታዎች ለመመለስ የሚያስችል ወይም መፍትሄ በመስጠት ከነገሮች ጋር አብሮ ለመሄድየሚያስችል ድርጊት ሊያከናውን አይችልም፡፡“
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 እኔም እንደዚሁ በኢትዮጵያ ላይ ተመሳሳይ የሆነ የክርክር ጭብጤን አቀርባለሁ፡፡
ኢትዮጵያ በፖለቲካ ቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብታለች፣
ኢትዮጵያ በዘ–ህወሀት የአገዛዝ ስርዓት ውስጥ እንደ ሀገር የመቀጠሏ ሁኔታ ፍጹም በሆነ መልኩ ወድቆ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ዘ–ህወሀት በብችኝነት ህዝቡን በጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት ውስጥ እጅ ከወርች በመጠፍነግተቆጣጥሮ ይዞት ባለበት ሁኔታ የትኛውም ትልቅ ብሄራዊ የሆነ የፖለቲካ ቡድን ደስ ብሎት ሊኖር አይችልም፡፡
ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የዘ–ህወሀት የእራሱን የአገዛዝ ስርዓት እና ስልጣን ለማጠናከር ሲል የጎሳ ፌዴራሊዝም አባዜንእና በፖለቲካ የከፋፍለህ ግዛን ፖሊሲ በማራመድ ተግባራት ላይ ሲውተረተር ይገኛል፡፡ ዘ–ህወሀት በስልጣን እርካብላይ ተፈናጥጦ ለመኖር እንዲመቸው የፍርሀት፣ የጥልቅ ጥላቻ እና በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱን ጎሳ ከሌላው ጋር በማናቆርዕኩይ እስትራቴጂ ነድፎ በመተግበር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡
እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ የዘ–ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካዊ የፖለቲካ ቅሬታላላቸው ቡድኖች እና ግለሰቦች በትክክለኛው የፌዴራሊዝም አወቃቀር መስፈርት መሰረት እራሳቸውን በእራሳቸውማስተዳደር እንዲችሉ የፈቀደ በማስመሰል የህዝብ ንብረት የሆነውን መሬቱን ለባዕዳን እየሸጠ እና ሌላውንም የሀገሪቱንአንጡራ ሀብት እየመዘበረ ኪሱን በዶላር በማጨቅ ላይ ይገኛል፡፡
የዘ–ህወሀት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ ተገልለው ለቆዩት ብሄረሰቦች የጎሳ ፌዴራሊዝም ሀውልት በማቆምበአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ የጎሳ ፌዴራሊዝም ሰፍኗል በማለት ዘ–ህወሀት እራሱን የበላይ ጠባቂ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ፍጹም የሆነ ሸፍጥ!
ላለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት ዘ–ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም የመጫወቻ ኳስ በማዘጋጀት አንዱን የጎሳ ቡድን ከሌላኛውየጎሳ ቡድን ጋር እያጋጨ ሀገሪቱን በትክክል ባልታሰበበት ሁኔታ ከፍሎ እና ሸንሽኖ ህዝቦችን በኃይማኖት እየለያየእያጋጨ እያተራመሰ ከፋፍሎ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡
ላለፈው ሩብ ምዕት ዓመት ዘ–ህወሀት ለጥቅም የሚገዙ የይስሙላ የፖቲካ ፓርቲዎችን በማቋቋም አስመሳይነት የሸፍጥጨዋታ ሲጫወት ቆይቷል፡፡ እራሱን የኢትዮጵይያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ብሎበመጥራት የዘ–ህወሀትን የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች (ጅቦች አላልኩም) የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጠብቁ በመምሰልእየገደሉት እና እያሰቃዩት ይገኛሉ፡፡
ዘ–ህወሀት የጎሳ ታማኝነትን እያዘጋጀ እና የጎሳ ፍርሀትን እና ጥልቅ ጥላቻን እያራመደ ሲያካሂድ የነበረው የሸፍጥጨዋታ ከእንግዲህ ወዲያ የሚቀጥል አይሆንም፡፡
በአሁኑ ጊዜ ያለው እውነታ ዘ–ህወሀት በኢትዮጵያ በሚገኝ በእያንዳንዱ የጎሳ ቡድን እየተጣለ ነው ያለው፣ ምንም ደጋፊየለውም!
የማስመሰል ጨዋታው ተጠናቅቋል፣ እናም ይህንን ጉዳይ ዘ–ህወሀት በሚገባ ተገንዝቦታል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ከሩብ ምዕተ ዓመታት በኋላ በዘ–ህወሀት አማካይነት ለእራሱ የተፈጠረለትን የጎሳ ክፍፍልእያንዳንዳቸውን ምንም ዓይነት ጥቅም የማያገኙበት እና በዘለቄታዊነት ዘ–ህወሀት ብቻ አሸናፊ ሆኖ ተጠቃሚየሆነበትን ስርዓት አንድ በአንድ ተገንዝበውታል፡፡
ዘ–ህወሀት የእራሱን ፍላጎት ፍጹም በሆነ መልኩ በህዝቦች ጫንቃ ላይ እየጣለ ያለው ሁኔታ ሊያሰኬደው እንዳልቻለከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገነዘበው መጥቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ተማሪዎች እና ወጣቶች ለሀገሪቱ ጥቅም እና ነጻነታቸውን ለማስከበር ወደፊት ገፍተው በመሄድ ላይ ናቸው፡፡
ሆኖም ግን እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዋናው የግድብ ውኃ አንዲት ጠብታ ብቻ ናቸው፡፡ ዘ–ህወሀት የሌባ ጣቱንወደ ንጹሀን ዜጎች ላይ በመቀሰር እና የተማሪዎችን ተቃውሞ በግድያ በመጨፍለቅ ሊያስቆመው እንደሚችል አድርጎያስባል፡፡
ዘ–ህወሀት ያልተገነዘበው ጉዳይ ቢኖር እያንዳንዷ የተማሪዎች ቅሬታ ተሰባስባ ህዝባዊ በሆነ ቁጣ፣ ማዕበል፣ ጥላቻ እናመቃቃርን ፈጥራ ወደ ግብዓተ መሬቱ የሚያደርሰው መሆኑን ነው፡፡
የዘ–ህወሀት ትልቁ ቅርንጫፍ በሚገነደስበት ጊዜ የጎሳ ፌዴራሊዝም አልጋ ተንኮታኩቶ ይወድቃል፣ እናም ዘ–ህወሀትወደ ታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ ይወረወራል፡፡
የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋች የስራ ጌቶች ዘ–ህወሀት እ.ኤአ. ግንቦት 2015 ምርጫውን መቶ በመቶአሸነፊያለሁ ብሎ ካወጀ በኋላ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና ላይ በመገስገስ ላይ ናት በማለት እየነገሩን ይገኛሉ፡፡
ባራክ ኦባም ቢሆን የአእምሮ ክህሎታችንን በሚፈታተን መልኩ በመዘለፍ ይህንን ቡድን እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015ተቀላቅሏል፡፡ አስመሳዩ ፕሬዚዳንት ተብዬ እንዲህ ብሏል፣ “እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 በተካሄደው ምርጫ ዘ–ህወሀትመቶ በመቶ ያሸነፈበት ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡“ ባራክ ኦባማ ስለኢትዮጵያ እውነት እንዲናገር ነግሬው ነበር፡፡ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ስለኢራቅ የጦር እልቂት አምጭ መሳሪያዎች የፈጠጠ ውሸት ዋሽቷል፡፡ ባራክ ኦባማ ስለዘ–ህወሀትሀሳብን የማስቀየሻ የውሸት የምርጫ ውጤት ሙልጭ አድርጎ ዋሽቷል፡፡
ኢትዮጵያ በማህበራዊ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ወድቃለች፣
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንገብጋቢው ጥያቄ ረኃብ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አበ2016 የመጀመሪያው ግማሽ በኢትዮጵያ ቢያንስ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለረኃብ እንደሚጋለጡ ይፋ አድርጓል፡፡
ዘ–ህወሀት ከዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች እና ከአበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመሆኑ በአሁኑ ጊዜበሀገሪቱ ውስጥ ተከስቶ ህዝቡን በችጋር እየጠበሰ እና እልቂትን እየፈጸመ ያለውን የረሀብ ቀውስ ከምንም ባለመቁጠርረኃብ በሀገሪቱ ውስጥ በፍጹም የለም፣ አለ እንኳ ቢባል የሚኖረው የምግብ ዋስትና እጦት እና የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገርእጥረት እጦት ነው እያሉ የሚጠሩት ነው በማለት የፕሬስ መግለጫዎችን ሁሉ አጨናንቀው ይገኛሉ፡፡
ዘ–ህወሀት የሚጠቀምበት አዲሱ ፋሽን ደግሞ ረኃቡን ያመጣው ኤል ኒኖ እየተባለ የሚጠራው ፍጡር ነው በማለትከደሙ ንጹህ ነን በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ ረኃቡን በየጊዜው የሚያመጣው እና የሚፈጥረው ብልሹ አስተዳደራቸው እናየማይለወጠው ገታራው ፖሊሲያቸው መሆኑን ለአምዲትም ሰከንድ ቢሆን ማመን አይፈልጉም፡፡ ምክንያቱ የተግምባርድሁሮች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በምሁራን እና በባለሙያዎች የሚሰጥን ማንኛውንም ዓይነት አዎንታዊ ምክረ ሀሳብአእምሯው ሊቀበል አይችልምና ነው፡፡ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም የሚባለው ዓይነት ነገር መሆኑ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት የቪኦኤ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት በድርቅ በተመቱ አካባቢዎች በመገኘት ለአርሶ አደሮች ቃለመጠይቆችን በማካሄድ የሚከተሉትን ዘገባዎች በመግለጫ መልክ አቅርቧል፡
“ሰዎች ስለረኃቡ እና ስላለባቸው መከራ እንዲናገሩ አይፈቀድም፡፡ እነርሱ (ዘ–ህወሀት ማለታቸው ነው) ስለረኃቡያለውን መረጃ ሁሉ ይደብቃሉ፡፡ ስለዚህ ነገር አንድም ነገር መናገር አይፈልጉም፡፡ ስለረኃቡ ሲናገር የተገኘ ሰው የነፍስማጥፋት ወንጀል እንደፈጸመ ወንጀለኛ እኩል ጥፋተኛ ተብሎ ይፈረጃል፡፡ ስለረኃቡ መናገር ወንጀል ነው፡፡ ስለረኃቡየሚናገሩ ሰዎችን ያስራሉ፡፡ ሰዎችን ይደበድባሉ፡፡ ሰዎችን ያስፈራራሉ፡፡ ሰዎች ተርበዋል፡፡ በእርግጠኝነት ተርበዋል፡፡በርካታ የሆኑ ሰዎች ምንም ዓይነት የሚላስም ሆነ የሚቀመስ ነገር የላቸውም፡፡ ከ4-5 የሚሆኑ የበቆሎ ራሶች 10 ብርያወጣሉ…“
ዘ–ህወሀት እና ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች የረኃቡን እውነተኛ ገጽታ ለመደበቅ ከሚል ዕኩይ ምግባር ባዶየፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማራመድ ስራ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ እናም እስከ ጥርሳቸው ድረስ በዋሹ ቁጥር በሚሊዮኖችየሚቆጠሩ ወገኖቻችን በረኃብ የሞት ነጣቂ ተኩላ ይነጠቃሉ፡፡
ዘ–ህወሀት “ረ“ ሀብ የምትለዋን ፊደል በፍጹም መጠቀም አይፈልግም፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 2008 አሁን በህይወት የሌለው የዘ–ህወሀት አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ ለታይም መጽሔት እንዲህየሚል ቃለ ምልልስ ሰጥቶ ነበር፣ “በኢትዮጵያ የረኃብ አደጋ ለበርካታ ጊዚያት ሲከሰት ቆይቷል፡፡ እንዲህ ዓይነት አደጋሲከሰት ለጉዳዩ ትኩረት የማያደርግ ደደብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በእኛ ሁኔታ ምንም ዓይነት ረኃብ የለም – የአስቸኳይ ጊዜብቻ ነው፡፡ ረኃብ በፍጹም የለም…በአንዳንድ አካባቢዎች በአንዳንድ ኪስ ቦታዎች የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረትብቻ ነው ያለው“ በማለት በድፍረት በቅጥፈት ተናግሯል፡፡
ዘ–ህወሀት እና የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች 15 ሚሊዮን የሚሆነውን ህዝብ የረኃብ ሰለባ ያደረገውንየረኃብ አደጋ እንደዚህ ባለ አሳፋሪ የቃላት እና የሀረጎች አጠቃቀም በመሸፋፈን ያለው የምግብ እጥረት፣ የምግብክፍተት፣ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ የምግብ ዋስትና እጦት እና በኤል ኒኖ ድርቅ ምክንያት የተከሰተ የግብርናምርት እጥረት እና በመሳሰሉት ነው በማለት የቅጥፈት ልብስ ለማልበስ ይሞክራሉ፡፡
አሁን በቅርብ ጊዜ ያለው ጥረት ደግሞ የኢትዮጵያን ረኃብ “የስነ ምግብ ቀውስ” እያሉ የሚጠሩበት አካሄድ ነው፡፡ አዎ፣“የስነምግብ ቀውስ”ይሉታል ፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 2015 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ጽ/ቤት እንዲህ በማለት አስጠንቅቋል፣“በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠናከረ ምላሽ እስካልቀረበ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት እና የስነምግብቀውስ ሊከሰት ይችላል፡፡“
ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች “ረ“/”F) የምትለዋን ፊደል ለማስወገድ ሲባል የእንግሊዝኛን ቋንቋ እያሰቃዩእንዳሉ ስነገነዘብ ምን ያህል የወረዱ ፍጡሮች እንደሆኑ እንገነዘባለን! ያም ሆነ ይህ ምን ዓይነት የውሸት የማጭበርበርአነጋገር ነው እባካችሁ?
በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳተኝነት እና በሚሊዮኖች ለሚሆኑ ሰዎች ደግሞለመፈናቀል የሚያበቁነው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሜን ጨምሮ “የተፈጥሮ አደጋ” ሲባል ሰምቻለሁ፡፡
ምግብ በማያገኙ ሰዎች ላይ የሚከሰተው “የስነምግብ ቀውስ” አደጋ በተመሳሳይ መልኩ እንደ ተፈጥሮ አደጋ እኩልተደርጎ ሊቆጠር ይችላል ለማለት ነዉን?
ወደኋላ መለስ ብለን ስንመለከተው “የስነምግብ ቀውስ” አደጋ ረኃብ ተብሎ የሚጠራውን ነገር ለመጥራትየሚጠቀሙበት ሐረግ ነው፡፡
ቢቢሲ ብቻ ነው ረኃበን ረኃብ ብሎ በመጥራት ድፍረት ያለው፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ምጣኔ ሀብት ቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብታለች፣
ውሸቶች፣ ተራ ቅጥፈቶች እና የሀሰት የቁጥር ድርደራ ጨዋታዎች በዓለም ባንክ፣ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እናበዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ እና በሁሉም የአውሮፓ እና አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶችአማካይነት የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት 11 በመቶ (ይቅርታ የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ህዳር 2014 ባወጣው ዘገባውየኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ዕድገት 10.9 በመቶ ይል ነበር) የምጣኔ ሀብት ዕድገት ባለፉት አስር ዓመታት ዕድገትአስመዝግቧል በማለት የሚዘግቡ ቢሆንም የምጣኔ ሀብቱ በአሁኑ ጊዜ በአስከፊ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብቶ ይገኛል፡፡
ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች ሁሉም ኢትዮጵያውን ከአለት በበለጠ መልኩ የደደቡ ናቸው ብለውእራሳቸውን የሚያሳምኑበትን እውነታ እገነዘባለሁ፡፡
የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት በፍጥነት እያደገ ያለ እና በዓለም ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገትን ከሚያስመዘግቡ ሀገሮችመካከል አንዱ ነው በማለት ሌት ከቀን እንደበቀቀን እየደጋገሙ ውሸትን በመዋሸት የኢትዮጵን ህዝብ እና የዓለም አቀፉንማህበረሰብ ለማሳመን ቅጥፈትን ከቶ ሲያራምዱ የሚውሉት ለምንድን ነው?
ላለፉት አምስት ዓመታት የኦክስፎርድ የድህነት እና የሰው ኃይል ልማት ተነሳሽነት ዘርፈ ብዙ የድህነት አመልካቾች/Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHDI) Multidimensional Poverty Index ባወጣው የድህነት እና የሰው ኃይል ልማት መለኪያ መስፈርትመሰረት ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ በፕላኔቷ ውስጥ ካሉ ሀገሮች በሙሉ በድህነት በሁለተኛ ደረጃላይ የተቀመጠች መሆኗን ይፋ አድርጓል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የዓለም ባንክ ባወጣው ዘገባ መሰረት በአጠቃላይ በአገልግሎት እና በግብርና ዘርፉ ላይ ትኩረትባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ አስደናቂ የሆነ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗን እንዲህ በማለት ይፋአድርጓል፡
“የግብርና የምርት ውጤቶች ዕድገት ሊመዘገብ የቻለው የግብርናውን ምርታማነት በማሳደግ እና ሊታረስ የሚችለውንየመሬት መጠን በመጨመር ነው፡፡ ለግብርናው ምርት ማደግ እንደ ዋና ዋና ነገሮች ሊቆጠሩ የሚችሉት የኤክስቴንሽንአገልግሎት እና ለአርሶ አደሮች ስልጠና መሰጠት በመቻሉ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ እየተመዘገበ ያለው የግብርና ምርት ዕድገትበዋናነት መንግስት በኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ በመንገዶች ግንባታ እና በትምህርት ላይ ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ንዋይበማፍሰሱ እንደዚሁም ደግሞ ምቹ የሆኑ የዋጋ ማበረታቻዎችን ማድረግ በመቻሉ ነው“ ብሏል፡፡
አንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያችሁ የግብርናውን ምርታማነት በማሳደግ እና ሊታረስ የሚችለውን የመሬት መጠንበመጨመር መንግስት እያደረገ ባለው ከፍተኛ ጥረት እ.ኤ.አ በ2015 የግብርና ምርት ዕድገትን ሳይሆን ረኃብንለማምረት ቻለ ማለት ነው፡፡ የሚታየው እውነታ ይኸ እና ይኸ ብቻ ነው መቀነስም መጨመርም የሚቻል ነገር ሊሆንአይችልም፡፡
የዘ–ህወሀት መሪዎች ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከቻይና እርጥባን በመለመን እና ለማኝ መንግስት በመሆንእራሳቸውን በስልጣን ላይ እንደ መዥገር አጣብቀው መቆየት እንደሚችሉ አድርገው ያስባሉ፡፡
እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ከለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በምጽዋት ከሚያገኘው እርጥባን ውጭ ለአንድምቀን ቢሆን በስልጣን ላይ ሊቆይ አይችልም፡፡
ታዋቂ የሆነችው አፍሪካዊት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና የሙት እርዳታ/Dead Aid መጽሐፍ ደራሲ ዳምቢሳ ሞዮየኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ሁኔታ በማስመልከት እንዲህ ብላለች፣ “በኢትዮጵያ 97 በመቶ የሚሆነው ግዙፍየመንግስት በጀት የሚገኘው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡“ በእርዳታ እና በብድር እስትንፋስ ህይወት ዘርቶ ስለሚንቀሳቀስአገዛዝ ከዚህ በላይ ምን ማለት ይቻላል?
በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባውን ጠቃሚ ነገር ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተባለው ዓለም አቀፍድርጅት እንዲህ በማለት አስቀምጦታል፣ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ተግጠዋል፡፡ ፍጹም ከሆነእጦት እና ድህነት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት በከፍተኛ ሁኔታ ትግል የሚያደርጉ ቢሆንም ቅሉ በሕገ ወጥ የገንዘብዝውውር ምክንያት በወንዙ ውስጥ ወደ ላይ በመዋኘት ላይ ይገኛሉ“ በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ እንግዲህ የዘ–ህወሀት ጉድ “ወደ ታች ነው እንጅ ውኃ አወራረዱ ሽቅብ ሽቅብ አለኝ እኔንስ ለጉዱ” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በስነ ህዝብ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብታለች፣
የዘ–ህወሀት መሪዎች ባለፈው አስርት ዓመታት ውስጥ 10.9 በመቶ ዓማካይ አመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገትአስመዝግባለች በማለት ሁልጊዜ ያናፋሉ፡፡ (እንደ አህያ “ያናፋሉ” አላልኩም።)
ሆኖም ግን የዘ–ህወሀት መሪዎች ለመናገር የሚጠሉት 3 በመቶን ሊዘል ትንሽ ስለሚቀረው እና የኢትዮጵን ህዝቦችህልውና ስለሚፈታተነው ልቅ የተደረገ የስነ ህዝብ መጣኔ ጉዳይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት ለበርካታ አስርት ዓመታት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ አገዛዙ እንደ አንድኃላፊነት እንደሚሰማው ቡድን እንኳ ስለ ስነህዝቡ ሁኔታ አንድም ትንፍሽ የሚለው ነገር የለም፡፡ በሙስና መብከት እናመበስበስ እንጅ ይህ ነገር ለእርሱ ጉዳዩ አይደለምና፡፡
እ.ኤ.አ በ1967 የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 23.5 ሚሊዮን ነበር፡፡
አ.ኤ.አ በ1990 ወደ 51 ሚሊዮን ከፍ አለ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ በ2003 68 ሚሊዮን ደረሰ፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 የህዝቡ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመምጣት 80 ሚሊዮን ደረሰ፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 የዩኤስ አሜሪካ የስነ ህዝብ ቆጠራ ቢሮ በሰጠው ግምት መሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 91 ሚሊዮንደረሰ፡፡
እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ አማካይ ዓመታዊ የህዝብ ዕድገት መጣኔ ከ3 በመቶ በላይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ይኸ ነገር እንዴት ነው የሚል እና ኃላፊነት የሚሰማው አካል ጠፍቷል፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 የዩኤስ አሜሪካ የስነ ህዝብ ቆጠራ ቢሮ ስለኢትዮያ ህዝብ ብዛት በጣም አስፈሪ የሆነ ትንበያ በመስጠትእ.ኤ.አ በ2050 በወቅቱ ካለበት የህዝብ ቁጥር በሶስት ጊዜ እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን ይደርሳል ብሏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2025 ማለትም ከዛሬ አስር ዓመታት በኋላ የዩኤስ አሜሪካ የስነ ህዝብ ቆጠራ ቢሮው በሰጠው ትንበያመሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 131 ሚሊዮን ይደርሳል ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ 99 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ መመገብ አትችልም፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 ደግሞ 87 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2006 78 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡
እንደዚሁም ሁሉ እ.ኤ.አ በ1984 40 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ1974 32 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2025 ኢትዮጵያ 131 ሚሊዮን ህዝቦቿን ለመመገብ ምን ያህል ገሀነም እንደሚሆንባት ልናስበውእንችላለን?
ኢትዮጵያ ወደፊት የምግቡ ደረጃ ካለበት የእድገት መጠን ጋር ሊሄድ የሚችል የስነ ህዝብ ዕድገት እንዲኖራት ለማስቻልየህዝቡን የዕድገት ሁኔታ ከምጣኔ ሀብት ዕድገቱ ጋር ለማመጣን እንዲቻል የማልተስ እልቂት ወደሚባለው የተቃወሰየህልወት እርምጃ (ማለትም በሽታ፣ ረኃብ፣ ጦርነት፣ ወዘተ የመሳሰሉት ነገሮች የህዝቡን ቁጥር ይቀንሱታል) በማለትዝም ብሎ በግዴለሽነት የማየት ሁኔታ የሚታይ ይመስላል፡፡
በአንድ ወቅት አሁን በህይወት ለሌለው ለአምባገነኑ የዘ–ህወሀት መሪ በይስሙላ ፓርላማ ተብየው የስነ ህዝብ ጉዳይንየሚመለከት ጥያቄ ቀርቦለት የሚወለደው ሰው ሆድ ብቻ ሳይሆን የሚሰሩ እጆች ጭምር ይዞ ነው የሚመጣው የሚልምላሽ በመስጠት ተሳልቆ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ እንግዲህ ይኸ የሚያሳየው ሰውየው ስለ ስነህዝብ ጉዳይ ምንነትምንም ነገር እወቀቱ የሌለው መሆኑን እና እርሱ የሚመራው መንግስት ስለዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ምንም ዓይነት እርምጃለመውሰድ ክህሎቱ የሌለው መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያመላክታል፡፡ እንደ እርሱ አባባል ቢታይ እንኳ የኢትዮጵያ ህዝብበየጊዜው ለረኃብ ሰለባ የሚጋለጠው የሚወለዱት ህጻነት ሆድ ብቻ ይዘው የሚመጡ እንጅ የሚሰሩ እጆች የሌሏቸውስለሆኑ ይሆን?
እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘ–ህወሀት መሪ መለስ ዜናዊ እራሱን ከፍ ከፍበሚያደርግ መልኩ እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “ትርፍ ምርት ለማምረት የሚያስችለንን ስትራቴጂ ቀይሰናል፣ እናምእ.ኤ.አ በ2015 ከውጭ ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ ሳይደረግልን እራሳችንን መመገብ እንችላለን“ ብሎ ነበር፡፡ከዚህም በተጨማሪ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ከተባበሩት መንግስታት የሚሊኒየም የልማት ግቦች ጋር በሚመሳሰል መልኩእ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ፍጹም ድህነት በ50 በመቶ ከአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጦት ጋር ይቀንሳል“ ብሎ ነበር፡፡ምን ዓይነት ዲያብሎሳዊ ውሸት ነው!
ዘ–ህወሀት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ኢትዮጵያን ህዝብ ዕድገት ለመቆጣጠር የሚያስችል እና 15 ሚሊዮኑንህዝብ ከአሰቃቂ ረኃብ ለማዳን ወይም ደግሞ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ምንም ዓይነት ዕቅድም ሆነ ፕሮግራምየለውም፡፡
ዘ–ህወሀት እራሱ ወደ ቀውስ ቅርቃር ውስጥ እየገባ ነው፣
ዘ–ህወሀት አስተማማኝ የሆነ ወታደራዊ ኃይል አለኝ፣ በውሸት ላይ የተፈበረከ የምጣኔ ሀብት ስኬት አለኝ፣ በሀገሪቱውስጥ አስተማማኝ የፖለቲካ መረጋጋት አለ፣ ወዘተ በማለት በእራሱ የቅጥፈት ትረካ እራሱን ሕጋዊ አስመስሎ ለማቅረብሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ዘ–ህወሀት እና ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋች ግብረ አበሮቹ መልካም እና ጥሩ ስም ያለው እያስመሰሉበማቅረብ ስለምጣኔ ሀብቱ ዕድገት የሀሰት የቁጥር አሀዞችን በመደርደር የነቀዘ እና የበከተ ገጽታውን ለመደበቅ በመሞከርላይ ይገኛሉ፡፡
ዘ–ህወሀት የኃይል እና የጭቆና አገዛዙን ለማስቀጠል የመጨረሻውን አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ለህዝብ ለማሳየትበዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ሆኖም ግን ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ከዚህ በኋላ “አንዲት ጋት ወደ ኋላ አናፈገፍግም” በማለት በጽናት የተሞላስሜቱን በማሳየት ላይ ይገኛል!
እውነታውን ሙልጭ አድርጎ መካድ የአምባገነኖች ሁሉ መለያ ባህሪ ነው፡፡ ዘ–ህወሀት ለዚህ የተለዬ ብችኛ ሊሆንአይችልም፡፡
ለሁሉም አምባገነኖች የማይቀየሩ ዘላለማዊ እውነታዎች አሉ የምንል ከሆነ እምባገነኖች ሆን ብለው እያወቁ ደንቆሮዎች፣እውሮች እና ዱዳዎች ናቸው፡፡
ለህዝቦች ጩኸቶች እና እንባዎች ሆን ብለው ጆሮ ዳባ ልበስ የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
ስለደኃ ህዝቦች መሰቃየት፣ ለድርቅ አደጋ ሰለባ ለሆኑ እና አቅም ለሌላቸው ሁሉ አላየሁም በማለት አድፍጠውይቀመጣሉ፡፡
መከራን የሚገፉ ህዝቦችን ለይቶ በማውጣት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ከችግሮቻቸው ለማውጣት ባለመቻልዱዳ ሆነው በመቀመጥ ይመለከታሉ፡፡
ህዝቡ እነርሱን የሚወዳቸው ለመሆኑ ሌላ ማንንም ሶስተኛ ወገን ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን በእራሳቸው ያሳምናሉ፡፡
በማስመሰያው የቅርጫ ምርጫ ከህዝቡ መቶ በመቶ ድምጽ ያገኙ በመሆናቸው እና በዚህም መሰረት ስልጣን እንደያዙአድርገው የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳመን ይሞክራሉ፡፡
እነርሱ እብዶች ናቸው፡፡ ልክ እንዳበደ ቀበሮ፣ እውነታው ይኸው ነው፡፡
እ.ኤ.አ የካቲት 2011 የሊቢያ ህዝባዊ አብዮት እየተቀጣጠለ ባለበት ሁኔታ አምባገነኑ ሙአማር ጋዳፊ ለዓለም አቀፉማህበረሰብ እንዲህ የሚል ቱልቱላውን ነፍቶ ነበር፣ “ህዝቡ እኔን ይወደኛል፡፡ ሁሉም ህዝቦች ከእኔ ጋር ናቸው፣ እናምይወዱኛል፡፡ የእኔ ህዝቦች እኔን ለመጠበቅ ሲሉ ይሞቱልኛል“ ነበር ያለው፡፡
እርሱን ከስልጣኑ ላይ ለማስወገድ የሚታገሉ የነጻነት ኃይሎችን “አይጦች እና በረሮዎች” በማለት ነበር የጠራቸው፡፡እራሱን የንጉሶች ሁሉ ንጉስ በማድረግ በቆሻሻ መውረጃ ፉካ ውስጥ የህይወቱ እስትንፋስ እስከምታልፍ ድረስ ሊቢያንእስከሚሞት ድረስ የመግዛት መብት እንዳለው አድርጎ ነበር የሚያምነው፡፡ በሊቢያ ውስጥ እራሱን ለ42 ዓመታት ያህልአምላክ አድርጎ የሚቆጥር አምባገነን በወሮበላ የዘራፊ ዓይነት አሟሟት ዓይነት ወደማይቀረው ዓለም በውርደትተሰናበተ፡፡
በመጨራሻዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተቃራኒው ዕጣ ፈንታ አሸናፊ ሆኖ የገዳፊ ዕድል በምታዘቀዝቅበት ጊዜ ጋዳፊ ተቃዋሚታጋዮቹ ምህረት እንዲያደርጉለት ፍትህን ጠየቀ፡፡ እንደ ቆሻሻ አይጥ ተስቦ እና እንደበረሮ በኃይል ተደልዞ ምህረትእየጠየቀ ከፉካው ውስጥ በመውጣት እንዲህ አለ፡ “አትግደሉኝ!“
ከአምባገነኑ ሳዳም ሁሴን በፊት የጣሊያን ፋሽሽት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ እንዲህ በማለት ጉራውን ቸርችሮ ነበር፣“በእያንዳንዷ የልቤ ምት ሁሉ ለጣሊያን ህዝብ አገልግሎት እሰጣለሁ፡፡ በመሆኑም ሁሉም ጣሊያናዊ እኔንእንደሚወደኝ እና እንደሚረዳኝ ይሰማኛል፡፡“
የኡጋንዳ ህዝብ አራጅ የሆነው ኢዲ አሚን ዳዳ እንዲህ የሚል አነስተኛ የሆነ ስሜታዊነትን አንጸባርቆ ነበር፣ “ህዝቦችመሪያቸውን መውደድ አለባቸው!“ ይህንን የማያደርጉ ከሆነ መሪያቸውን እንዲወዱ የሚያደርግባቸው ጠንካራ የሆኑየእራሱ መሳሪያዎች በመጠቀም ስራውን ይሰራል፡፡
የዛየሩ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ በጸጥታ ቀስ ብሎ በመሳቅ ለውጭ ግንነት አድራጊዎቹ ሲናገር ህዝብ እርሱን ስለሚወደው ህዝቡእርሱን መውደድ ብቻ አይደለም እንዲያውም በስልጣኑ ላይ እንዲቆይ ይፈልጋል በማለት ባዶ ጉዳውን ሲቸረችርነበር፡፡
ደም መጣጩ ወታደራዊ አምባገነን መንግስቱ ኃይለማርያም ከአርበኝነት እና ከሀገር ወዳድነት የይስሙላ ማታለያተልዕኮው አንጻር ህዝቡን እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ብረት ቀጥቅጦ የመግዛት ዓላማ ነበረው፡፡ እርግጥ ነው መንግስቱለድፍን 17 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውንን በገፍ እንደ ቄራ ሰንጋ እያረደ ሲገድል የቆየ ስለነበር እንደእርሱ እምነት ያለምንም ጥርጥር ሀገር ወዳድ ነው፡፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 አሁን በህይወት የሌለው የአፍሪካው ልዩ የሆነው ወሮባለ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያህዝብ የእርሱን ወሮበላ ፓርቲ እና በውስጠ ታዋቂነት ደግሞ የእርሱን የፓርቲ መሪነት በመውደዱ ምክንያት 99.6በመቶ የህዝብ ደጋፍ በማግኘት ምርጫውን አሸንፈናል በማለት የሸፍጥ እና የቅጥፈት ቱሪናፋውን ዘረገፈ፡፡ ህዝቡእነርሱን እና ኢህዴግን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው እናም ምንም ዓይነት ኃይል የእርሱን ድርጅትሊነቀንቀው እንደማይችል በእብሪት አፉን ሞልቶ ተናግሯል፡፡ ህዝቡ የእርሱን ፓርቲ በመምረጥ ላሳየው መልካም የህሊናዳኝነት እና ፍትሀዊነት ከልብ እንደሚያመሰግን እና የህዝቡን ይሁንታ በካርዳቸው እንደሰጡት በማድረግ የድርቅናቅጥፈቱን በአደባባይ አሰራጭቷል፡፡
በመጨረሻም የዘ–ህወሀት ችግር በነብሩ ጀርባ ላይ ወጥቶ እንደሚጋልበው ነብር ጋላቢ ሁሉ ለመውረድ አስፈሪ ሆኖየመገኘቱ ሁኔታ እየተባለ እንደሚነገረው ተረት ነው፡፡ ለድፍን 25 ዓመታት ዘ–ህወሀት የነብሩን ጭራ ይዞ ለመልቀቅእየፈራ በመወራጨት ላይ ያለ የዕኩዮች ስብስብ ነው፡፡
መሄድ እንዲችሉ ልቀቋቸው፡፡ ለመሄድ እንዲችሉ ፍቀዱላቸው፡፡
ነብር ጋላቢው ለበርካታ ጊዜ በመጋለቡ ምክንያት ታምሟል እናም በጣም ድካም ይዞታል፡፡ ዘ–ህወሀት ከስልጣን እርካብላይ እንዲወርድ በሚገደድበት ጊዜ በፈጣጣዎቹ ዓይኑ አፍጥጦ ይመለከታል፣ ጥርሶቹን ያንገጫግጫል፣ እናምየተንጨፈረሩ ጥፍሮቹን ይሰነዝራል!
በጋንዲ የተነገሩትን እንዲህ የሚሉትን ዘላለማዊ እውነታዎች ዘ–ህወሀት እንዲያስብበት እነግረዋለሁ፡ “በታሪክ ሂደትሁሉም የእውነት እና የፍቅር መንገዶች ያሸንፋሉ፡፡ አምባገነኖች እና ገዳዮች ለጊዜው የማይበገሩ አሸናፊዎች መስለውይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜ ይወድቃሉ፡፡ ይህንን ነገር አስቡት ። ሁልጊዜ ይወድቃሉ፡፡“
ዘ–ህወሀት ከዚህ ዘላለማዊ እውነታ ሊያመልጥ አይችልም፡፡
የድሀረ ዘ–ህወሀት ኢትዮጵያ፣
በዘ–ህወሀት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ እና ከምንም አድልኦ በጸዳ መልኩ፣ በሰለጠነ አኳኋን፣ በጓዳዊነት፣ ቅንነትንበተላበሰ መልኩ የእራሴን ምልከታ ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
እውነቱን እንዳየሁት፣ አብሬው እንደኖርኩት፣ እንደሚሰማኝ፣ እንዳሰብኩት፣ እንደተገነዘብኩት አድርጌ አቀርባለሁ፡፡
ለኢትዮጵያውያን ድምጽ የለሾች፣ ኃይል የለሾች እና ለተስፋ የለሾቸ እናገርላቸዋለሁ፡፡ አዎ፣ እራሴን በእራሴ ሾሚያለሁ፣ሆኖም ግን ጥልቅ በሆነ መከባበር እና አገልግሎት ላይ በተመሰረተ መልኩ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በዘ–ህወሀት ከተፈጠረው የሌሊት ቅዠት ሊወጣ የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡
ዘ–ህወሀት ያንን መንገድ አይጠቀምበትም፡፡
የዘ–ህወሀት አመራር እንደሞተው የሶቪዬት አመራር ሁሉ ያሉትን የጥፋት አደጋዎች ወይም ባሉበት መፍትሄ ለመስጠትእና ለውጥ ለማምጣት ሊሰራ አይችልም፡፡
ሆኖም ግን የመውጫ መንገዱ አለ፡፡
ስለውይይት መድረክ ነው፣ ስለጽኑ አርበኝነት መንገድ ነው፣ ስለማህበረሰቡ የማሰብ መንገድ ነው፣ ስለ መንፈሳዊህይወት የማሰብ መንገድ ነው፡፡
ወደ ብርሀን ወይም ደግሞ ቀጣይነት ወዳለው ጨለማ ውስጥ ስለመግባት መንገድ ነው፡፡
ስለሆነም ለእኛ በመስታወቱ ላይ የተጻፈልን ጥያቄ እና ለዘ–ህወሀት፣ ለደጋፊዎቹ እና ለግብረ አበሮቹ በግድግዳው ላይየተጻፈላቸው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፡ “ዘ–ህወሀት በሚወድቅበት ጊዜ ምን መደረግ አለበት?“
ለዘ–ህወሀት መልሱ ቀላል ነው፡፡ ተመትተው፣ እየጮኹ እና እያከኩ ወደ ታሪክ የቆሻሻ ማስቀመጫቸው ይሄዳሉ፡፡
ለእኔ የድህረ ዘ–ህወሀት ኢትዮጵያ የሸክስፒርን ጣያቄዎች ያቀርባል፡፡
ለጋራ ዕድል መተባበር ወይም አለመተባበር ያ ነው ጥያቄው፡፡
በዘ–ህወሀት የጋህነም መንገድ ላይ መጓዝ መቀጠል እና እራስን ወደ ገደል አፋፍ ላይ ወስዶ መጣል የሚለው ሌላውጥያቄ ነው፡፡
እኔ በዘ–ህወሀት ወዳጅ አይደለሁም ፡፡ (እሺ፣ ለቧልት ያህል ነው ያልኩት፡፡)
ዘ–ህወሀት እራሱን ከመጥፋት ለማዳን ቀደም ሲል ያወደማትን ኢትዮጵያን መጠበቅ መቻል ይኖርበታል የሚል እምነትአለኝ፡፡
እራሱን ለማዳን ዘ–ህወሀት እስከ ዛሬ ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በጎሳ ፌዴራሊዝም ስም ሲገነባው የቆየውን የጥላቻንግድግዳ የግርዶሽ ግንብ መናድ አለበት፡፡
ዘ–ህወሀት ለዓመታት የገነባው የጥላቻ ግንብ በእራሱ ላይ ከመደርመሱ በፊት የጥላቻን ግንብ ቀድሞ ማፍረስ እናማስወገድ ይኖርበታል እላለሁ፡፡
ዘ–ህወሀት ከጀርባ የእናንተ አመራር፣ ግብረ አበሮች እና ደጋፊዎች ያሉበትን በግድግዳው ላይ የተጻፈውን የእጅ ጽሁፍማንበብ ይኖርባችኋል እላለሁ፡፡
ዘ–ህወሀት ኢትዮጵያውንን እንደ በረት ከብት በነገድ፣ በጎሳ፣ በኃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በመደብ ወዘተ በመከፋፈልበገነባችሁት የክልል ግንብ ላይ የተጻፈውን የእጅ ጽሁፍ ማንሳት ይኖርባችኋል እላለሁ፡፡
ዘ–ህወሀት ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳትገናኙ ከቪላችሁ ጀርባ የገነባችሁትን ግንብ እና እስር ቤት ላይየጻፋችሁትን የእጅ ጽሁፍ አንብቡት እላችኋለሁ፡፡
ዘ–ህወሀት ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በገነባችሁት የጥላቻ ግንብ ላይየጻፋችሁትን የእጅ ጽሁፍ አንብቡት እላችኋለሁ፡፡
የዘ–ህወሀት አመራሮች የጥላቻ ግንብ በእራሳችሁ ላይ ከመናዱ በፊት እራሱን የጥላቻን ግንብ አስቀድማችሁ ናዱትእላችኋለሁ፡፡
ምናልባትም በመጽሐፍ ቅዱስ የአቀራረብ ዘይቤ ዘ–ህወሀትን (አሕዛቦቹን አላልኩም) ለመስበክ እችላለሁ፡፡
የኢያሪኮ ከተማ ግንቦች በጣም ጠንካሮች፣ ኃይለኛ ምሽጎች እና ለመስበርም የማይሞከሩ ነበሩ፡፡ የኢያሪኮን ግንብ መስበርየሚችል ምንም ዓይነት ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል አልነበረም፡፡
ሆኖም ግን ህዝቡ የኢያሪኮን ግንብ ለመስበር የወታደር ኃይል አላስተባበረም ነበር፡፡ ህዝቡ ጸጥታን በተላበሰ መልኩ ቀስብሎ ለስድስት ቀናት በመጓዝ ወደ ግንቡ ተቃረበ፡፡ በሰባተኛው ቀን ህዝቡ ኾ ብሎ ጮኸ፡፡ የኢያሪኮ ግንብ ወዲያውኑፈረሰ፡፡
የዘ–ህወሀት ግንብ በወታደራዊ ኃይል አይፈርስም፡፡ የጦር እና አውዳሚ መሳሪያዎችን በገፍ እና በብዙ ቁጥር በህዝብሀብት እየገዛ አከማችቷል፡፡ የአውዳሚ እና የጦር መሳሪያዎችን ከቻይና፣ ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ወይም ኬሎችምከሚፈልጋቸው ሀገሮች ወሰን በሌለው መጠን አከማችቷል፡፡
ህዝቡ አንድ ሆኖ ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ “አምባገነናዊ አገዛዝ በቃን! ስልጣንን ከሕግ አግባብውጭ መጠቀም ይብቃ! ሙስና ይብቃ! የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይቁም! በቃ በቃ ነው!“ በማለት በአንድ ድምጽሲጮህ የዘ–ህወሀት ግንብ እሳት እንዳልነካው ሸክላ ፍርክስክስ ብሎ ይወድቃል፡፡
የዘ–ህወሀት ግንብ ህዝቦች ስለ ዘ–ህወሀት ስያቅለሸላቸው አና ሲያስታዉካቸው ዘ–ህወሀት ይወድቃል ይደረመሳል፡፡
ዘ–ህወሀት ይወድቃል ምክንያቱም ዘ–ህወሀት የኢትዮጵያን ህዝቦች አእምሮ እና ልብ ሊቆጣጠር አልቻለምና፡፡
በወታደራዊ ኃይል ማቋረጫ የሌለው ጽናት ሊኖር አይችልም፡፡ ለረዥም ጊዜ ለጭቆና ተዳርጎ የቆየን የህዝብ ቁጣ እናብስጭት እንደዚሁም ሁሉ በየዕለቱ ክብሩን አጥቶ በውርደት ተዘፍቆ ኑሮን በመግፋት ላይ ያለን ህዝብ ማቆምየሚያስችል በምንም ዓይነት መንገድ በመሬት ላይ የሚገኝ ምድራዊ ወታደራዊ ኃይል ሊኖር አይችልም፡፡
የአንድ ሀገር እውነተኛ ጥንካሬዋ፣ የአንድ ሀገር መንግስት እውነተኛ ጥንካሬው የሚለካው የአንድን ሀገር ህዝብ አእምሮእና ልብ መቆጣጠር ሲችል ነው፡፡
የወደፊቷ ኢትዮጵያ አሁን በሚደረጉ ድርጊቶች፣ በማይደረጉ ድርጊቶች ወይም ደግሞ በዘ–ህወሀት ምላሾች ወይምበእርሱ ግብረ አበሮች ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡
የወደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት የምታደርገው የወጣት ህዝቧን አእምሮ እና ልብ በመቆጣጠር እና ለሀገራቸው ባላቸውፍቅር፣ በህዝቡ፣ ህዝቡ እራሱን ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት፣ ወንድሞቹን እና እህቶቹን ከገቡበት አዘቅት ውስጥመንጥቆ የማውጣት ፍላጎት ሲኖረው እና ከድህነት ብቻ ሳይሆን ከሞራል ስብዕና ኪሳራ ጭምር ነጻ ማድረግ ሲችልነው፡፡
ዘ–ህወሀት ይህንን ያልኩትን ሁሉ ማድረግ ከቻለ የሚፈራውን ቀውስ ማስወገድ ይችላል፡፡
እኩልነትን በማረጋገጥ፣ አንድነትን በማራመድ፣ ወንድማማችነትን በማጠናከር፣ የስልጡንነት አካሄዶችን በመተግበር እናጨካኝነትን በማስወገድ፣ አረመኔያዊነትን እና ጭራቃዊነትን በማጥፋት የጥፋት ቀውስን ማስወገድ እችላለሁ፡፡
ዘ–ህወሀት ፍትህን በማስፈን፣ ፍትሀዊነትን በማስተማር፣ እውነተኛው ነገር እንዲሰራ በማደፋፈር፣ በተጠያቂነት ላይአጠንክሮ በመስራት፣ የጭካኔ ድርጊቶችን ከመፈጸም ይልቅ አዲስ የፈጠራ ባህልን በማዳበር እና በመጠቀም፣ ችግሮችንሰላማዊ በሆነ መንገድበመፍታት፣ ፍቅርን በማሳየት፣ ልግስናን በመውደድ፣ በሰለጠነ መልኩ በመንቀሳቀስ፣ ቅዱስ የሆኑሀሳቦችን በመከተል፣ በታማኝነት እና ክብርን በጠበቀ መልኩ በመራመድ የህዝቦችን አእምሮ እና ልብ መቆጣጠርይችላል፡፡
ሆኖም ግን ዘ–ህወሀት የኢትዮጵያን ወጣቶች አእምሮ እና ልብ ለመያዝ እና ለማሸነፍ ያለችው ጊዜ በጣም ትንሽ ናት፡፡(70 በመቶ የሚሸፍነውን በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ትኩረት በማድረጌ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡)
ምናልባትም ዘ–ህወሀት ከተለያዩ ዘመናት በርካታ የሆኑ ሰብአዊ መከራዎችን ከተቀበለው እና የእነርሱ ቅርብ ጓደኛእንዲህ በማለት የጠቀሰው መልዕክት የበለጠ ግልጽ ሊያደርግላቸው ይችላል፡ “አስቀድሞ ወጣቱን የያዘ የወደፊቱንመጻኢ ዕድል ይቆጣጠራል፡፡“
ይቀጥላል…
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ህዳር 28 ቀን 2008 ዓ.ም