ማን ይሆን ወሬኛው!?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከሳምሶን

ዛሬ ደግሞ “ትግል ወሬ አደለም” አሉን

ማን ይሆን ወሬኛው!!!?
ማነው ያሰለቸን!?
ባልጨበጥነው ተስፋ በማይዳሰሰው፤
ታጋዩን በሙሉ ጠቅልሎ ያስመረቀው፤
በለቅሶው ጋጋታ መስኮቱን የሞላው።

የትኛው ሰው ይሆን አንድ ጠጠር ወርውሮ፤
ከወሬ ያለፈ ስንዝር ተጠናክሮ፤
አባይን ተከዜን ባሮን ተሸጋግሮ፤
ላፍታ እንኳን ለሴኮንድ መንደር አሸብሮ፤
እንባውን ያበሰ ያስቆመው ለቅሶውን የህዝቡን እሮሮ።

ኧረ…! ኧረ…! ኧረ አልበዛም እንዴ!?
በባጥ የቆጥ ጦማር፤ እውነት በሚመስል፤
የዋሁን ንፁሁን፣ በነፃነት ጥማት የተንገላታውን፤
ባደባባይ ሰብኮ፤
ባደባባይ ዋሽቶ፤
ባደባባይ ቀጥፎ፤
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል፤ የሚለውን ብሂል እንደሌለን ሁሉ፤ በውሸት ተራሮች እውነትን ለማራቅ፤
በከንቱ ልፈፋ እውነትን መጋረድ እንደሚቻል ሁሉ፤ ከህዝብ ለመደበቅ….፤

ቀባጥሮ…. ቀባጥሮ…. ቀባጥሮ….
ትላንት በህዝብ ፊት እንደዛ እንዳላለን!!!

አንድ አመት አይፈጅም፤ ኧረ እዛም አይደርስም!!!
የወያኔን ስልጣን ማስወገጃ ውሉ ቁልፉን አግኝተነዋል።
ኧረ ችግር የለም አያሳስበንም!
ባንድ ጀምበር ደምስሰን አመድ ልናረገው ዝግጅቱ አልቋል።

እኛ ተስፈኞቹ ያንን ሁሉ ውሸት አምነን እንዳልነበር፤
ቀኑ ሲያልፍ ደግሞ፤ ቃላቸው ሲሰበር፤ ሌላ ተስፋ ሰንቀን፤
ባላየ ባልሰማ የይቅርታውን ጐርፍ በምላሹ ሰጥተን፤
በማያልቅ ቅጥፈቱ ሪፊል ለመደረግ ዝግጁ በሆንን!?
ደግሞ ደጋግሞ ሲዋሽ በትዝብት ዝም ባልን!?
ላለመጠላለፍ በትግስት ባለፍን!?

ምን አስቦ ይሆን!!!?
ምንስ ሰርቶ ኖሮ!!!?
ከወሬ በስተቀር፤ አብሮ ከማላዘን፤ ሙሾውን ደርድሮ።
መሬት ላይ ጠብ የሚል አንዳችም ሳይኖረው፤
ዛሬም ባደባባይ በለመደው መስኮት ቅጥፍ ያደረገው።

ምን የሚሉት ይሆን እንዲህ ፖለቲካ!?
ፋይዳ ለሌለው ቅጥፈት ሚያነካካ!?
ኧረ ተማር በሉት!?
የ21ኛው ዘመን እንደሆነ ከገባው አስረዱት!?
ከርሱ ባዶወሬ ህዝቡ እጅግ መጥቋል፤ ብላችሁ ንገሩት!?