” የትናንቱ ህወሓት ዛሬ የለችም ነገም አትመጣም ” – የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ነበር ተኽለብርሃን አርአያ
ነባር ታጋዩ በፓርቲው ውስጥ ከማእከላይ ኮሚቴ እስከ ቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ለዓመታት በኃላፊነት ነበሩ።
ሐቀኛ ፣ ከሙስናና አድሎአዊ አሰራር የፀዱ ናቸው ተብለው በትግል ጎዶቻቸው የሚወደሱት ታጋዩ ከሁለት ዓመታት በፊት የተካሄደውንና የህወሓትን አመራር ለሁለት ቡድን ከፍሎ ክፉኛ ያዳከመው 14ኛ ጉባኤ ህገ-ወጥ ነው ብለው በመቋወም ፓርቲውንና ስልጣናቸውን ለቀዋል።
ታጋይ ተኽለብርሃን አርአያ ጥር 6/2018 Landa Report ከተባለ ሚድያ ጋር ህወሓትን አስመልክተው በሰጡት ከአንድ ሰዓት በላይ ርዝማኔ ባለው ቃለ-መጠይቅ ምን አሉ ?
– ህወሓት በተለይ ከ1993 ዓ.ም የመሪነት መከፋፈል ወዲህ የዓላማ ጥራት ችግር ያጋጠመውና መዳከም የጀመረ ነው።
– ላለፉት 25 ዓመታት ሰብአዊ ሀብቱ ( Social capital ) የበተነ ፓርቲ ነው።
– አመራር እና አባሉ በኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና መዘፈቅ ከጀመረ ቆይቷል።
– አዲስ ተተኪ ሀሳብ የሌለው ፤ በኔትወርክና ጥቅም የተሳሰረ ልል መሪነት ነው ያለው።
– የአሁኑ ህወሓት ስትራቴጂክ አመራር የለውም።
– ስትራቴጂክ አመራር የሌለው ፓርቲ ደሞ ፓርቲ ሆኖ አይቀጥልም።
– የግል ጥቅም እንጂ የአላማ አንድነት ያላሰባሰበው አመራር ቡድኖች እየፈጠረ አንዱ ሌላውን እያሳደደ እየበላ ፓርቲውን ወደ ማይድንበት ደረጃ አድርሶታል።
– ለ60 ቀናት ተሰብስበው ከመጨቃጨቅ ባሻገር የፈጠሩት የአስተሳሰብና የአመራር አንድነት አልነበረም።
– በመጨረሻ አንዱ ቡድን ሌላውን ቡድን ገፍትሮ ነሀሴ 2016 ዓ.ም ቁጥጥር ኮሚሽን ያልደገፈውና ያልተቀበለው ጉባኤ አካሄደ።
– ጉባኤው ህወሓት ወደ አራት ቡድን መከፋፈል ያዋለደ ነው።
– አንዱ ቡድን ስምረት ሌላው ወለዶ የሚባሉ ፓርቲዎች መስርቷል ፤ የተቀሩት ህወሓት ነን የሚሉት ደግሞ ለሁለት ቡድን ተከፍለው ውስጥ ለውስጥ እየተባሉ ነው።
– ደብረፅዮንና ጌታቸው ህወሓት በማዳከም ታሪክ ይጠይቃቸዋል።
– የትናንቱ ህወሓት ዛሬ የለችም ነገም አትመጣም።
– ዛሬ ያለው ህወሓት ስርዓትና መርህ አልባ ነው።
– ለአሁኑ መድረክ የሚዋጅ ህወሓት የለም።
– ስለ ግሉ ጥቅሙ እንጂ ስለ ህወሓት ጥንካሬ የሚጨነቅ አመራር የለም።
ትግራይ እንዴት ነው መዳን ያለባት ?
– የአሁኑ አጀንዳ ትግራይ እንዴት መዳን አለባት እንጂ ፤ ህወሓት እንዴት መዳን አለበት አይደለም መሆን የሚገባው።
– ውይይትን እና ስርዓት ማስቀደምን ያስፈልጋል።
– የተለያዩ አመለካከቶች የሚያስተናግድ አቋፊ መንግስት ማቋቋም ያስፈልጋል።
– የፓለቲካ የስህበት ማእከሉ ፓርቲዎች ሳይሆን መንግስት ስለ ማጠንከር መሆን አለበት።
– ምርጫ መካሄድና አለማካሄድ የህዝብ እንጂ የፓርቲዎች መብት አይደለም።
– ህዝብ ለምርጫ ይዘጋጃል ፓርቲዎች የሚያወዳድራቸው ሀሳብና እጩ ያቀርባሉ።
– እኔ የሌለሁበት ምርጫ አይካሄድም የሚለው አይሰራም።
– ለምርጫ ምቹና አስቻይ ሁኔታ መፈጠር አለበት።
– ትግራይ በህዘብ ምርጫ የቆመ ስቪል መንግስትና አስተዳደር ያስፈልጋታል።