የአብይ አገዛዝ ገንዘብ ስለሌለው ስንዴ ከውጪ ገዝቶ ማስገባት ስለማይችል የተፈበረከች ዜና ተሰራጭታለች ። የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት፣ ኢትዮጵያ ከ2013 ዓ፣ም ጀምሮ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ማቆሟን በምግብ ራስን መቻልን አስመልክቶ ባወጣው ዝርዝር መረጃ አስታውቋል።
በአውሮፓዊያኑ 2023/24 አገሪቱ 23 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ማምረቷን የገለጠው ጽሕፈት ቤቱ፣ በቀደመው 2022/23 ደሞ 15 ነጥብ 1 ሚሊዮን ቶን ስንዴ አምርታ እንደነበር ጠቅሷል።
ጽሕፈት ቤቱ፣ መንግሥት ስትራቴጂክ ትኩረቱን በምግብ ዋስትና ላይ ማድረጉ፣ አገሪቱ ከስንዴ ገዢነት ራስን ወደመቻል አሸጋግሯታል ብሏል።
ኾኖም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ረድኤት ድርጅቶች፣ ስንዴ ከውጭ ገበያ ገዝተው የሚያስገቡበት ኹኔታ ሊቀጥል እንደሚችል ጽሕፈት ቤቱ ጠቁሟል።
አገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን እንድትችል ካስቻሉ ርምጃዎች መካከል፣ የመስኖ ስንዴ ልማት መጀመሩ፣ የግብርና ማሺነሪዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱና የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሻሻሉ ይገኙበታል ተብሏል። አገዛዙ ገንዘብ ስላሌለው ያሰራጨው መረጃ ነው።