በጅማ ዞን በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ተሰደዱ፣ መኖርያ ቤታቸው ተቃጠለ
(በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ ቀበሌ ቦሬ ከተማ በሚገኙ ከሺህ በላይ በሆኑ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ባነጣጠር ጥቃት መኖርያ ቤቶቻቸው እንዲሁም የንግድ ሱቆቻቸውን ጨምሮ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ለማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ በስልክ ተናግረዋል፡፡
የጥቃቱ መነሻ ምን እንደሆነ እስከ አሁን በትክክል አልታወቀም፡፡
ጥቃቱ በትናንትናው ዕለት የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተተኮሰ ጥይት የተጀመረ ሲሆን በቀበሌው የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ ስጋት ላይ ናቸው ተብሏል።
ጉዳዩን ለማረጋጋት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሥፍራው ቢገኙም ጥቃቱ እስከ አሁን እንዳልቆመና ወደ ሌላ ቀበሌ እየተዛወረ ነው ተብሏል።
የአካባቢው ነዋሪዎችም ጥቃቱን ሸሽተው ወደ አጎራባች የደቡብ ክልሎች እየሄዱ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡ (የዜናው ምንጭ Mahibere Kidusan Broadcast Service – ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው። )