አንድ የአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) ላይ የጣለውን እርዳታ የመስጠት እገዳ በጊዜያዊነት እንዲያነሳ ትናንት ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአሜሪካ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ፍርድ ቤቱ፣ በቀድሞው የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር የሥልጣን ዘመን ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በተለያዩ አገራት ለገባባቸው የእርዳታ ውሎችና ስምምነቶች ያቋረጠውን ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ እንዲቀጥል ማዘዙን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር፣ የድርጅቱ ሠራተኞችና ከድርጅቱ የገንዘብ እርዳታ የተቀበሉ የፕሮጀክት ፈጻሚ ድርጅቶች ሥራ እንዲያቆሙ ተጨማሪ ትዕዛዞችን ማስተላለፍ እንዲያቆምም ፍርድ ቤቱ አሳስቧል።
የፕሬዝዳንቱ የእርዳታ እገዳ እንዲነሳ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት፣ በጤና ዙሪያ የሚሠሩ ኹለት ድርጅቶች ናቸው።