የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለባለስልጣናቱ ግድያ ኃላፊነቱን ወሰደ

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ከትናንት ወዲያ በመፈጸመው ጥቃት የወረዳውን የብልጽግና ፓርቲ አመራርና የወረዳ አስተዳዳሪ መግደሉን አረጋግጧል።

የቡድኑ ታጣቂዎች፣ የወረዳውን የጸጥታ ሃላፊና አብረዋቸው የነበሩ ሌሎች ግለሰቦችን እንዲኹም በርካታ የመንግሥት ታጣቂ ኃይል አባላትን መማረካቸውንም ቡድኑ ገልጧል።

ቡድኑ በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት የሱሉልታ ወረዳ አስተዳዳሪ አበበ ወርቁን መግደሉን በዕለቱ መዘገቧ ይታወሳል።

የቡድኑ ታጣቂዎች ከትናንት ወዲያ በምሥራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር መጋጨታቸውንና ጉዳት ማድረሳቸውንም ቡድኑ ባሠራጨው መረጃ ላይ ጠቅሷል።