በስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ የጠላት ብልፅግና ወታደርን ወሽመጥ በመቁረጥ ውጤታማ ድል ተመዘገበ!

በስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ የጠላት ብልፅግና ወታደርን ወሽመጥ በመቁረጥ ውጤታማ ድል ተመዘገበ!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ  አማራ ኮር 1   ባለሽርጡ ክፍለጦር ላይ ጥቅታ ለማድረስ ከጉቢሳ  ወደ ኮለቦ፣ ከጭሰ አባሊማ ወደ ሲልኮ፣ከጊራና ወደ ጉባ ፣ከመርሳ ወደ ሀብሩና ፋጂ የተንቀሳቀሰው የጠላትን ሀይል  በቀን 26/05/2018 ከኮለቦና ሩጋ ያለውን የጠላት ሀይል ስቦ በማስገባት መነዮ ቀሊና ላይ ምሽት 1:30 ላይ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።

የባለሽርጡ ክፍለጦርን ሊያጠቃና የክፍለጦሩን ነባር ይዞታዎች ሊወር የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በአምስት አቅጣጫ ለማፈን ቢሞክርም የጠላትን የጥፋት እቅድ ቅዠት በማድረግ 50 ሙትና 78 ቁስለኛ በማድረግ ከትላንት  ከጥዋቱ 12:30 እስከ ዛሬ 27/05/2018 ዓ.ም በቆየ አውደ ውጊያ የጠላትን ከበባ ያለምንም መስዋዕትነት በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌና በሌሎች በሳል የክፍለጦሩ ወታደራዊ ጠበብቶች  በመስበር በጥላት ላይ ከፍተኛ ስብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

በዚህ አውደ ውጊያ የተበሳጨው የጠላት ሀይል በደቡብ ወሎ ዞን ተወለደሬ ወረዳ ሲልኮ እየተባለ በሚጠራው ቦታ 450 የሚደርሱ ወጣቶችን፣ አርሶ አደሮችን እና የቀን ሰራተኛዎችን በማፈን ስልጠና ሰልጥናችሁ አገራችሁን ትጠብቃላችሁ በሚል ሰበብ ወደ ማጓሪያ ቀጠና አስገብቶ  ፋኖን ማረኩ በሚል የሀሰት ዶክመንተሪ ዝግጂት ላይ ይገኛል።
በተያያዘም በሀይል ላፈናቸው ንፁሀን በየቤቱ እየገባ የግል ታጣቂ ግለሰቦችን መሳሪያ ለማስወረድ ድንገተኛ ፍተሻና ድብደባ እያካሄደ ይገኛል።

©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ