ገዱ እና ደመቀን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ወደ ኤርትራ ልኬያለሁ ( አብይ አሕመድ )

በርካታ ሰዎች ወደ ኤርትራ ልኬያለሁ።የሚሉት አብይ አሕመድ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ሆነው በፓርላማቸው ተከስተዋል።

የላኳቸው ሰዎች ገሚሱ አሁን ከኛ ጋር የሉም። ለምሳሌ ክቡር አቶ ገዱ ያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ። ከአንዴም ሁለቴ ኤርትራ ልኬያቸዋለሁ። የላኳቸው የትግራይ ህዝቤን አታጎሳቁሉ፣ ሀብቱን አትዝረፉ፣ ጸቡ ከTPLF እንጅ ከትግራይ ህዝብ አይደለም በሚል ነው (ይህን መልዕክት ለኤርትራ እንዲያሳውቁ ማለታቸው ነው)።

አቶ ገዱ አሁን እኛ ጋ የሉም። ግን ክር/ማተብ አላቸው፤ ህሊና አላቸው። ዛሬ ቢደብቁ በታሪክ ውስጥ ይወጣል። ስለምን ጉዳይ እንደተነጋገሩ እሳቸውም ያውቃሉ፤ ሻዕቢያም ያውቃል፤ እኛም እናውቃለን። አሉ አልሞቱም። እሳቸው (ገዱ) Access ይደረጋሉ ሊናገሩ ይችላሉ።

ጉዳዩ በእሳቸው መፈታት ሲያቅተው አቶ ደመቀን ልኬያለሁ። አቶ ደመቀ አሁንም እኛ ጋ የሉም፤ በህይወት ስላሉ ለእምነታቸው ለህሊናቸው ሊጠየቁ ይችላሉ። ለምን ጉዳይ እንደሄዱ ያውቃሉ።

ታስታውሱ ከሆነ መቐለ ልንገባ ትንሽ ሲቀረን የሦስት ቀን ‘አልቲማተም’ ብለን አውጀን ነበር። ብዙው ምስጢሩ አልገባውም።

የቸገረን እኛ ሽሬን ስንለቅ ከኋላ ይገባሉ። አክሱም ስንለቅ ከኋላ ይገባሉ። መቐሌ ስንገባ ደግሞ ገብተው ትልቁን ከተማ Damage ያደርጋሉ ብለን፥ ካሁን በኋላ ከውቅሮ እናልፋለን ብትሉ ወያኔን ትተን ወደእናንተ ነው የምንዞረው በውጊያው ብለን ውቅሮ ላይ የሚጠብቅ ኃይል አስቀምጠን ነው መቐሌ የገባነው።

ይሄ ጸብ ተፋፍሞ ሄዶ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሲፈረም ‘ እንዴት TPLF ሳይጠፋ፣ ትግራይ ሳይወድም ፊርማ ይደረጋል ? ‘ በሚል ነው የመጨረሻ ጫፍ የደረሰው ጸቡ። ከዚህ ኃይል ጋር ነው እንግዲህ ያኔ የTPLF ሰዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንስራ ያሉት።

የትግራይ ህዝብን የሚጎዳ እና የሚጠቅም ነገር ይሄ መንግስት ነው የሰራው ወይስ TPLF? (ሁሉም TPLF ላይሆን ይችላል፤ አክራሪ TPLF በሚል ይውሰድ) ማነው? የሚለው ዛሬ ብዙ Emotion፣ ብዙ ፕሮፓጋንዳ፣ ብዙ ውሸት ስላለ ነው፤ ነገ ግን ታሪክ ያወጣዋል።

ማንም ሰው እውነትን ለጊዜው መሸፈን እንጅ ከነአካቴው ማጥፋት አይችልም። እኛ መጨረሻ ፕሪቶሪያ ስንፈራረም መቐለ ለመግባት አንድ ቀን ነበር የቀረን፤ አሸንፈናል ጦርነቱን። ሲሉ አብይ አሕመድ የውሸት ዶፍ በፓርላማው አዝንበዋል።