የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፖሊስ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ለውጥ አደርጓል።
አዲሱ ሰሌዳ ይፋ የማድረግ ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በዋና መሥሪያ ቤቱ ከቀኑ 8፡00 ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፥ አዲሱ ሰሌካ ከዚህ በፊት የነበረውን የተዘበራረቀና ወጥነት የሌለው የሰሌዳ አጠቃቀም ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው ብሏል።
ሰሌዳው በፖሊስ ተሽከርካሪዎች አማካኝነት ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ጥሰት እንዳይፈፀም በተሟላ መልኩ ለመቆጣጠር የሚያስችል እንደሆነ ገልጿል።
” አዲሱ ሰሌዳ ዝም ብሎ ቀለምና ቁጥር ብቻ የተቀየረ አይደለም ” ያለው ፌዴራል ፖሊስ ” ከዘመናዊ የዲጂታል የመረጃ ቋት (Database) ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለአሠራርና ለቁጥጥር ቀላል ያደርገዋል ” ሲል አሳውቋል።
ከዚህም ባሻገር ሰሌዳዎቹ በህገወጥ መንገድ የማይባዙ ከፍተኛ ሰኩሪቲ ያላቸው እና የደኅንነት መጠበቂያ ምስጢራዊ መለያዎች ያሏቸው መሆኑ ለየትኛውም የማጭበርበር ስራ ተጋላጭ እንዳልሆኑ ገልጿል።
አዲስ የሰሌዳ ስርዓት የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ ለመከታተል እንደሚረዳ ተመላክቷል። ይህም የወንጀል መከላከል ኦፕሬሽናል ስራዎችን በተፋጠነ፣ ፖሊሳዊ ስነምግባርን በተከተለ መንገድ መካሄዱን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ብሎም አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ይረዳል ብሏል።