ከባሕርዳር ከተማ አፍንጫ ስር በአገዛዙ ወታደሮች ላይ የተፈፀመው ደፈጣ ጥቃትና የተገኘው ድል!
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ስር ከሚገኘው 22ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አባላት በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደራዊ ኃይል ላይ ሊመከት የማይችል የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል መቀዳጀታቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደራዊ ኃይል ላይ ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ጥር 25/2018 ዓ/ም ከእኩለ ቀን በኋላ ሲሆን፡ በዚህም የጠላት ኃይል ከባድ የሆነ እልቂትን ተከናንቧል።
የአገዛዙ ወታደሮች ዙ23ና ሌሎች ከባባድ መሣሪያዎችን ታጥቀው ወታደራዊ ሬሽን በማጀብ ከባሕር ዳር ጭንባ እያጓጓዙ እንዳለ ነው ጥቃቱ የተፈፀመባቸው።
ባሕርዳር አፍንጫ ስር ይጎዲ ቀበሌ አቅራቢያ ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲደርሱ የቦምብ ውርጅብኝ የወረደባቸው የአገዛዙ ወታደሮ፡ በዚህም በርካታ ጓዶቻቸው ሙትና ቁስለኛ እንደተደረጉባቸው መረብ ሚዲያ ከ22ኛ ክ/ጦር ለማረጋገጥ ችሏል።
ከጥቃቱ የተረፈው የአገዛዙ ኃይል ሙትና ቁስለኛውን በተሽከርካሪ ጭኖ ወደ ባሕርዳር ከተማ በመሸሽ ላይ እንዳለ “የእናንተ ልጆች ናቸው የመቱን” በሚል ንፁኋኖችን መደብደቡ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የጦር ተንታኞች፡ አማራዊ የጦር ብልሀትን ከሽምቅ ሣይንስ ጋር የዋሃደ ነው ባሉት በዚህ ደፈጣ ጥቃት፡ የፋኖ አቅም ምን ያህል ጠንካራና በትንሽ የሰው ኃይል ትላልቅ ግዳጆችን በስኬት የሚወጣ መሆኑን ያስመሰከረ ነው ያሉ ሲሆን፡ በአነፃሩ ደግሞ የአገዛዙ ኃይል የሚሰነዘርበትን ጥቃት ተከላክሎ እራሱን ማዳን የማይችልበት ደረጃ ላይ መድሱን በገሀድ አሳይቷል ብለዋል።