ከባሕርዳር ከተማ በቅርብ ርቀት በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት መድረሱ ተነገረ!
ጥቃቱ የተፈፀመው ወታደራዊ ሬሽን አጅበው ከባህር ዳር ጭንባ እየተንቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የጦር ተንታኞች፡ አማራዊ የጦር ብልሀትን ከሽምቅ ሣይንስ ጋር የዋሃደ ነው ባሉት በዚህ ደፈጣ ጥቃት፡ የፋኖ አቅም ምን ያህል ጠንካራና በትንሽ የሰው ኃይል ትላልቅ ግዳጆችን በስኬት የሚወጣ መሆኑን ያስመሰከረ ነው ያሉ ሲሆን፡ በአነፃሩ ደግሞ የአገዛዙ ኃይል የሚሰነዘርበትን ጥቃት ተከላክሎ እራሱን ማዳን የማይችልበት ደረጃ ላይ መድሱን በገሀድ አሳይቷል ብለዋል።