የደቡብ ወሎ ዞን ኮማንድ ፖስት በንፁኋኖች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ስለመወሰኑ መረጃው አፈትልኮ ወጣ!
የደቡብ ወሎ ዞን ኮማንድ ፖስት አመራሮች በመካነሰላም ከተማ ባካሄዱት ሚስጥራዊ ስብሰባ ከወትሮው በባሰና ተከታታይነት ባለው መልኩ በንፁኋኖች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ስለመወሰናቸው ለመረብ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመላክታል።
ይህም፡ ሕዝቡ በሚፈፀምበት ጥቃት ተማሮ ጦርነቱን አስቁሙልኝ በሚል እንዲጠይቅና ፋኖንም በአደባባይ ወጥቶ እንዲያወግዝ ያስችልልናል በሚል ነው ውሳኔውን ያስተላለፉት ብለዋል ምንጮቻችን።
አገዛዙ ጦርነቱ የተራዘመብኝ ሕዝቡ ለፋኖ ደጀን በመሆኑ ነው ብሎ ያምናል።
በአንድም በሌላም መንገድ በሕዝቡ ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት ተባብሶ እንዲቀጥል በማድረግ፡ ሕዝቡ በመሰላቸት ለፋኖ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆምና ጦርነቱ እንዲቆም ተማፅኖ እንዲያቀርብ ለማድረግ አገዛዙ እንደ አማራጭ እየተጠቀመው የሚገኘው አካሄድ ነው።
ወዲህ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጥላቻ እና ቂም የሚወጣበት መንገድ ሆኖ አግኝቶታል።
ስለሆነም ከወደ ፋኖ የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ሲያቅተው የፈሪ በትሩን በንፁኋን ላይ በማንሳት ሰቅጣጭ ግፍ መፈፀሙን ቀጥሏል።
የደቡ ወሎ ዞን ኮማንድ ፖስት አመራሮች ጥር 20/2018 ዓ/ም በመካነሰላም ከተማ ባካሄዱት ዝግ ስብሰባ ሕዝቡ በሚፈፀምበት ጥቃት ተማሮ ከፋኖ ይርቃል፡ እንዲሁም ፋኖን ወደ አደባባይ ወጥቶ እንዲያወግዝ ያስደርግልናል ያሉትን ውሳኔ ስለመወሰናቸው ምንጮቻችን መረጃውን አድርሰውናል።
ውሳኔው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በተጠናና ተከታታይነት ባለው መልኩ በንፁኋኖች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም የማድረግ ሴራ ሲሆን፡ ይህም መካነሰላምን ጨምሮ በዞኑ ስር በምዕራብ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ነው ያሉት የመረብ ሚዲያ ምንጮች።
ሴትና ህፃናት ላይ ሳይቀር ፍፁም ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ይወሰዳል ነው የተባለው።
ወልዶ ያሳደጋቸውን ሕዝብ የሚጠሉና እየጠሉ የሚያስተዳድሩት የኦህዴድ ብልፅግና ተላላኪው በአዴን ምንጣፍ ጎታች የሆኑት የደቡብ ወሎ ዞን ካድሬዎች ያሳለፉትን ውሳኔ ሁሉም ሰው በውል ተረድቶ እራሱን ከነዚህ ሰው በላ አውሬዎች እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።