ስፔን በሃገሯ ያለ ፈቃድ ለሚኖሩ እሰከ 800ሺህ ለሚደርሱ ስደተኞች ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ልትሰጥ ነው።

ስፔን በሃገሯ ያሉ በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ስደተኞች የህጋዊ ፈቃድ ልትሰጥ እንደሆነ ገልፃለች።

የስፔን የስደተኞች ሚኒስትር ኤልማ ሳይዝ በስፔን ያለ ፈቃድ ያሉ ስደተኞች በስፔን እስከ አንድ አመት የሚቆይ የስራ ፈቃድና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ፈቃዱ የሚሰጠው ከፈረንጆቹ ታህሳስ 31፣ 2025 በፊት ወደ ስፔን ለገቡ ስደተኞች መሆኑና በስፔን ከአምስት ወራት በላይ ስለመኖራቸው ማስረጃ ለሚያቀርቡ እንደዚሁም የወንጀል ታሪክ ለሌላቸው ነው ተብሏል።

በውሳኔው በስፔን የሚኖሩ ከ500 ሺህ እስከ 800 ሺህ ስደተኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሚኒስትሩ ስደተኞቹ ፖሊሲው ወደ ስራ ከገባ በኋላ ከመጪው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው።