ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እድሜ ጠገብ ታሪካዊ ቅርሶች በአገዛዙ ወታደርች ዘረፋ ተፈፀመባቸው

በአማራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ 01ቀበሌ የአስት ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና የፋሬታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እድሜ ጠገብ ታሪካዊ ቅርሶች በአገዛዙ ወታደርች ዘረፋ ተፈፀመባቸው!

የአገዛዙ ወታደሮች ዛሬ ጥር 20/2018 ዓ/ም አዳራቸውን በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የነበሩ ቅርሶችን መዝረፋቸውን ተከትሎ በአሁን ሰዓት በአከባቢው ከባድ ውጥረት ነግሷል።

የአከባቢው ማሕበረሰብ ቅርሶቻችንን መልሱ በሚል የአገዛዙ ወታደሮችን ተቃውሞ ወደ አደባባይ የወጣ ሲሆን፡ ወታደሮቹም ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ መክፈታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ዘረፋ የተፈፀመባቸው የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና ፋሬታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከ200 ዓመታ በላይ እድሜ ያስቆጠሩ ቅርሶች መገኛ ቅዱሳን ስፍራዎች ናቸው።