የሙጃ ማርያም ከተማ ኗሪው ወጣት ባለሐብት በአገዛዙ ሰራዊት በጭካኔ ተገደለ!

የሙጃ ማርያም ከተማ ኗሪው ወጣት ባለሐብት በአገዛዙ ሰራዊት በጭካኔ ተገደለ!

በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ግዳን ወረዳ መናገሻ ሙጃ ማርያም ኗሪ የሆኑት ወጣት ባለሐብት አራጋው ሲሳይ በአረመኔው ብልፅግና ሰራዊትና አመራሮች ጥር 17/2018 ዓ/ም አመሻሽ 2:00 ሰዓት ላይ በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ አንድያ ህይወቱ ልታልፍ ችላለች።

በግዳን ወረደ ብልፅግና አመራሮችና በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት አዛዦች የጦስ ዶሮ የሆነው ወጣት ባለሐብት በተሸረበበት ሴራ 5ሚሊዮን ብር ለአብይ አህመድ ወንበር መፅናት ለሚታትሩ መከላከያ አመራሮች የሐብት ማከማቻ ግዛት እንዲከፍል፣ባይከፍል እንደሚገደል ውሳኔ ተወስኖ እንዲከፍል ሲነገረው እንደሚገድሉት ስላወቀ ካሶኒውን ሽጦ ቢከፍላቸውም የፋኖ ደጋፊ ስለሆነ መረሸን አለበት በሚል ውሳኔ በአረመኔዎቹ የጦስ ዶሮ ሊሆን ችሏል።

ይህንን ግድያ ያስተባበሩትና የውሳኔ አካል የሆኑት
1ኛ. እንዳለው አባተ:- የግዳን ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ
2ኛ. አማኑኤል አያሌው:- የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ
3ኛ. ሰማኝ ባዮ:- ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ እና
4ኛ. ሙጃ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሲሆኑ በቀጥታ በጄኔራል አሰፋ ቸኮል ትዕዛዝ ከዚህ በፊት እያንዳንዳቸው 1.5ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉና ካልከፈሉ እንደሚረሸኑ ተነግሯቸው የተጠየቁትን ከከፈሉ በኋላ ወጣቱ ባለሐብት እንዲረሸንና አፈፃፀሙን እንዲያስተባብሩ የተሰየሙ ጥቁር አማራዎች መሆናቸውን የውስጥ መረጃዎች አሳውቀዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው በመሩት የመንግስት ሰራተኞች መድረክ ላይ መንግስት አገልጋዩን ሰብስቦ ሰሞኑን የሚረሸን ሰው አለ በማለት የተናገረ ሲሆን በተናገረ ሁለት ቀን ባልሞላው ውስጥ ወጣቱን ባለሐብት አምስት መከላከያዎች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ደፈጣ ይዘው በአምስት ክላሽንኮፍ ጥይት በሳስተው ከገደሉት በኋላ ለሌሎች ትምህርት ይሆናል በማለት እጅና እግሩን በሳንጃ በመቆራረጥ፣እንዲሁም ብልቱን በመቁረጥ ህዝቡን እንዳሸማቀቁት ታውቋል።

ህዝቡም በዚህ ድርጊት ማዘኑንና ከአብራኩ በወጡት የአፉኝት ልጆች እየታረደ፣እየተሳደደ፣እየተደፈረ፣ሐብት ንብረቱ እየተዘረፈ መሆኑን በመረዳቱ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ መግባቱ ታውቋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ