በምስራቅ ጎጃም ዞን ከታፈሱ 1330 ወጣቶች መካከል 850 የሚደርሱት ከደብረ ማርቆስ ማሰልጠኛ ካምፕ መጥፋታቸው ተረጋግጧል

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከታፈሱ 1330 ወጣቶች መካከል 850 የሚደርሱት ከደብረ ማርቆስ ማሰልጠኛ ካምፕ መጥፋታቸው ተረጋግጧል”

እነዚህ አራት ወጣቶች  ደረጀ ጎሹ፣ ደሳለኝ ወርቁ፣ እንዳለ ይበልጣልና ዝጋለ ሰጤ ይባላሉ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ከመርጡለ ማርያም ከተማ መሐል አደባባይ ታፍሰው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ ከተጓዙ 110 ወጣቶች መካከል ይገኙ ነበር።

ደሳለኝ ወርቁ በመርጡለ ማርያም ከተማ ዙሪያ የሸዋት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ከአመታት በፊት በደረሰበት የአንጀት መታጠፍ በቀዶ ጥገና ህክምና ህይወቱ የተረፈች መሆኑን የሚመሰክር ለምጽ በሆዱ መሀል ተመልክተናል። ቀሪ ሶስት ወጣቶች ከተሰማሩበት የጉልበት ስራ በሚኒሻዎች ታፍሰው ከደሳለኝ ወርቁ ጋር በአንድ መኪና ተጭነው ደብረ ማርቆስ ወታደራዊ  ማሰልጠኛ እራሳቸውን ማግኘታቸውንም ከታፋሾች አንደበት ሰምተናል።

ሚኒሻዎች እየደበደቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱን በኋላ ስልካችንን ቀምተው ምሽት በአንድ መኪና አጭቀው የወሰዱን 60 የመርጡለ ማርያም ከተማ ወጣቶችና 50  የዙሪያ ቀበሌ ወጣቶች በድምራችን 110 ሁነን ደብረ ማርቆስ ከተማ ስንደርስ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ወረዳዎች ታፍሰው ከመጡት ጋር 1330 እንሆን ነበር ያሉት ወጣቶቹ በወታደራዊ ካምፕ ለ10 ቀናት መቆየታቸውን ያስታውሳሉ ።

በደብረ ማርቆስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ በገባን በሁለተኛው ቀን ለሁለት ከፍለው ወደ አዳራሽ ወስደው የሀይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ሽማግሌዎች የሚደበደቡበትን video እንድንመለከት ካደረጉን በኋላ ከዚህ ወጣችሁ ብትጠፉ ጥንፈኛው እንደዚህ ያሰቃያችኋል እያሉ ሲያሸማቅቁን እኛ እየሳቅን እንመለከታቸው ነበር እያሉ በፈገግታ የገጠማቸውን ነገር ሁሉ እያወጉን አረፈድን።

ለቀን ስራ ይሆናል ብለን በለበስነው ልብስ ስፖርት ሲያሰሩን የነበሩትም ከታፈሱት ውስጥ ግዙፍ ሰውነት ያላቸው ተመርጠው ሲሆን ከ45 ቀን በኋላ ፓራ ኮማንዶ ሁነን እንደምንመረቅ ተነግሮን ስልጠና ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ ቀን በቀን ወጣቶች እየጠፉ ወደ ሀገራቸው ሲሔዱ እኛም ጠፍተን ወደ እናተ መጠናል አዚህ ከመጣን በኋላ አስፈላጊው እንክብካቤ ተደርጎልናል በማለት ለ206ኛ ኮር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

“ፓራ ኮማንዶ “ወይንስ “ፋራ ኮማንዶ” የሚለው ሳይገባን በቀን ስራ ልብሳችን እና በባዶ እግራችን አሰልጥነው ወደ ጦርነት ሊማግዱን መሆኑን በመረዳት በማሰልጠኛ ከነበረው 1330 ታፋኝ መካከል 850 የምንሆነው እየጠፋን ወደ ፋኖ ተቀላቅለናል ያሉት እነዚህ ወጣቶች የአረመኔው ስርዓት ሰሞኑን በከተማዎች እያደረገ ያለውን የወጣቶችን አፈሳ እና ስቃይ ትክዝ እያሉ አጫውተውናል ።

በስርዓቱ ታፍሰው ከማሰልጠኛ የወጡትን ወጣቶች በመንከባከብ ላይ የሚገኘው 206ኛ ኮር በመርጡለ ማርያም ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ወጣት ልጆቻችሁን የተነጠቃችሁ እና የጠፉባችሁ የእነዚህ ወጣት ቤተሰቦች
ዛሬ ልጆቻችሁ ከወንድሞቻቸው ጎን በአስተማማኝ ሁኔታ ይገኛሉና ልጆቻችሁን ትረከቡ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!