የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን አብዱላሂ፣ አሜሪካ ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠቷ የማይቀር እንደኾነ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ፣ አሜሪካ ለሶማሌላንድ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አገር ትኾናለች የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ይህን ፍንጭ የሠጡት ትናንት ዱባይ ውስጥ በተካሄደ የዓለም መንግሥታት ውይይት ላይ ነው።
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሶማሌላንድ እውቅና ሊሠጥ እንደሚችል አንዳንድ ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ሲዘግቡ መቆየታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ፣ እስካሁን ወደ አሜሪካ አላቀኑም።