የምዕራብ አገራት አምባሳደሮች መቀሌን ጎበኙ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ መቀሌን የጎበኙ የምዕራብ አገራት አምባሳደሮች የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ፈራሚዎችና አስማሚ አካላት ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው የመመለሱን ጉዳይ ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጡት መጠየቃቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

አምባሳደሮቹ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል የተቻላቸውን ኹሉ ጥረት ለማድረግ ቃል እንደገቡም ጌታቸው ገልጸዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ውስጣዊ ፖለቲካዊ ችግር፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ፌደራል መንግሥቱና ሌሎች ባለድርሻዎች ተፈናቃዮችን በጊዜ ወደቀያቸው አለመመለሳቸው የፈጠረው እንደኾነ ከአምባሳደሮቹ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ መግባባት ላይ እንደተደረሰበትም ጌታቸው ጠቅሰዋል።

አምባሳደሮቹ፣ የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች የሥልጣን ሽኩቻቸውን ወደ ጎን ብለው፣ ተፈናቃዮችን በመመለስ ላይ እንዲያተኩሩም አሳስበዋል ተብሏል።