የደብረሲና ከተማ ከንቲባ እርምጃ ተወስዶበታል።

የደብረሲና ከተማ ከንቲባ
ወንድምሲገኝ ማሙዬ እርምጃ ተወስዶበታል።

የፋኖ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ምድብተኞች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማ በር ወረዳ መቀመጫ የሆነችው የደብረሲና ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወንድምሲገኝ ማሙዬ በድንተኛ የታጣቂዎች ጥቃት ተገደሉ። የወረዳው አስተዳደር፣ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በታጣቂዎች “በግፍ” እና በአሰቃቂ” ሁኔታ ተገድለዋል በማለት ዛሬ ባሠራጨው መረጃ ግድያውን አውግዟል። “ክፉዎች አመራሩን አካላቸውን ቢገድሉትም፣ አመራሩ ለሕዝባቸው ያሳዩትን ቅንነትና የሰሩትን መልካም ሥራ ግን ከታሪክ ገጽ ሊያጠፉት አይችሉም” ያለው የወረዳው አስተዳደር፣ አመራሩ ለደብረሲና ከተማ ልማት ሌት ተቀን የተጉ እና ለሕዝቡ ጥያቄ ቀረቤታ የነበራቸው እንደነበሩ ገልጧል። ታጣቂዎቹ የተቀዳሚ ምክትል ከንቲባውን ሕይወት ብቻ ሳይሆን ለከተማዋ የነበራቸውን ታላቅ ራእይ እና ሕልም አጨልመዋል በማለት የወረዳው አስተዳደር የገለጠ ሲሆን፣ የአንድን አመራር ሕይወት “በጭካኔ” ማጥፋት “ትልቅ አገራዊ ኪሳራ” ነው በማለትም ግድያውን ኮንኗል።