በሚኒሻና ፖሊስ አስገዳጅነት ከሦስት ወረዳዎች ተጠርተው ለስብሰባ በተቀመጡ ንፁኋኖች ላይ አገዛዙ በፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ከ100 በላይ የሚሆኑት ተገደሉ!
ከፋኖ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ያልቻለው አገዛዙ ስብሰባ በሚል ስም ንፁኋንን ከየመኖሪያ ቤታቸው ከሰበሰበ በኋላ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀምሯል።
በድሮን ጥቃቱ ንፁኋኑን በአስገዳጅነት ሰብስበው የብልፅግና መንግስትን ሕዝቡ በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች መደገፍ እንዳለበት መመሪያ ሲሰጡ የነበሩ በርካታ የሚኒሻና ፖሊስ እንዲሁም የካድሬ አባላትም አብረው ነው የተገደሉት ያሉት የመረብ ሚዲያ ምንጮች፡ ይህም አገዛዙ ሲያገለግሉት የነበሩትን ልክ እንደ ሸንኮራ አገዳ አላምጦ እየተፋቸው ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።