የአዳነሽ አቤቤ ግብር ቢሮ ” በተለመዶ የጣራና ግድግዳ ግብር እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩን ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ እንድትከፍሉ እናሳስባለን ” ብሏል።
በዚሁ መግለጫው ግብሩ የከተማ ቦታና ቤት ግብር በከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት የሚሰበሰብ ግብር መሆኑ መገንዘብ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን 429 ሺህ 829 ግብርከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል ብሏል።
የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ በሰጡት ቃል ፥ ” ግብር ከፋይ ነዋሪዎች ያለቅጣት መክፈያው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከየካቲት 30 በፊት እንዲከፍሉ እና ያልከፈሉ ነዋሪዎች ግን ቅጣቱን ከነወለዱ ለመክፈል እንደሚገደዱ ” ገልጸዋል።
አቶ ሰውነት ” እናት ፓርቲ ካስተላለፈው መልእክት ጋር በተያያዘ እኛን የሚመለከተን ነገር የለም ” ያሉ ሲሆን ለቢሮው የደረሰው ምንም አይነት የፍርድ ቤት እግድም ሆነ መመሪያ አለመኖሩን በመግለጽ ” ሰው ጋር መዘናጋት ይታያል ይህ ደግሞ ለቅጣት ሊዳርጋቸው ይችላል በቀረው ጊዜ ክፍያችሁን ፈጽሙ ” ሲሉ አሳስበዋል።