ፋኖ በጎንደር እና በወሎ ቤተአምሓራ ቀጠና በተመሣሣይ ወቅት በፈፀመው ስኬታማ ደፈጣ ጥቃት አኩሪ ድል መቀዳጀቱን አስታወቀ!

በሰሜን አማራ ቀጠና አምባጊዮርጊስ አከባቢ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት የፖሊስ አዛዡን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች ሲገደሉ አንድ ወታደራዊ ፓትሮል ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ታውቋል።

በተመሣሣይ በምስራቅ አማራ ቀጠና ገረገራ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ፡ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መንቀሳቀሻ የነበረች አንድ ወታደራዊ ፓትሮልን ጨምሮ ሌሎች ተሽከርካሪዎች መማረካቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።

በጎንደር እና በወሎ ቤተአምሓራ ቀጠና በተመሣሣይ ወቅት በተፈፀመው ደፈጣ ጥቃት፡ ፋኖ የሽምቅ ውጊያ ሳይንስ እውቀቱን ተጠቅሞ አኩሪ ድልን የተቀዳጀበት ነው የተባለ ሲሆን፡ ይህም የፋኖን የውጊያ አቅም ከፍታን በተግባር ያሳየ ነው ተብሏል።